2015-09-25 16:55:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የጋራ ጥቅም በመገንባት ማንኛውንም ዓይነት ዓመጽ መቃወም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከተጠዋቱ ልክ 10 ሰዓት በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ምክር ቤት ምሉእ ጉባኤ ተገኝተው ታሪካዊና በሞቀ ጭብጨባ የተሸኘ ንግግር እንዳስደመጡና ቅዱስ አባታችን ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ምክር ቤቱ ንግግር ያስደመጡ የመጀመሪያ ር.ሊ.ጳ. መሆናቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማሲሚሊያኖ መኒከቲ አስታውቀዋል።

ቅዱስነቸው ወደ ምክር ቤት የጉባኤ አዳራሽ እንደገቡም ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ከተቀመጡበት በመነሳት የእንኳን ደህና መጡ መግለጫ የሞቀ ጭብጨባ በማቅረብ ከተቀበሉዋቸው በኋላ ባስደመጡት ንግግር፦ ምክትል ሊቀ መንበር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር፣ ክቡራት የምክር ቤቱ አባላት ሁሉ ሰላምታን እቅርበው

ወዳጆቼ

በዚህች የነጻነት መሬትና የከበሩ እሴቶች ቤት በሆነችው አገር ምክር ቤት ተገኝቼ ንግግር እንዳስደምጥ ላደረጋችሁልኝ ጥሪ አመሰግናለሁ ብለው ገዛ እራሳቸው የአመሪካ ዓቢይ ክፍለ አለም ተወላጅ መሆናቸው አስተዋውቀው፣ በቀጥታ የምክር ቤቱ ተመራጮች የሚወክሉትን ሁሉ የጋራ ጥቅም እርሱም አንድነትና መደጋገፍ ሁሉ በቀላሉ ላደጋ ሊጋለጥ የሚችለውን ለመከላከል የሚለው ክቡር እሴት ለማረጋገጥ በሚደረገው ፖለቲካዊ ጥረት የሚያጋጥሙት ተግዳሮችን በማስታወስ፣ የምክር ቤቱ አባላት እንደ የእስራኤል ልጆች አባትና የሕግ ሊቅ፣ በሕግ አማካኝነት እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር አምሳያ የተፈጠረ መሆኑ ለመከላከል የተጠሩ ናቸው ብለዋል።

ዛሬ ለእናተን የምለው ቃል በእናንተ በኩሉ ለመላ የተባበሩት የአማሪካ መንግሥታት ሕዝብ አቀረባለሁኝ

የጋራ ጥቅም ተካፍሎ በመኖር ይኖር

ወንዱም ሴቱም ለመንግሥት ግብር ከፋይ ብቻ ሳይሆን ዕለት በዕለት በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልገው ሁሉ ድጋፍ በማቅረብ የኅብረተሰብ ሕይወት የሚገነቡና የሚደግፉ ናቸው ብለው ይኸንን ጉዳይ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት አናሥር ላይ በማተኮር የዛሬው ተጨባጩ ሁነት በታሪክ የአገሪቱ ዜጎች እንደ አብራሃም ሊንኮልን ማርቲን ሉተር ኪንግ ዶሮትይ ደይና ቶማስ መርቶን የመሳሰሉትና ሌሎች የአገሪቱ ዜጎች የበለጠ መጻኢ የጋራ ጥቅም በተካፍሎ የመኖር ሂደት ለማረጋገጥ መስዋዕትከት የከፈሉትን ታላላቅ ሰዎች ታሪክ ጋር በማዛመድ ገልጠዉታል።

አንድ ሕዝብ ወደፊት ለማለትና ይኸንን በክብር ለመከወን በአገሪቱ ታላላቅ ሰዎች አብነት ተሸኝቶ የተለያዩ ቀውሶች ውጥረቶችና ግጭቶች ያልፋል።

አብርሃም ሊንኮልን፦ ነጻነትና ሥጋት

በዚህ የነጻነት ጠበቃና አቃቢ የሆው የአገሪቱ ርእሰ ብሔር አብራሃም ሊንኮን የተገደለበት 150ኛው ዓመት በሚዘከርበት በአሁኑ ወቅት፣ ነጻነት የተካነው መጻኢ ለመገንባት ለጋር ጥቅም ፍቅር፣ ለሌለው የአበል ድጋፍ የሚልና የመተባበር መንፈስ ያለው አስፈላጊነት የማያጠያይቅ መሆኑ ያረጋግጥልናል፣ የምንኖርበት ዓለም ግጭትና አመጽ ጥላቻና አሰቃቂ ተግባር ይባስም ይኽ ዓይነት አሰቃቂ ተግባር በእግዚአብሔርና በሃይማኖት ስም የሚፈጸምበት ሆነዋል። ማንኛውም ዓይነት ሃይማኖት ለግላዊ የአታላይነት ወይንም ለርእዮተ ዓለማዊ አክራሪነት ፈተና የተጋለጠ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ እላይ ከጠቁሱት ሃሳብ ጋር በማያያዝ ክፋትና መልካም  ብፁዕናና ኃጢአት ብሎ ለሁለት ለሚከፋፍለው ፈተና እጅ ሳይሰጥ፣ የሃይማኖት ነጻነት የቀልብ ነጻነት የግል ነጻነት መንከባከብ ያስፈልጋል። ገዳዮች ወይንም አምባገነኖችን መምሰል ሳይሆን እንደ ሕዝብ እነዚህ ጸረ ሰብአዊ የሆኑትን ተግባሮች እምቢ ማለት ይኖርባችኋላ።

