2015-10-05 15:16:00

ሮማ፦ ቁምስናዎች ስደተኞችና ተፈናቆዮችን በማሰናገድ ግብረ ሠናይ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እያንዳንዷ ቁምስና እያንዳንዱ ሰበካ እያናንዱ አቢያተ መንፈሳዊ ማኅበር ስደተኞችና ተፈናቃዮችን በማስተናገድ ተግባር እንዲተጉ ያስተላለፉት ጥሪ በተለያዩ አገሮች የሚገኙት ሰበካዎች እግብር ላይ እየዋለ መሆኑ ሲገለጥ፣ የሮማ ሰበካ ኅይነት ቢሮ ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለውም በሮማ 80 ቁምስናዎች የተለያዩ አቢያተ መንፈሳዊ ማኅበራት የቅዱስ አባታችን ጥሪ እግብር ላይ እየዋለ ነው።

በሮማ የሚገኙት ቁምስናዎች ስደተኞችና ተፈናቆዮች ለማስተናገድ ብቃት እንዲኖራቸው በ 12 ቁምስናዎች ለመጀመሪያ እርዳታ አቅርቦት በሁለቱ ቁምስናዎች ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ እርዳታ አቅርቦት ብቃት እንዲኖራቸው ለማድርግ ያስቸኳይ የመጠለያ ቤቶች የግንባታ ሥራ እያፋጠኑ መሆናቸው የሮማ ሰበካ ኅየንተ ሐዋርያዊ ቡሮ መግለጫ ያመለክታል።

በካሪታስ ለሚጠራው ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ለሮማ ሰበካ ቅርንጫፍ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ኤንሪኮ ፈሮቺ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያቀረቡት ጥሪ የሰበካዎች የቁምስናዎች የማኅበረ ክርስቲያን የሁሉም የእያንዳንዷ ክርስቲያን ቤት ልብ እንዲከፈት ማድረጉ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው የቅዱስ አባታችን ጥሪ ለሮማ ሰበካቸው ብቻ ሳይሆን ኵላዊ ጥሪ መሆኑ በኤውሮጳና በሌሎች ክፍለ ዓለም እግብር ላይ መዋሉ ያረጋግጥልናል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.