2015-09-25 16:32:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ጋር


እ.ኤ.አ. መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ ልክ 11 ሰዓት ተኩል በቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ ካቴድራል ከመላ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ጋር እንደተገናኙ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዋሽንግተን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ዶናል ወርልና በመቀጠልም የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ሊቀ መንበር የልዊስቪለ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ኤድዋርድ ኩርትዝ ካስደመጡት የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ቀጥለው በለገሱት ምዕዳን፦

እ.ኤ.አ. መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በዓለ ዮም ኪፑር ለሚያከብሩት የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች ወንዶሞቻችን መልካም በዓል እመኛለሁ ኦሪት ዘሌዋውያን “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም እንደ እኔ ቅዱሳኖች ሁኑ” እግዚአብሔር በቅዱስና ጎዳና ወደፊት እንዲሉ ያበረታታቸው ብለው፣ በሁሉም የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳትና በአገሪቱ ከምትገኘው በእናንተ እረኝነት ሥር ለምትምራው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመማን ሰላምታ የሚያስተጋባ ለቀረበላቸው የእንኳን ደህና መጡ መልእክት አመስግነው፣ በአገራችሁ ሓዋርያዊ ዑደት እንዳከናወን ቅድም ዝግጅቱን በማዋደድ ለማስተናገዴ ያሳያችሁን ትብብር አመስገናችኋለሁ።

በእናንተ በኩልም እንደ መልካም እረኛ በትከሻችሁ በማኖር በፍቅር የምትመርዋት በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ለምትገኘውን መላይቱን ቤተ ክርስቲያን በፍቅር በእቅፌ አኖራታለሁ፣ በእናንተ ብኩልም ለመላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ቅርበቴን አረጋግጡልኝ አደራ።

በአገልግሎታችሁ ር.ሊ.ጳ. እንደሚሸኛችሁ ለማረጋገጥ እወዳለሁ፣ ያጽናናችኋል ይደግፋችኋል ምንም’ኳ ያረጁ እጆች ያሉት ቢሆንም በእግዚአብሔር ጸጋ ተደግፌ እደግፋችኋለሁ።

በወንጌላዊ ፍቅር ተነቃቅታችሁ በአገራችሁ ለክርስቶስ ቤት በሆነቸው ቤተ ክርስቲያን በኩል ለመላ የአገሪቱ ሕዝብ የምትሰጡት ድጋፍ የላቀ ነውና እግዚአብሔር ይመስገን። ለሐዋርያዊ ወንበር በመላ ዓለም ለአስፍሆተ ወንጌል፣ ለሚሰቃየው ሕዝብ የምትሰጡት የድጋፍ አስተዋጽኦ የሚደነቅ ነው።

በግብረ ሰናይ አገልግሎት ለስደተኞች የምትሰጡት አገልግሎት ለአገራችሁ ያላችሁ ፍቅር የሚመስከር ተግባር ነው። … ሳትፈሩ ያንን ቤተ ክርስቲያናችሁን የሚያዋርድ መስዋዕትነት የሚጠይቅ የሚያጋጥማችሁ መሰናክል ወቀሳን ክስ ሳትፈሩ ምንም’ኳ እራቁት የሚያስቀር ቢሆንም ቅሉ ያ የክርስቶስ አገልጋይ መሆን የሚጠይቀው ታማንኝነትና ኃላፊነት ዳግም በማበከር በብርታትና በጽናት በመጋፈጥ የምታሳዩት ትሁት አገልግሎት በቅርብ የማወቀው ጉዳይ ነው።

እኔ የሮማ ጳጳስ በእግዚአብሔር ጥሪ የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዳቅብ ከአመሪካ ክፍለ ዓለም የመጣሁኝ መላይቱ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ፍቅር በእውነት በእምነት እንድታድግ በማድረጉ ጥሪ እንደሚያገለግል ጳጳስ ነው እፊታችሁ ሆኜ የምናገረው። የቤተ ክርስቲያን ስቃይ አልዘነጋውም አቀበት ተራራው ለማስተናገድ የማይመች ሁኔት ሁሉ እንደዚያች ያገራችሁ የሥነ ግጥም ሊቅ የበረቱ የማይዝሉ ክንፎች ያስፈልጋል፣ ሆኖም ጥበበኛው እንደሚለውም ተራራውን ለይቶ መዋቁ ጭምር ያስፈልጋል ብለዋል።

