2015-09-23 16:43:00

ቅዱስ አባታችን፦ ቤተሰብ ወደ ፊት ለመጓዝ የእርስ በእርስ መፈላለግ አስፈላጊ መሆኑ የሚያንጽ ቤት ነው


ቅዱስ አባታችን ያሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንዳበቃም በኵባ ሰዓት አቆጣጠር በሳንቲያጎ ደ ኩባ ወደ ፍልሰታ ለማርያም ካቴድራል ተዛውረው ልክ 11 ሰዓት ወደ ካቴድራሉ እንደገቡም በብፁዕ አቡነ ጋርሲያ ኢባኘዝ እና ምእመናን አቀባብል ተድርጎላቸው ብፁዕ አቡነ ኢባኘዝ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ካስደመጡ በኋላ ቅዱስነታቸው ከቤተሰብ ጋር ተገናኝተው የአንዲት ቤተሰብ ምስክርነትና የዮሓውንስ ወንጌል ምዕ.2 ከቁጥር 1 እስከ 11 ንባብ ከተደመጠ በኋላ ስብከት ማሰማታቸው የቫቲና ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ ገለጡ።

የቅዱስነታቸው 10ኛው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ዋነኛው ዓለማ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ፊላደልፊያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ስምንተኛው የቤተሰብ ጉባኤ መገኘት የሚል ጉባኤውን በንግግር ለማስጀመር የሚል መሆኑ ያበከሩት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ አያይዘው ቅዱስ አባታችን የኩባ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው አጠናቀው ወደ ተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ከመነሳታቸው ቀደ በማድረግ በለገሱት ስብከት፦

ቤተሰብ ወደ ፊት ለመጓዝ የእርስ በእርስ መፈላለግ አስፈላጊ መሆኑ የሚያንጽ ቤት ነው

በዚህ በአሁኑ ወቅት የቤተሰብ ቤተሰብአዊ ሁነት ሲጠፋ ሁሉም ወደ መከፋፈልና ወደ ብቸኝነት ሕይወት ሲያቀና ይታያል፣ ቤተሰብአዊ ቀርቶ ወደ ተራ ክምርነት ስብስብነት እየተዘለቀ ነው። እያንዳንዱ ሰው ወደ ደሴታዊ ብቸኝነት ይለወጣል፣ ይኽ ደግሞ በቀላሉ ለመጠማዘዝ ለሚቃጠው መስተዳድር ምቹ ይሆናል። በቤተሰብ ለጭምብልነት ሥፍራ አይኖርም፣ እንደ መሆናችን የምንኖርበትና የሌላው መልካም የምንሻበት ሥፍራ ነው። ለእኔ ባይነት በሁላችን ውስጥ ያለ ስሜት ነው፣ ሆኖም በቤተሰብ ቤተሰብአዊ መንፈስ ሳይኖር ሲቀር ያ ትንሹ ለእኔ ባይነት ስሜት ግዙፍ ይሆናል፣ በርእሰ ማእከልነት መኖር ይጀመራል። ወድማማችነት ትብብር በጋራ በሥራት ፍቅርና ውይይት ለመኖር ያዳግታል።

አለ ቤተሰብ መጻኢ አይኖርም፣ አባትና እናት መርሳት አለ መጻኢ ያስቀራል

መጻኢን ማሰብ ክቡር ውርሻ የሆነው ቤተሰብአዊ ዓለም ማሰብ ማለት ነው። ባዶ ቤት እርሱም የጉዕዝነት ባዶ መሆን የሚያመለክት ሳይሆን የእርስ በእርስ ግኑኝነት የተነፈገ፣ ሰብአዊ ግኑኝነት የሌለው ይቅርታ የማይኖርበት መተሳሰብ የማይኖርበት ማለት ነው። ስለዚህ የእርስ በእስር ሰብአዊ ግኑኝነት ባዶ ሲሆን አባት እናት አያቶች የሚዘነጉበት ሲሆን ሰው መሆን ሰብአዊነት የምንማርበት መሠረታዊ የሆነው እውነት እናጠፋለን።

እግዚአብሔር በዕለታዊ ሕይወት እውነት ይገለጣል፣

በዕለታዊ ሕይወት የእግዚአብሔር ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ ድንቅ ስራ ይገልጥልናል፣ የቃና ዘገሊላ ሰርግ እናስተውል፣ ኢየሱስ ተልእኮው በይፋ የጀመረበት ሥፍራ ነው። ብዙውን ጊዜም ማእድ እራት ቤተሰብ መጎብኘትን ያዘወትራል፣ እርሱም የእግዚአብሔር እቅድ ለመግለጥ ነው። ኢየሱስ አይለይም፣ እንዳውም ቀራጮች ኃጢአተኞችን እንደ ዘኪዮስ የመሳሰሉን ይመርጣል፣ ምህረትን እንድናጣጥም ወደ ቤታችን ይገባል። እየሱስ የዕለታዊ ሕይወት ድካምና ውጣ ውረድ ሁሉን ያውቀዋል። ስለዚህ የዕለታዊ ሕይወት ገጠመኝ ሊያስፈራን አይገባውም፣ በቤተሰብ ውስጥ በባልና ሚስት መካከል አለ መግባባት ቢፈጠርም የጦፈ ውይይት መጋጨትም ቢታይበትን ሊያስፈራን አይገባውም። ይኸንን ዕለታዊ ሕይወት ኢየሱስ ጠንቅቆ ያውቀዋል። ቤተሰብ የእግዚአብሔር ተጨባጭና ተግባራዊ ፍቅር የሚገለጥበት ስፍራ ነው። ድህነት ምኅረት ይቅር መባበል።

ከዚህ ጋር በማያያዝ ቅዱስ አባታችን በፊላደልፊያ የሚካሄደው ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ በማሰብ በዚህ የሳንቲያጎ ካቴድራል የተሰበሰቡትን የኵባ ቤተሰቦችን በዚህ ባካሄዱት ጉብኝት ቤተኛ ሆነው እንዲሰማቸው በማድረጋቸውም አመስግነው፣ በቤተሰብ ሁሉም ቤተኛ ነው። የኵባ ቤተሰብ ተቀባይ ቤተኛነት እንዲሰማህ የሚያደርግ ደግ ቤተሰብ ነው ብለው ጥቅምት ወር እንዲካሄድ የጠሩት ቤተሰብ ዙሪያ የሚመክረው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አስታውሰው፣ በፊላደልፊያ ስለ ሚካሄደው ዓለም አቀፋዊ የቤተሰብ ጉባኤና ሊካሄድ ስለ ተጠራዊ ሲኖዶስ አደራ ጸልዩ፣ ሁላችን ስለ ቤተሰብ እናስብ ቤተሰብን እንንከባከብ አደራ ጸልዩ።

ቅዱስ ቁርባን የኢየሱስ ቤተሰብ ማእድ ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ይኸንን ቅዱስ እራት እንዲያዘወትር አደራ፣ ቅዱስ ቁርባን የቤተሰባዊነት ኅያው ሥፍራ ነው ብለው ስለ ተደረጋላቸው አቀባበልና መስተንግዶ ሁሉ አመስግነው አደራ አያቶች አረጋውያን እንዳይዘነጉ፣ ህያው ተዘክሮ ናቸው። ሕፃናት ወጣቶች የሕዝብ ጉልበት ናቸው። አረጋውያን አያቶች ሕፃናትና ወጣቶች የሚንከባከብ ሕዝብ ዋስትና አለው። እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ አደራ ስለ እኔ ጸልዩ ብለው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ አስታወቁ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.