2015-09-16 16:07:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ቤተ ክርስቲያን እናት እንጂ ድርጅት አይደለችም


ቤተ ክርስቲያን እናት እንጂ በጽኑ ሕጎች ላይ የቆመች ድርጅት ወይንም ማኅበር አይደለችም። ድርጅትና ማኅበር ስትሆን ወላጅ አልቦ ሆኖ ትቀራለች። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ እንደ ተለመደው ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም. የቤተ ክርስቲያን ኅዳሴ አስፈጻሚው የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ አባላት በጠቅላላ ዘጠኙ ብፁዕና ካርዲናሎች በማሳተፍ ቀጥለው ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ቅድስት ድንግል ማርያም የትህትና የደግነት የርህራሄ ባህርይ ያለው የእናትነት መንፈስ የምትኖር መሆን አለባት በሚል ቅውም ሃሳብ ላይ ያጠናነረ ስብከት መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን በላቲን ሥርዓት ከዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 19 ከቁ. 25 እስከ 27 የተወሰደውን ቃለ ወንጌል አስደግፈው፣ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ይህችውልህ እናትህ ሲል ለሚወደው ደቀ መዝሙር የተናገረው ቃል ማርያም እናት መሆንዋ ካለ ማስተዋል ስለ እርሷ ማሰብ እንደማይቻል ያረጋግጥልናል።

ኢየሱስ ወላጅ አልባ እንድንሆን አይተወንም፣ እምትንከባከብ እናት አለችን

የማርያም እናትነት ኢየሱስ በዚያ እነሆ ልጅሽ በማለት በሰጣት ልጅ አማካኝነት ድንበር የለሽ እናት ሆናለች። ይኽ ኵላዊነት እናት ከመስቀል የተሰጣት ጸጋ ነው። የምንኖርበት ዓለም በተለያየ ምክንያት በወላጅ አልባነት በሽታ የተጠቃ ሆነዋል፣ ሆኖም ኢየሱስ ወላጅ አልባ አልተዋችሁም እነሆ እናታችህ ሲል እናቱን በመስጠተ አረጋግጦልናል።

ቤተ ክርስቲያን እናታ እንጂ አለ ሰብአዊ ፍቅር የጸናች ድርጅት አይደለችም

ባህታውያን ሩሲያውያን መንፈሳዊ ሁከት ሲያጋጥ ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም መጐናጸፊያ ሥር እንወሸቅ፣ ወደ እርሷ እንሂድ ይላሉ፣ ይኽ የሰጡት ምዕዳን ቅዱስ አባታችን በለገሱት ስብከት አስታውሰው፣ ማርያም ተቀብላ ከለላ ትሆንልናለች፣ ቤተ ክርስትያን እናት ነች፣ ቅድስት እናት ነች፣ ቤተ ክርስቲያን በሚሥጢረ ጥምቀት አማካኝነት እኛን ትወልዳለች፣ እንደ ማኅበረሰብ እንድናድግ ትደግፈናለች፣ ቤተ ክርስቲያንን አለ የእናትነት መንፈስ ማሰብ አይቻልም፣ አለ እናትነት መንፈስ ሕግ ላይ የጸናች ማሕበር ሆና ትቀራለች።

ቤተ ክርስቲያን አለ የእናትነት መንፈስ ሥርዓትና የደረቀ ሕግ ሆኖ ትቀራለች

ቤተ ክርስቲያን እናት ነች እንደ እናትም ሁላችንን ትቀበለናለች፣ በትህትና በመስተንግዶ የስቃይ ተካፋይ በሆነው የእናትነት መንፈስ አማካኝነት ሁላችንን ትቀበለናልች፣ ትንከባከበናለች፣ እናትነት ባለበት ሥፍራ ሁሉ ሕይወት አለ፣ ደስታ ሰላም ማደግ አለ። እናትነት ሳይኖር ሲቀር ወይንም በሌላ ነገር ሲተካ፣ ሕይወት የሌለው ሥርዓትና ደረቅ ሕግ ይኰናል፣ ጌታ ሆይ ዛሬ ለእያንዳንዳችን ልጄ ሆይ እናትህ ይህችውልህ ይበለን በሚል ጸሎት የለገሱት ስብከት ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.