2015-10-02 15:46:00

ቅዱስ አባታችን ለኮምቦናውያን፦ ጸሎትና መሥዋዕትነታዊ አብነት የተልእኮ ማእከል


ተልእኮ እውነት የሚሆነው ክርስቶስንና ጸሎትን ማእከል ሲያደረግ ነው የሚል ቅዉም ሃሳብ ማእከል በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኮምቦኒ ዘልበ እየሱስ ወንጌላዊ ልኡካን ማኅበር እስከ ፊታችን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. እያካሄደው ባለው የማኅበሩ አዲስ ጠቅላይ አለቃና የበላይ መማክርት የመረጠበት ጠቅላይ ጉባኤ ተሳታፍያንን የማኅበሩ አባላት እ.ኤ.አ. መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ተቀብለው በለገሱት ምዕዳን፣ ያንን ወደ የከተሞቻችን ጥጋ ጥግና ወደ የኅብረተሰብ ጥጋ ጥግ ክልል እንድንሄድ የሚያደርገን ፍቅር ከኢየሱስና ስለ ወንጌል የደም ሰማእትነት ከፍለው ካለፉት የኮምቦኒ ማኅበር አባላት እንማር እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።

ጸሎት የግብረ ተልእኮ መሠረት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የለገሱት ምእዕዳን ያንን ኮምቦናውያን ልኡካን ዘልበ ኢየሱስ በሚለው እርሱም ልበ ኢየሱስ የሚለው የማኅበሩ መለያ አበክረው፣ በቅድሚያ የወንጌል ልኡካን መሆን በተለይ ደግሞ ክርስቶስን ገና ላላወቁት ወይንም ካወቁት በኋላ ለዘነጉት ማበሠር የሚል ነው። ስለዚህ የማኅበሩ መንፈሳዊ ተልእኰ ከኢየሱስ ጋር መሆንና ወንጌል ማበሰር ማለት ነው። ገዛ እራስ ስለ ወንድሞች መስጠት የሚለው አጽብ ድንቅ ሃብት በጸሎት ከጌታ ጋር ከመሆን የሚታደል ጸጋ ነው። ከኢየሱስ ጋር መሆን በጠቅላላም እኛነታችንና ተግባራችንን ይወስናል፣ ይኽ ዓይነቱ መሆን የሚጎለብተውም በጸሎት ከጌታ ጋር በመሆን በቅዱስ ቁርባን ፊት ከማስተንተን ከእርሱ ጋር ልብ ለልብ በመገናኘት ነው። ከላይ የሚመጣ ፈጣን በሆነ ሁነት የለውጥ ባለ ቤት በሆነው ኅብረተሰብ የሚያቀርበው ተግዳሮት በሚገባና በተስተካከለ ብቃት ባለው ቋንቋና በሚገባ ማስተግበሪያ ለመግጠም የሚያስችለው ጥበብ ከእግዚአብሔር ቃል ነው የሚገኘው።

የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ወደ ኅብረተሰብ ጥጋ ጥግ ይገፋፋል

ኮምቦናዊ ዘቅዱስ ልበ ኢየሱስ መሆን ማለት ቅዱስ ዳኒኤል ኮምቦኒ የተቀበለው የተልእኮ መንፈሳዊ ጸጋ መመስከር የሚል ሲሆን፣ እርሱም መኃሪው የኢየሱስ ልብ ፍቅር ለተናቁት ከለላ ለሌላቸው ለብቻቸው ወደ ሚተዉት ለማቅረብ የሚገፋፋ ነው። ስለዚህ በተወሳሰበው አስቸጋሪ ሁኔታና እምቢ ባይነት ሁሉ ለመግጠም የሚያስችል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለማቅረብ የሚያበቃ ጥበብ እንታደል ዘንድ ቅዱስ ልብን እንለምነው።

ያ የሰው ልጅ እጅግ የወደደው ልብ ወደ የኅብረተሰብ ጥጋ ጥግ የዚያ ታጋሽና ታማኝ የሆነው ጽኑ ፍቅር ለመመስከር ይገፋፋናል፣ የደማው የኢየሱስ ልብ ከማስተንተን ዘወትር በዚህ ባለንበት ዘመን ያንን ነጻው የጌታ ፍቅር በጠና ችግር ውስጥ ወደ ሚገኙትና ንኡሳን ወደ ሆኑት በመሄድ በፍቅር የሚገለጥ ትብብርና ድጋፍ ይሆንልናል፣ እንዲህ ባለ ሁነትም ፍትህ ሰላም መከባበርና የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ዘወትር ለማነቃቃት ትችላላችሁ።

የብዙ የኮምቦናውያን ሰማእንታት አብነት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የኮምቦኒ ማኅበር አባላት እስካለንበት ዘመን ድረስ የደም ሰማዕትነት የከፈሉት የኮምቦኒ ልጆች አብነት ተከተሉ አደራ፣ የእነዚያ ስለ ወንጌል የደም ሰማዕነት የከፈሉት ኮምቦናውያን ወንድሞቻችሁ ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋት ዘርና የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተልእኮዋችሁ ጠባቂያን ናቸው፣ ብለው ቅዱስነታቸው ለኮምቦናውያን ያላቸው አክብሮትና አድናቆት ገልጠው፣ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ከመሰናበታቸው ቀደም በማድረግም በእውነቱ እናንተ የምትጋፈጡት አደጋ፣ የምታከናውኑት አገልግሎት ምክንያት ለእናንተ ትልቅ አድናቆትና አክብሮት እንዲኖረኝ ማረጉንም ልገጽላችሁ እወዳለሁ እንዳሉ ኦንዳርዛ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.