2015-09-20 17:57:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአሥረኛው ዓለም አቀፍ ሓዋርያዊ ጉዞ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለአሥር ቀናት የሚያካሄዱትን አሥረኛውን ዓለም አቀፍ ሓዋርያዊ ጉዞአቸን ለመጀመር ትናንትና ጥዋት በቫቲካን ከሚገኘው የቅድስት ማርታ መኖርያ ቤታቸው ሽኝት ተደርጎላቸው ከለዮናርዶ ዳቪንቺ ፍዩሚቺኖ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ደግሞ የክልሉ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጂኖ ረአሊ የሚገኝዋቸው የስንብት ሽኝት አድርገውላቸዋል፣ በሮም ሰዓት አቆጣጠር አሥር ተሩብ ተነሥተው ከአሥራ ሁለት የበረራ ሰዓቶች በሰላም በሃቫና ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አሥራ አንድ ሰዓት በጆሰ ማርቲ ዓለም አቀፍ የሃቫና አየር ማረፍያ ደርሰዋል፣

የክዩባ ፕረሲደትን ራውል ካስትሮ የሃቫና ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ኦርተጋ ኢ አላሚኖ የቅዱስነታቸው እንደራሴ ኑንስዮ አፖስቶሊኮ በክዩባ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጆርጆ ሊንግዋ እና ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች የሚገኙባቸው ታላቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፣ ከአየር ማረፍያ እስከ ከተማ ባለው የአሥራ ስምንት ኪሎሜትር መንገድም ከአንድ መቶ ሺህ በላይ የሚሆን ሕዝብ ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ቅዱስነታቸውም ክፍት በሆነ መኪና ሰላምታ እያቀረቡና እየባረኩዋቸው በሕዝቡ መካከል እንዳለፉ ከቦታው የመጣ ዜና አመልክተዋል፣

በአለም አቀፉ አየር ማረፍያ በተደረገው አቀባበል የቅድስት መንበርና የክዩባ አገራዊ መዝሙሮች ከተዘመሩ በኋላ የክዩባ ፕረሲደንት ራውል የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ካደረጉ በኋላ ቅዱስነታቸውም ለመላው የክዩባ ሕዝብ በአገር ውስጥ ለሚገኙና በመላው ዓለም በስደት ለሚገኙ ሰላምታ አቅርበው ፕረሲደንት ራውል ለወንድማቸው ፊደል ካስትሮ ልዩ ሰላምታቸውና አክብሮታቸው እንዲያስተላልፉ ጠይቀዋል፣ አጋጣሚውን በመጠቀም የጠቀሱት ሌላ ነገር ደግሞ ቅድስት መንበርና ⷍዩባ ዲፕሎማስያዊ ግኑኝነት ከመሠረቱ አለምንም ማቋረጥ ሰማንያኛ ዓመቱ እያከበረ መሆኑን ነው፣

ከሳቸው በፊት ክዩባን የገበኙ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊና ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛና በማስታወስም ፈራቸውን እንደሚከተሉ አረጋግጠዋል፣

“ቤተ ክርስትያን የክዩባ ሕዝብ በሚያደርገው የተስፋ ጉዞና በሚያሳስብዋቸው ነገሮች እንደምትሸኛቸው ነጻ በሆነ መንገድና በሁሉም የመገናኛ ዘርፍ ወንጌልን ከዳር እስከ ዳር ለመስበክም ትቀጥላለች” ሲሉ ቤተ ክርስትያን ከክ ዩባ ሕዝብ ጐን መሆንዋን ገልጠው አገሪቱንና ሕዝብዋን በእመቤታችን ድንግል ማርያም በማማጠን ንግግራቸውን ደምድመዋል፣

ከዚህ በመቀጠል ለአሥራ ስምንት ኪሎሜትር ያህል ተስልፎ ባጀባቸው ሕዝብ መካከል እየተጓዙ በሃቫና በሚገኘው የቅድስት መንበር እንደራሴ ኑንስዮ አፖቶሊኮ መኖርያ ቤት በመድረስ ራታችውን በልተው እዛው አድረዋል፣

ዛሬ ጥዋት ሃቫና ከተማ በሚገኘው ታላቁ አደባባይ ማለት አብዮት አደባባይ ቅዳሴ አሳርገዋል፣ አደባባዩ እስከ ስድስት መቶ ሺህ ሰዎች ሊያስተናግድ ይችላል፣

በቅዳሴው የተነበበው ወንጌል ስለ ትሕትና የሚናገረው ማር 9፤30-37  “ከዚያም ወጥተው በገሊላ በኩል አለፉ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ያስተምር ስለ ነበር ማንም ያውቅ ዘንድ አልወደደም፤ ለእነርሱም። የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጣል፥ ይገድሉትማል፥ ተገድሎም በሦስተኛው ቀን ይነሣል ይላቸው ነበር። እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉም፥ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ። በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱ ግን በመንገድ። ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? ተባብለው ነበርና ዝም አሉ። ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠርቶ። ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን አላቸው። ሕፃንም ይዞ በመካከላቸው አቆመው አቅፎም። እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም አላቸው። 

 