ሰላም፦ ቃል የተገባውን ማክበርና ማረጋገጥ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሰላም ለማረጋገጥ ማለም፣ ስህተቶች ማረም የተገባው ቃል ማክበር በዚህ አኳያ የግልና የሕዝቦች ጥቅም ማነቃቃት ያስፈልጋል። በዚህ መሠረተ ሕንጸትም የእምነት ድምጽ ያለው ጠቀሜታ ማስተዋል ይኖርብናል። ምክንይቱም እምነት በእያንዳንዱ ሰውና በሕብረተሰብ ዘንድ ያለው መልካምነት እንዲጎላ ለማድረግ የሚደግፍ ነውና። በታደሰ ፖለቲካና አዲስ ማኅበራዊ ስምምነት በተካነ ሂደት አማካኝነት መፍትሔ ሊያገኙ ከሚገባቸው ከተለያዩ ኢፍትሓዊ ተግባሮች የሚወለዱት በዓለም የሚታዩት አዳዲስ የባርነት ቅርጾች ሁሉም ለማጥፋት ሁሉም እንደየኃላፊነት አስተዋጽኦ መስጠት ይኖርበታል።

ማርቲን ሉተር ኪንግ፦ ስደተኞችና መስተንግዶ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከሰልማ እስከ ሞንቶጎመርይ የጥቁር አመሪካ ዜጎች ለተሟ ሰብአዊ ፖለቲካዊ መብትና ክብር አክብሮት ያለመ ማርቲን ሉተር ኪንግ የመራው  የሰላም የእግሩ ጉዞ አስታውሰው፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ ባለ ተግባር የገለጠው ህልም ዛሬም ባለፉት የመጨረሻ ዘመኖች ወደዚህች አገር ለገቡት በሚሊዮን ለሚገመቱ ሕዝቦች ኣስተንፋሶ ሆነዋል።

እኛ የዚህ ክፍለ ዓለም ሕዝቦች ስደተኞችን መፍራት አይገባንም፣ ምክንያቱም ባንድ ወቅት ሁላችን ስደተኞች የነበርን ነን። ይኸንን የምላችሁም እኔ ለገዛ እራሴ የስደተኛ ቤተሰብ ልጅ መሆኔ በማስተዋልና እዚህ በምክር ቤቱ በአባላነት ከምትገኙት ውስጥም ባንድ ወቅት ስደተኞች የስደተኛ ቤተሰብ ተወላጆች ሊኖሩ እንደሚችሉ በማስተዋል ነው ብለዋል።

አዱሱን ትውልድ ለጎረቤትህ ቅርብ ላሌለው ጀርባውን እንዳይሰጥ እናንጸው ብለው፣ ወዳጄ ማን ነው? በአሁኑ ሰዓት የሚታየው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነፍ ፍጻሜ ወዲህ ያልታየው የስደተኞች ጸዓት ተከስተዋል። ሌላውና ጎረበቴ ወዳጄ እርሱ ነው። ሁሉም ሊደረግልህ የምትሻው አንተም በተራህ ለሌላው ማድረግ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ብዙ ውጣ ውረድ የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም። ዋስትና የምንሻ ከሆን ዋስትና እንስጥ ሕይወትን የምንሻ ከሆን ሕይወትን እንስጥ እድል የምንሻ ከሆን እድል እንስጥ።

የሞት ፍርድ ማስወገድ

እያንዳንዷ ሕይወት የተቀደሰች ነች፣ እያንዳንዱ ሰው የማይታበል ክብር የተካነ ነው። ስለዚህ ኅብረተሰብ ወንጀለኛው ዳግም በሰላም ከኅብረተስብ ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር በማድረግ ያተርፋል እንጂ ትርፉ ለሞት በመዳርግ አይደለም።

