2015-09-28 16:27:00

ቅዱስ አባታችን ፦ የሃይማኖት ነጻነት በሰው ልጅ በኑባሬ ያለ ባህርይ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ  ልክ 4 ሰዓት ተኩል ከላቲን አመሪካውያንና ከስደተኞች ማኅበርሰብ ጋር ተገናኝተው     ከፊላደልፊያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ጆሰፍ ቻፑት ከቀረበላቸው የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ቀጥለው በለገሱት ምዕዳን፦

ውዶቼ ይኽ የምንገኝበት የነጻነት ማል ሥፍራ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት አገር የትውልድ ቀን የሚያስታውስ ነው ብለው የሰው ልጅ ካለው ሰብአዊ ክብሩ ጋር በሚጣጣም መንገድ በነጻነት ለመኖር የሚያካሂደው ትግል ትእምርት የሆነ ሥፍራ ነው።

የዚህ አገር ሕዝብ ለዚያ ቀደምት የአገሪቱ አበው አገሪቱን ለመመስረት ለተከተሉና እግብር ላይ ላዋሉት እሴቶች ታማኝ የመሆን ኃላፊነት አለበት። ያንን የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር በታደሰ መንፈስ አደራ ኅያው አድርጉ።

ቅዱስ አባታችን የተገኙበት ሥፍራ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት አርአያ መሆኑ የሚያረጋገጥ ነው። ከእናንተ ጋር ሆኜም ስለ የሃይማኖት ነጻነት ለማስተንተን እወዳለሁ ብለው፣ የሃይማኖት ነጻነት መሠረታዊ የሰው ልጅ መብትና ክብር ነው፣ ከሁሉም አጠገባችን ከሚገኘው ከእኛ እምነት የተለየ ሃይማኖት የሚከተል ሁሉ ለማክበርና ተከባብሮ ለመኖር ተጠርተናል። ስለዚህ የተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ግኑኝነትና ውይይት አለ ምንም መራራቅና ጸብ መኖር እንዳለበትም የሃይማኖት ነጻነት ሰብአዊ መብትና ክብር የሚያዘው ለመከበበር የሚያነቃቃ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

የሃይማኖት ነጻነት በግልም በማኅበረሰብም ደረጃ ለእግዚአብሔር ስግደትና አምልኮ ማቅረብ የሚመለከት ነው። የሃይማኖት ነጻነት በባህርዩ የአምልኮና የስግደት ሥፍራ ልቆ የሚሄድ ክብር ለበስ ነው። ምክንያቱ ሃይማኖተኛነት ሰው በኑባሬ የተሰጠው ባህርይ ነውና።

ሃይማኖቶ አዲስ አድማስ፣ አዲስ አስተሳሰብ የሚያነቃቃ አመለካከትን የሚያሰፋ ለመለወጥ ለእርቅ የኅብረተሰብ ብሩህ መጻኢ ለመገንባት የሚያነቃቃ ለጋራ ጥቅም መስዋዕትነት የሚያነቃቃ ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አያይዘው፦ ማድረ ተረዛ ዘካልኵታን ጠቅሰውም የሃይማኖት ባህላችን ሌላውን ለመቀበል መጠራታችን ያስገነዝበናል ብለዋል።

የምንኖርበት ዘመን ዓለማዊ ትሥሥር የተላበሰ ግብረአዊ ሙያ የሚገዛበት ነው። የባህሎች ልዩነት ማግለለም ሁሉም አንዳዊ ቀለም ምድረግ ይሆናል። ዓለማዊ ትሥሥር አሉታዊ አይደለም፣ ሆኖም ሁሉም አንድ ቀለም እንዲኖረው የሚያደርግ ሲሆን በርግጥ አሉታዊ ሆኖ ነው የሚቀረው፣ የሕይወት ባህል ማቀብ ማክበር፣ ድጋፍ ለሚያስፈልገው ቅርብ መሆን ለስደተኛው መተባበር። እናንተ ባንድ ወቅት ስደተኞች የነበራቸሁ በዚህች አገር መስተንግዶ አግኝታችሁ የምትኖሩ በተራችሁ ደጋፊያን የመሆን ኃላፊነት ይጠበቅባችኋል። …. ውዶቼ ላደራግችሁሉኝ የሞቀ አቀባበል ከልብ አመስገናችኋለሁ። ነጻነትን እንንከባከብ፣ እናነቃቃ እንጂ ነጻነትን አንበድል ለተሳሳተ ዓላማ አናውል፣ ከእግዚአብሔር የተሰጣችሁ ጸጋ ነውና። የሃይማኖት ነጻነታችሁን ተንከባከቡ፣  እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ አደራ ስለ እኔ ጸልዩ ብለው ጌታ ያስተማረው ጸሎት አብረው እዛው ከተገኙት ጋር ደግመው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.