2015-09-30 15:45:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዓሥረኛው ዓለም አቀፋዊ ሓዋርያዊ ዑደት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኩባና በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት እንዲሁም በተባበሩት መግንሥታት ድርጅት ያከናወኑት ሓዋርያዊ ዑደት ሁሉም የመገናኛ ብዙኃን ታሪካዊ በማለት ገልጠዉታል፣ ቅዱስነታቸው በዚህ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ዑደት ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለመላ ዓለም ኅብረሰብ ጭምር የተናገሩት መለስ ብለን ስንቃኝ፦  

በቅድሚያ ድልድይ መገንባት የሚል በዚህ ግጭት ውጥረት በተሞበት ዓለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሉም ለያይ ግንብ ሳይሆን አገናኝ ድልድይ ገንቢ ሆኖ እንዲገኝ በማለት ጥሪ አቅርበዋል። ይኽ ደግሞ ማኅበራዊ ውጥረት ይልቅ ማኅበራዊ ወዳጅነት ከመለያየት ብቃት መቀራረብና አንድነት የሚያሳስብ ነው።

በርእዮተ ዓለምና በእምነታዊ ጽንሰ ሓሳብ ውስጥ አለ መዘጋት፦ ከውጫዊው ጠላት ነጻ መሆን ስንሞክር ለውስጣዊ ጠላት መቀመጫ ልንሆን እንችላለን እርሱም ለጥላቻ መንፈስ የተገዛን ልሆን እንችላለን፣ እምነት ገዛ እራስ ክፍት ማድረግ ማለት ነው፣ ትምክህተኝነት ያገላል፣ እምነት ለምርጦች ለጥበበኞች ላዋቂዎች ብቻ አይደለም እምነት ለሁሉም መሆኑ አሳስበዋል።

ታናናሾችን በማገልገል እጅግ በላቀ ተግባር እየሱስን ማገልገል፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚያ አሥረኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደታቸው አማካኝነት የፍቅር አመክንዮ በጥልቀት ገልጠውልናል፣ የምንከተለው አመክንዮ የሚያናጋ፣ ለተናቁት ለተጠሙት ለታረዙት ለተጨቆኑት ማገልገል የሚል ፍቅር። የፍቅር የላቀው ትርጉም፣ በባለንጀራህ ፊት ያንን ማራኪው የጌታን አርአያና አምሳያ መመልከት። ማፍቀር እሩቅ ያለውን በሃሳብ ሳይሆን አጠገብህ ያለውም በተግባር ቀርቦ ማገልገል ማለት ነው። ትሁታንን የታመሙትን ያንን አለም የሚንቀው እንደ ውዳቂ የሚምለከተው ድኻው ጽንስ በማስወረድ ተግባር ለሞት የሚዳረገውን የሚመርጥ ፍቅር መኖር።

የእኛ አብዮት የርህራሄና በየዋህነት የሚያልፍ ነው፦ ክርስቲያናዊ አብዮት የፍቅር ያሳቢነት የየዋህነት አብዮት ነው። ይኽ ደግሞ ድኻውን ሚስኪን ብሎ የሚያልፍ ሳይሆን ጉልበትን አጥፎ ማገልገል የሚል ከተቸነከረበት አስከፊው ሁኔታ ነጻ ማውጣት ማለት ነው። አለ ምንም ፍርሃት ያንን ሕይወትን ከሚለውጠው የኢየሱስ ምህረት ጋር መገናኘት። ቅዱስ አምብሮዚዩስ እንደሚለውም ምህረት ባለበት የኢየሱስ መንፈስ አለ፣ ድርቅናና ግትር ባይነት ባለበት ደግሞ ተልእኮ እንደ ሙያ ይኖራል፣ ይኽ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የወሲብ ዓመጽ ሰለባ ከሆኑት ዜጎችና ከእስረኞች ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት በቃልና በሕይወት መስክረዉታል።

ቁሳዊ ባርነት፦ በመንፈስ ድኾች የሆኑት ብፁዓን ናቸው፣ ቁሳዊ ሃብት በትክክልና በተገባ ሂደት ማስተዳደር ያስፈልጋል። በሚገባ ማስተዳዳር ሲባል የቁሳዊ ሃብት ተገዥ መሆን ማለት አይደለም፣ የመንፈስ ድኽነት፣ ደግነት የዋህነትን ይወክላል በእግዚአብሔር መተማመንን ያነቃቃል።