ዶሮትይ ደይ፦ ማኅበራዊ ፍትህ ተፈጥሮን መንከባከብ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የካቶሊክ ሠራተኞች እንቅስቃሴ የመሠረተቸው የእግዚአብሔር አገልጋይ ዶሮትይ ደይን አስታውሰው፣ ዶሮትይ፣ ሰዎችን ከከፋ ድኽነት ለማላቀቅ በኖረቸው ሕይወት የማኅበራዊነትና የፍትኃዊነት አብነት ነች። በዚህ በአሁኑ ወቅት ተከስቶ ባለው የኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት አደራ መተባበርና መደጋገፍ እንዳይጠፋ፣ የድኽነት ቀንበር ለመስበር ማንም የማይነጥል ሁሉንም የሚያቅፍ ለጋራ ጥቅም  የሚል ተፈጥሮን የሚያከብር የሰለጠነ ኤኮኖሚ ያስፈልጋል። ወቅቱ የመንከባከብ ባህል ለማረጋገጥ ጽናትና የተዋጣለት ሥልት የሚያስፈልግበት ሁነት ነው። ተፈጥሮን ለመንከባከብና ድኽነት ለመዋጋት ሁሉም እንዲተጋ ቅዱስነታቸው ባስደመጡት ንግግር አደራ እንዳሉ ሚኒከቱ ገለጡ።

ቶማስ መርቶን፦ የሕዝቦች አገናኝ ድልድይ መገንባት

ቅዱስ አባታችን የቺስተርንቸስ ማህበር አባል ባህታዊ የጸሎት ሰውና አስተዋዩ ሊቅ ቶማስ መርቶን አስታውሰው፣ በሕዝቦችና በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ሰላም በማነቃቃት የኖረበት የልዩነትና የጥላቻ መንፈስ የተሞላው ኅብረተሰብና ሥርዓት ሁሉ ተጋፍጠዋል። ከዚህ ጋር በማያያዝም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታትና በአገረ ኩባ መካከል የጸናው አዲሱ ግኑኝነት በማስታወስ አደራ አገናኝ ድልድይ እንገንባ፣ የሰላም የውይይት መሣሪያ እንሁን ብለዋል።

የጦር መሣርያ ንግድ ይቁም

በጦር መሣሪያ አቅርቦት የሚፈጸመው በደም ንጹሓን በሚበከለው ሃብት የመደለቡ ጉዳይ ቅዱስነታቸው አውግዘው፣ አስነዋሪውና በዝምታ በመልከቱ ምርጫ ተጠያቂነት እንዲኖረን የሚያደርግ የጦር መሣሪያ ንግድ እቅርቦት ያብቃለት።

ቤተሰብ

ቅዱስነታቸው ባስደመጡት ንግግር በፊላደልፊያ የሚካሄደው ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ በማስተዋል፣ ለኅብረተሰብ ግንባታ ቤተሰብ ያለው ማእከልነት አስገንዝበው፣ ቤተሰብ ያለው መሆናዊ ሃብትና ውበት ለማስተጋባት እወዳለሁ፣ ያ የቤተሰብና የትዳር መሠረት የሆነው ሰብአዊ ግኑኝነት እጥያቄ ውስጥ ሲገባ ማየቱ እጅግ ያሳዝናል።

ወጣቶች

በአሁኑ ወቅት ወጣት ትውልድ ቤተሰብ ላለ መመሥረት ምርጫ በሚዳርግ ባህል የተጠቃ ሆነዋል። ስለ መረጠው ሳይሆን መጻኢ የመገንባቱ ዕድል በማጣቱና አልፎ አልፎም ተስፋ አልቦ ነጻነት መሳይ አመጽ ተስፋ ቀቢጽነትና ለተለያዩ አመጽ ሰለባ እንዲሆን ይኽ ሁነት በከፋ ባርነት እንዲኖር ስለሚዳርገውም ነው። የወጣቱ ችግር የእኛ ችግር ነው ብለው ለወጣቱ ትውልድ ከፍ ያለ እድል እንዲፈጠርለት አደራ፣ ይህች ብዙ ሰዎች መልካም ህልም እንዲያልሙ ያደረገች መሬት ወጣቶች ያንን ያለፉት አበይት የአገሪቱ ልጆች አስተንፍሶ እንዲያደርጉ አደራ።

ለሁላችሁም የእግዚአብሔ ርቡራኬ እማጠናለሁ፣ ቤተሰቦቻችሁ ልጆቻችሁ ጌታ ይባርክ፣ ጌታ የአመሪካ ሕዝብ ይባርክ፣ እያንዳንዳችሁ ይባርክ፣ አደራ ስለ እኔ ጸልዩ፣ ከእናንተ ውስጥ የማያምን ካለም ደግሞ መልካሙን ይመኝልኝ ዘንድ አደራ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ

እግዚአብሔር አመሪካን ይባርክ ብለው ያስደመጡት ንግግራ እንዳጠቃለሉ ሚንከቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.