2015-09-25 16:41:00

በቅዱስ ፓትሪክ ካቴድራል ቅዱስነታቸው ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር ተገናኝተው አጽናኝ ቃል ለገሱ


እ.ኤ.አ. መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በካቴድራል ቅዱስ ፓትሪክ የሚገኘውን የግብረ ሠናይ ማእከል ጎብኝተው እንዳበቁ ከጎዳና ተዳዳሪ ዜጎች ጋር ተገናኘው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይላሉ ከእናንተ ጋር እንድገናኝ ፈቅዳችሁ እዚህ ድረስ መምጣታችሁ አመስገናችኋለሁ በሕይወት ችግር ውጣ ውረድ ሲያጋጥመኝ እምማጠነው ቅዱስ ቢኖር ቅዱስ ዮሴፍ መሆኑ ልናዘዝላችሁ እወዳለሁ፣ ካጋጠሙት ችግሮችም አንዱ ማርያም ይዞ በመጓዝ ላይ እያለ እርሷ እረጉዝ ስለ ነበረች “በቤተልሄም ከተማ ሳሉ ማርያም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ በዚያም የበኵር ልጅዋን ወለደች በመታቀፊያ ጨርቅ ጠቀለለችው በእንግዶች ማደርያ ስፍራ ስላላገኙ በበረት መመገቢያ ግርግም ውስጥ አሰተኛችው” (ሉቃ. 2, 6-7) መጽሓፍ ቅዱስ ግልጽ ነው። እንዴ የእግዚአብሔር ልጅ እያለ እንዴት ማደሪያ ስፍራ እያገኝም የሚል ጥያቄ በቅዱስ ዮሴፍ አእምሮ እንደሚብሰለሰል እያጠራጥርም፣ ይኽ ጥያቄ ዛሬ እናንተ እንዴት ሆኖ ነው ማደሪያ ቤት እማላገኘው በማለት በምታቀርቡት ጥያቄ ይደገማል ኅያው ነው፣ በእናንተ ጥያቄ ያ የቅዱስ ዮሴፍ ጥያቄ ኅያው ነው። ለዮሴፍ ብርሃን የሆነውም እምነቱ ነበር። ኢየሱስ ግልጽ ነው ተርቤ አብልታችሁኛል ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል እንድግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛል ታርዤ አልብሳችሁኛል፣ ታምሜ ጠይቃችሁኛል ታስሬ ጎብኝታችሁኛል … (ማቴ. 25,35) ጥያቄውና ፍርዱም ምን መሆኑ ከወዲሁ ገልጦልናል፣ ስለዚህ ተግባራችን ምን መሆን እንደሚገባው ተነግሮናል፣ ኢየሱስ ዛሬም ከሚሰቃዩት ጋር ይሰቃያል፣ ለእርሱ ያለን ፍቅር ብቁ መመዠኛዎት እናንተ ናችሁ። በእናንተ አማካኝነት ያለው የእርሱ ኅላዌ ነው የሚመራን ያለው። በጸሎትና በግብረ ሠናይ እንተሳሰብ፣ እግዝአብሔር ይባርካችሁ፣ በለጋስነቱም ይድረሳችሁ፣ በፍቅሩ ይጠብቃችሁ፣ አደራ ስለ እኔ ጸልዩ ብለው ያስደመጡት ቃል እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.