ከቤተ መቅደሶችዋ የምትወጣ ቤተ ክርስቲያን፦ የተቀበልነው የእግዚአብሔር ሕላዌ ባለንበት የሚያስቀር ሳይሆን እንንቀሳቀስ ዘንድ ወደ ሌላው እናቀና ዘንድ ይገፋፋናል፣ እርሱም የተቀበልነውን ደስታ እናካፍለው ዘንድ ነው። ከጓዳ መወጣት ከቤተ መቅዶሶችዋ የምትወጣ ቤተ ክርስቲያን፣ ለሕዝብም የተወሳሰበውን አንቀጸ እምነት በማቅረብ ሳይሆን በፍቅር መሸኘት በፍቅር ማገልገል፣ በትህትና ቀርቦ ማገልገል ኢየሱስ ሞቶ ሞትን አሸንፎ ተነሣ የሚለው ደስታ ማካፈል ነው ልብን ሞቅ የሚያደርግ። ቅዱስ የእግዚአብሔር ሕዝብ መሳሳትን አይፈራም መዘጋትን እንጂ፣ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ የወንጌል ሐሴት አበስሩ፣ ይኽ ደግሞ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚያሳትፍ ተልእኮ ነው።

ተስፋ ሕይወትን ይሰጣል፦ በዚህ ዓለማችን በተለያየ ቀውስ በተጠቃበት በአሁኑ ወቅት ቅዱስ አባታችችን ተስፈኝነት ሳይሆን ተስፋን ያነቃቃሉ። ተስፋ መሰቃየትን ያውቃል ሊደረስ የታለመው ዓላማ የሚጠይቀው መስዋዕትነት አያስፈራውም፣ እውነተኛው ተስፋ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እማኔ ማኖር ነው።

የሓሰት አንድነት ለመገንባት ከመሻት መለያና ማንነትን ማቀብ፦ ዓለማዊነት ትሥሥር ለገዛ እራሱ መልካም ነው። ነገር ግን ሁሉን አንድ ዓይነት ቀለም እንዲኖራቸው ለማድረግ ሲሞከርና አንዳዊ አድማስ ለማልበስ ሲፈለግ፣ አንዳዊ መለያ እንዲጠለቅ ሲያስገድድ፣ ጎጂ ይሆናል። ኅብረአዊነትን የሚያከብር መለያና ማንነትን የሚያከበር ዓለማዊነት ትሥሥር አወንታዊ ነው።

ነጻነትና ፍትህ የማይነጣጠሉ ናቸው፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኩባና በአመሪካ ደጋግመው አንዲት አገር ታላቅ የሚያስብላት የሁሉም ነጻነትና ሰላም ተከላካይነቷ ነው። ፍትህ የነገሰባት ስትሆን ነው። ስለ ተጨቆኑት ስለ ሚሰቃዩትና ስለ ድኾች የሁሉም ሰብአዊ መብትና ክብር እንዲጠበቅ ፍትህ የነገሰባት ስትሆን ነው። ምኅዳርን መንከባከብ ባጠቃላይ ሊደረግልህ የምትፈልገው ሁሉ ሌሌላው ማድረግ፣ የሚል አባባል አማካኝነት የውሁዳን የኅብረተሰብ ክፍል ባህል ሃይማኖት ሁሉ እንዲከበር የሚያሳስብ የጦር መሣሪያ ንግድ የሚያወግዝ መልእክት ነው።

ቤተሰብ መንከባከብ ስለ መጻኢ መቆርቆር ማለት ነው፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የአስረኛው የዓለም አቀፋዊ ሓዋርያዊ ዑደት ዋና ዓላማው ቤተሰብ የሚል ሲሆን፣ ቤተሰብ ዙሪያ እንዲመክር የጠሩት የመላ ካቶልካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ የሚጀመርበት ቀን በተቃረበበት ወቅት፣ የምንኖርበት ዓለም ቤተሰብ የሚወልደው አድነት እያስወገደ ዋዘፎነት ማለትም ስብስብነት እያረጋገጠ ነው። በስብስብነትና በዋዘፎነት የማንነት መለያ አይኖርም፣ እውነተኛ ግኑኝነት አይኖርም፣ እየተስፋፋ ያለው የአንድ ኅብረተሰብ ባህልና መለያ የሚጻራር ሁሉን ዋዞፎ የሚያደርግ ያኗኗር ሥልት አምባ ገነን በሆነበት ዓለም ስለ ቤተሰብ መብትና ክብር መሟገት ወላጆች የልጆቻቸው አስተዳደግ ተቀዳሚ ኃላፊነት እንዳላቸው እውቅና መስጠት አዳጋጅ እየሆነ መጥተዋል። የቤተሰብ ውበትና ውህበቱ የሚያጎላ ከዚህ ጋር የተስተካከለ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማረጋገጥ። በሚል ጥልቅ ሃሳብ ለማጠቃልል የሚቻል ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.