2015-09-30 15:54:00

ማርቲነዝ፦ ቤተሰብ ዙሪያ የቅዱስ አባታችን አስተምህሮ ለእንዳሻህ አተረጓጎም ዕድል አይሰጥም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቤተሰብ ዙሪያ የሰጡት የሚሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ ለእንዳሻህ እተረጓጎም ላሻሚነት ዕድል የሚሰጥ አለ መሆኑ በፊላደልፊያ በተካሄደው ስምንተኛው ዓለም አቀፋዊ የቤተሰብ ጉባኤ የተሳተፉት የካቶሊካዊ ተኃድሶ በመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ሳልቫቶረ ማርቲነዝ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውሳኔ መሠረትም ቀጣዩ በ 2018 ዓ.ም. የሚካሄደው ዘጠነኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ በዱብሊን የሚስተናገድ መሆኑ አስታውሰው፣ ቤተሰብ ሊዘነጋ አንደማይገባውና የፖለቲካው ዓለም ቤተሰብ የሚንከባከብና ቤተሰባዊነት የሚያነቃቃ መሆን እንደሚገባው ቅዱስ አባታችን ካለ መታከት ጥሪ እያቀርቡ ናቸው፣ ለቤተሰብ ተገቢ ሥፍራ የማይሰጥ ኅብረተሰብ ማሰብ እንደማይቻልና፣ ስለ ቤተሰብ የሚቆረቆር ኅብረተሰብ እንዲጸና እግዚአብሔር ይሻል።

በፊላደልፊያ የቤተሰብ ጉባኤ ዋዜማ ቅዱስ አባታችን፣ ፍጹም የሚባል ቤተሰብ የለም፣ ይኽ ደግሞ ተስፋ ሊያስቆርጠን አይገባውም፣ ባንጻሩ ፍቅር በሕይወት የምንማረው የሚኖር ዕለት በዕለት የሚያድግ መሆኑ ገልጠውታል። በሁሉም ውጣ ውረድ ውስጥ ፍቅር የሚወለድ የሚጎለበትና የሚኖር ጭምር ነው። ፍቅር ለዚያ ግጭት የመደምደሚያ ቃል ለሚያደርግ ቤተሰብ የሚቻል ነው። ስለዚህ ቤተሰብ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው የሚለው እውነት የሚኖርበት ነው። ችግር ስቃይ መከራ ሁሉ፣ ገዛ እራሳችንና ሌሎችን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ የሚያነቃቃ መንገድ መሆኑ ቅዱስ አባታችን አብራርተዋል።

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማዳን ገዛ እራሱ ሰው ሆኖ ለመምጣት በቤተሰብ ውስጥ ይወለዳል፣  በቤተሰብ በኩል ወደ ዓለም ሥጋችን ለብሶ ለመምጣት የመረጠው እግዚአብሔር ቤተሰብ ያለው ቅዱስ ክብር ምን ተመስሎው ገልጦልናል። አለ ቤተሰብ የአንድ ኅብረተሰብ መጻኢ ለአደጋ ይጋለጣል። ቅዱስ አባታችን የጠሩት እፊታችን እሁድ የሚከፈተው ሲኖዶስ ምስጢረ ተክሊል እጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ አይደለም፣ ምስጢረ ተክሊል የአንቀጸ እምነት ክፍል ነው ስለዚህ ይኸንን የአንቀጸ እምነት ክፍል በምንኖርበት ዓለምና በአሁኑ ወቅት እንዴት መኖር እንዳለበት ወቅታዊው የዓለም ሁኔት አንቦ መንገድ የሚያመላክትና የሚመለከተውም መንገድ ቤተሰብ ዙሪያ ለሚወጠነው ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ደጋፊ ይሆናል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.