እምናገራችሁ ሁሉ ከእኔ በፊት ያለፉት ኣርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ያሉትን የሰጡትን ትምህርት የሚያስተጋባ ነው ብለው፣ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የመጀመሪያቱ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በባልቲሞራ የተገባች መሆንዋንም በአመሪካ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ አስታውሰው፣ ከእኔ በፊት የነበሩት የሦስት አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉብኝት የታደላችሁ ናችሁ።

የምትከተሉት ሐዋርያዊ መርሃ ግብር ለመወጠንና ልፈርድ ሳይሆን፣ እንደ አንድ መምህር የጥናት ትምህርት ለማቅረብም ሳይሆን እዚህ በመካከላችሁ የምገኘው በዚያ ሁሉ ነገር በሚያስተምረው ጌታ ላይ በመተማመን ከፍቅር በሚመነጭ ነጻነት እንደ አንድ በወንድሞችሁ ፊት እንደሚናገር ወንድም ሆኜ ነው በመካከላችሁ እምገኘው።

የቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ነን፣ የእግዚአብሔር በጎችን እንዲንከባከቡ እግዚአብሔር እረኞች እንድንሆን የጠራን ነን። ታላቁ ደስታችን እረኞች መሆናችን ላይ የጸና ነው።

በእዚአብሔር እይታ የሚመለከቱ ያንን የእግዚአብሔር ቤተሰብ የሆነው መንጋ ለመመገብም ገዛ እራስን ዝቅ ማድረግ አለ እረፍት ጸንቶ መንቃት የሚያውቁ መሆን ያስፈልጋል።

ቤተ ክርስቲያን እንደ ነበልባል እሳት የምትማርክ መሆን አለባት፣ በእርግጥ ማንኛውም ዓይነት እሳት ትሁን ማለት ሳይሆን ያ በፋሲካ ማለዳ የሚበራው እሳት መሆን እንዳለባት ለማሳሰብ ነው፣ ያ ሞትን አሸንፎ የተነሣው ኢየሱስ ዛሬም የሚበላ ምግብ አላችሁ ወይ ሲል ይጠይቀናል፣ የዛሬው ድምጹም ያ ጥያቄ ነው። ድምጹን ማስተዋል ያስፈልጋል፣ የእርሱ ኅላዌ ሲዘነጋ የዚያ የእውነተኛና ልብን የሚያግለው ብርሃን አዳዮች ሁኑ በሚለው ተእኮአችን ድካም እናሳያለን። ለሕዝብ ቅርብ ሁኑ እረኞች ሁኑ አደራ፣ ቅርቦችና አገልጋዮች ሁኑ።

ስለ ስደተኞች ብናገር ይቅርታ አድርጉልኝ ስለ ገዛ እራሴ ለመናገር ብየ አይደለም፣ እንደ የሮማ ጳጳስ ብቻ ሳይሆን ከደቡብ ዓለም እንደ የመጣሁ በመሆኔ ስለ ስደተኞች ጉዳይ ለመናገር እወዳለሁ፣ ለስደተኞች ለተፈናቃዮች በምታቀርቡት ድጋፍ ላመሰግናችሁና ላበረታታችሁ እወዳለሁ፣ በእርግጥ ስደተኛ ኅብረአዊ በመሆኑ መንፍሱን ታነቡለት ዘንድ ከብድ ሊላችሁ ይችል ይሆናል፣ ሆኖም ስድተኛው የሚያካፍለው ሃብት እንዳለው ማስታወስ ይኖርብናል፣ ለማስተናገዱ አትፍሩ፣ የክርስቶስ የሞቀው ፍቅሩን አቅርቡለት። እነዚያ ስደተኞች አመሪካንና በአመሪካ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን እድገት እንደሚሆኑ አርግጠኛ ነኝ።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ ቅድስት እመቤት ታቅባችሁ

እግዚአብሔር ይስጥልኝ ብለው የለገሱት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.