2015-09-18 16:25:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ጦርነትና ውጥረት ለማርገብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጥረት መጓደል፣ የቤተ ክርስቲያን ድጋፍና ትብብር ለሁሉም


ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የተራድኦ ማኅበራት ጋር በመተባበር የውሁድ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት በጦርነትና በታመሰው ክልል የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ርእስ ዙሪያ እንዲመክር የጠራው ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም. መጀመሩ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተጋብእያኑን ተቀብለው በለገሱት ምዕዳን፣ በኢራቅና በሶሪያ ተከስቶ ያለው ስቃይና መከራ እልቂት የሚያዛምተው ቀውስ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ብቃት የተሳነው ይመስላል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ገለጡ።

በኢራቅና በሶሪያ ተከስቶ ያለው ግጭት በክልሉ ሕዝብ ላይ ለመግለጥ የሚያዳግት ስቃይ ከማስከተሉም ባሻገር በክልሉ ባህላዊ ውርስ ሊፈወስ የማይቻል አቢይ ጠባሳ እያስከተለ መሆኑ የገለጡት ቅዱስ አባታችን፣ በብዙ ሚሊዮን የሚገመተው የክልሉ ሕዝብ ቤቱንና ንብረቱ ጥሎ ለመሰደድና ለመፈናቀል አደጋ እያጋለጠ ነው። እንዲህ ባለ ወደ ወደ ሌላው የዓለማችን ክልል እየተዛመተ በክልሉ ሚዛኑ የጠበቀው ውስጣዊውና ክፍለ ዓለማዊው ሁነት የሚያወክ ጭንቀት የሚያሳድረው ግጭት መፍትሔ እንዲያገኝ በቂ መልስ ለመስጠት የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ብቃት የተሳነው ሲመስል፣ የጦር መሣሪያ ንግድ አቅራቢዎች የገዛ እራሳቸው ጥቅም በማርካቱ ረገድ አለ ምንም ችግር ሲንቀሳቀሱ ይታያል እንዳሉ ሎሞናኮ አስታወቁ።

የመገናኛ ብዙኃን በሚሰጡ ዜናዎች አማካኝነትም እየተስፋፋ ያለው የግጭቱ አሰቃቂነትና የሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ ተግባር ሁሉ ለማንም የተሰወረ እንዳይሆን አርገዋል፣ ማንም እንዳላየ ሆኖ መኖር አይችልም፣ በጦርነቱ ምክንያት ለስቃይ ለተጋለጠው የድኻው ሕዝብ ሁነት ሁሉም ግንዛቤው አለው፣ የሚበጀውም አለ ምንም ቅድመ ሁኔት መፍትሔ ማፈላለግ ነው፣ መልሱም የጦር መሣሪያ ሊሆን አይችልም፣ ምክንያቱም ሌላ አዲስ ውጥረት ያስከትላልና።

ተከስቶ ባለው ግጭት እጅግ ተጠቂው ድኻው የክክሉ ሕዝብ ቤተሰቦች አረጋውያን ህሙማን ሕጻናት ናችው፣ ከገዛ አገሩ የሚባረረው ለቅትለት አደጋ የተጋለጠው የደም ሰማዕትነት እይከፈለ ያለው የክልሉ ማኅበረ ክርስቲያን የጠቀሱት ቅዱስ አባታችን አያይዘው ለዚያ ክልል ሕዝብ ቅርብ በመሆን የሰብአዊ እርዳታ በማቅረብ የሚረባረቡት የተራድኦ ማኅበራት ሁሉን በማበረታታት በሶሪያ በኢራቅ እየተዘራ ያለው የክፋት መንፈስ የሕዝብ ሕይወት ለሞት ከመዳረግ አልፎም የክልሉ መዋቅራዊው ቅርጽ እያወደመ በተለይ ደግሞ የሰው ልጅ ኅሊና እያመከነ ነው፣ እባካችሁ ምንም’ኳ የዚያ ክልል ሁነት ከዓለም ትኵረት ሳያገኝ ቢቀርም አደራ የአመጽ ሰለባ የሆነውን ሕዝብ ለብቻው አንዳይተው” በማለት የለገሱት ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.