2015-09-16 15:57:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በኢየሱስ ፍቅር ሕመምተኛን መንከባከብ


እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢየሱስ ፍቅር ሕመምተኛውን መንከባከብና የጤና ጥበቃ አገልግሎት መስጠት ያለው አስፈላጊነት ያበከረ መልእክት ከወዲሁ እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ድንግል ማርያም ስቃይ አስባ በዋለችበት ቀን  ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስነታቸው የቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ምስል በማለት የሚገልጡት በወንጌል የሚነገረው የቃና ዘገሊላው ሠርግ ማእከል ባደረገው መልእካቸው፦

ኢየሱስ በናዝሬት የድኅነት ተእልኮውን አንድ በማለት የጀመረበት ቅዱስ ሥፍራ መሆኑ አብራርተው፣ ብዙውን ጊዜ አንድ በጠና የታመመ ሰው በውስጡ ለምን ይኽ በሽታ ለእኔ አጋጠመ፣ ለምን እኔ በማለት የሚያቀርበው ልሙድ የኅልውና ጥያቄ ቅዱስ አባታችን በመልክእክታቸው በማቅረብ፣ ይኽ ጥያቄ የሰው ልጅ ጥልቁና ውስጣዊው መሆኑን የሚመለከትና የሰው ልጅ ህልውና ወደ ቀውስ የሚመራ ከመሆኑም ባሻገር እቢተኛነት የሚያነቃቃ የህልውና ጥያቄ ነው ብለው ይኽ ደግሞ ወደ ቀቢጸ ተስፋ ፈተና የሚገፋፋ ሁሉም ነገር ትርጉም የለውም ወደ ሚለው የህልውና ማጠቃለያ የሚመራ ነው። በርግጥ እምነት በሽታ ወይንም ስቃይ እንዲወገድ አያደርግም፣ ነገር ግን ለበሽታና ስቃይ አናባቢ ቁልፍ ያቀርባልናል፣ ማለትም የህልውናና የመኖር ጥልቅ ትርጉም ምን መሆኑ ለመረዳት የሚያግዝ ነው። ይክ ቁልፍ በዚያች የሕይወት ጥበብ በተሞላቸው በቅድስት ድንግል ማርያም አማካኝነት ወደ ኢየሱስ በበለጠ ቅርብ ለመሆን የሚያበቃ መንገድ ሆኖ ይለገሥልናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በሽተኛን የእግዚአብሔር ደግነት በሚያንጸባርቅ ፍቅር ቀርቦ መንከባከብና ማከም

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት የቃና ዘገሊላ ሠርግ ሲያብራሩ፣ ሠርጉ ያ በእግዚአብሔር አሳቢነት በጸላይ መንፈስ በተሸኙት ደቀ መዛሙርት እና በቅድስት ድንግል ማርያም የተከበበው ኢየሱስ ማእከል ያደረገ የቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ምስል በማለት ገልጠው። ማርያም ተጽናንታ የምታጽናና እናት ስለ ሌላው የምታስብ በምኅረት የተሞላው የእግዚአብሔር ደግነት የሚያንጸባርቅ እናታዊ ልቧ ለሁሉም ቅርብ ታደርጋለች። ህመምተኞች ወደ እርሷ ይቀርባሉ።

ስለ ህመምተኛ የሚደረገው ጸሎት፦ የልብ ጤናና ሰላም

የታመመውን ልጃቸው የሚንከባከቡ ወላጆች፣ የታመሙትን በእድሜ የገፉትን ወላጆቻቸውን የሚንከባከቡ ልጆች ሁሉም ለቅድስት ድንግል ማርያም እናትነት የሚማጠኑ ናቸው፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥት ህሙማንን በመፈወስ ተምሳሌቱን ገልጦልናን፣ በዚህ ብቻ ሳይታጠር የእግዚአብሔር ጸጋ የሆነው የላቀው እርሱም እርጋታ የልብ ሰላም የተካነውን ሕይወት ገልጦልናል።

ለሚሰቃየው ማገልገል ሰውን ኢየሱስን እንዲመስል ያደርጋል

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቃናው ዘገሊላ ሠርግ ዕድመተኛውን የሚገለግሉትን በማሰብ ያንን ኢየሱስ ወደ ወይን የለወጠው ውኃ በማመላለስ አገልግሎት የተጠመዱ በወንጌል ስማቸው የማይገለጠው ጠቅላል ባለ አነጋገር አገልጋዮች ተብለው የሚጠቀሱት አለ ምንም ማመንታት በየዋህነት የታዘዙ፣ የተጠየቁትን የፈጸሙ፣ አዎ እርሱ የሚለውን አድርጉ ለሚለው ጥሪ የታዘዙ በማርያም ምክር የታመኑ ናቸው። ለኢየሱስ ድንቅ ሥራ ተባባሪ ሆኖ መገኘት ያለው ክብር የመሰከሩ ናቸው፣ የሚሰጠው አገልግሎት ይኸንን መምሰል አለበት፣ ኢየሱስን በመምሰል ጎዳን እንድናድግ ያደርገናልና።

በማከሚያ ቤቶች የግኑኝነትና የሰላም ባህል ማነቃቃት

ቅዱስነታቸው ያወጁት የምኅረት ዓመት፣ በቅድስት መሬት ታስቦ የሚውለውን የሕመምተኛው ቀን እንዲሁም ባለፈው ግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ቅድስና የታወጀላቸው የቅድስት መሬት ዜጎች ቅድስት ማሪያ አልፎንሲና ዳኒል ጋታስና ቅድስት ማሪያ ዘኢየሱስ ስቁል ቡአርድይን በማሰብ እያንዳንዱ ሕክምና ቤት ወይንም የምንኖርበት ቤት የግኑኝነትና የሰላም ባህል የሚያነቃቃ መሆን አለበት፣ በሽተኛው ለብቻው ለህመሙ የማይተውበት የተሟላና በቂ የህክምና አገልግሎት የሚያገኝበት መፈቀሩ የሚያስተውልበት ሥፍራ ሆኖ መገኘት አለበት። ማርያም የምኅረት አይኖችዋ በሰው ልጅ በተለይ ደግሞ በህሙማን ላይ ታኑር በሚል ጸሎት ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.