የሰማነው ወንጌል ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን “በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ?” በማለት ቀላል ያልሆነ ጥያቄ ያቀርብላቸዋል፣ ዛሬም ቢሆን ለእያንዳንዳችን “በየዕለቱ የምታወሩት ስለምንድር ነው? ፍላጎቶቻችሁ ምን ነው?” ሊጠይቀን ይችላል፣ ወንጌሉ እንደሚተርከው ሓዋርያት ዝም አሉ! ኃፍረት ዋጣቸው! ይህ ትናንትና ሓዋርያት የተናገሩት ዛሬም እኛ እርስ በእርሳችን “በመካከላችን የላቀ የበለጥ ማን ነው?” እንላለን፣ ኢየሱስ ሊነግሩት ግድ አይላቸውም! ጥያቄው ግን ገና በአእምሮአቸው ሳይሆን በልባቸው ነበር፣ ይህ ጥያቄ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሆኖ ሁሌ ያስቸግረናል፣ ስፍራው በልብ ስለሆነ ልናስወግደው አንችልም፣ አንዳንዴ ቤተሰብ ለልጆቻቸው አባትህን ነው ወይስ እናትህን እጅግ የምትወደው? ብለው ሲጠይቁ ሰምቼአለሁ፣ ከሁሉ በላይ የሚያስፈልጋችሁ ማን ነው እንደማለት ነው፣ ይህ ጥያቄ ለሕጻናት ግዝያዊ ጨወታ ቢመስልም የሰው ልጅ ታሪክ ግን ለዚህ ጥያቄ በሚሰጠው መልስ ተከናወነ፣

ኢየሱስ የሰው ልጅ ጥያቄዎች አያስፈሩትም! ሰብአዊ ባህርይም አያስፈራውም! እርሱ በልብ ታምቆ ያለውን ስለሚያውቅ ቀስ ቀስ ሊሸኘንና ሊያስተምረን ይሻል፣ ስለሆነም ጥያቄዎቻችንና ፍላጎቶቻችንን ቀስ በቀስ ትክክለኛ ፈር እንዲይዙ ይረዳናል፣ ለሁሉም የሚሆን የፍቅር ጐዳናን ያሳየናል፣ ይህ መንገድ ለሁሉም የሚሆን ነው፣

ኢየሱስ የሚያቀርብልን የሕይወት ጐዳና ብልጥ ለሆኑና ለተመረጡ ብቻ የሚሰጥ ወይንም ልዩ የመንፈሳውነት ደረጃ ላላቸው ሳይሆን ለሁሉም የሚሆን በዕለታዊ የሕይወት ኑሮ የሚያገለግል ብሎም ወደ ዘለዓለማዊው ሕይወት የሚመራ ቀለል ያለ መንገድ ነው፣

ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? ለሚለው ጥያቄ ኢየሱስ ቀለል ያለ መልስ ይሰጣል “ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን አላቸው” ታላቅ ሊሆን የሚወድ ሌሎችን ያገልግል እንጂ ሌሎች እንዲያገልግሉት አያድርግ፣ ታላቁ የኢየሱስ ትምህርት ይህ ነው፣ ሓዋርያቱ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ማን ይሆን! በክብር ቦታ የሚቀመጥስ! ከሕግ በላይ ሆኖ እንደፈለገው ሊያድርግ የሚችል ማን ይሆን! ሥልጣን ይዞ የበለጠ ጥቅም የሚያገኝ ማን ይሆን! ይሉ ነበር፣ ኢየሱስ ግን ይህንን ፍላጎታቸው ቀለል ባለመንገድ ይቋጨዋል “እውነተኛ ሕይወት ሌሎችን በማገልገል ነው” ይላቸዋል፣ ሌሎችን የማገልገል ጉዳይ ተጠንቅቀን ማየት ያለብን ጉዳይ ነው! አገልግሎት ሲባል በታላቅ ጥንቃቄ ደካማውን ተጐጂ የሆነውን እርዳታ የሚያስፈልገውን መርዳት ነው፣ ይህ ዓይነት ሰዎች በቤተሰቦቻችን በማኅበረሰባችን በሕዝባችን ይገኛሉ፣ ኢየሱስ እንድንረዳቸው የሚያቀርብልን በስቃይ ያሉ የሚከላከልላቸው ያላገኙ የተጐዱ ወገኖች ናቸው፣ ለእነርሱ ያደርግነውም ለእርሱ እንዳደረግነው መሆኑን በመጨረሻው ፍርድ ቀን ይገለጣል፣ ክርስትያን መሆን ማለትም ሌሎችን ለማገልግል መዘጋጀት ለሌሎች መብት መኖር ማለት ነው፣ ለዚህም ክርስትያን ሁሌ ጉዳዮችንና ፍላጎቶቹን እጐን አስቀምጦ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወንድሞቹን ማገልገል አለበት፣

ሌላ ዓይነት አገልግሎት ማለትም የጥቅም አገልግሎትም አለ፣ ከዚህ ፈተና መጠንቀቅ ያስፈልጋል፣ ጉዳዮቻችን በሚል ሽፋን የግል ጉዳዮችን የማመቻቸት ሁኔታ አለ፣ ሁላችን ለክርስትና የተጠራን ለአገልግሎት የተጠራን ነን፣ ይህንን የምናደርገው ደግሞ በጥቅም አገልግሎት ፈተና እንዳንወድቅ እርስ በእርሳችን እየተጋገዝን ነው፣ ስለኢየሱስ ፍቅር ስንል ደግሞ ሌሎችን በማስቀደምና በማገልገል ሲሆን ምናልባትም አጠገባችን ያለ ሰው ምን እየሠራ ነው እርሱስ አይሠራም እንዴ ከሚለው ፈተና ለመራቅ “ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን” የሚለውን የኢየሱስ ቃል እተግባር ላይ እናውል፣ በማለት ሰብከዋል፣  








All the contents on this site are copyrighted ©.