2015-09-14 19:16:00

የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እሁድ ዕለት እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ከተሰበሰቡ ምእመናንና ነጋድያን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል ተመርኵዘው እንዲሁም ባሁኑ ጊዜ ዓለምን አስቸግሮ ያለው ሥራ አጥነት በቤተሰብ ላይ እያስከተለ ያለው ችግርና የስደተኞች ጉዳይ አስመልክተው “እኔነትንና ራስወዳድነት የሚያስቀድመው ዓለማዊ አስተሳሰብን አስወግደን ኢየሱስንና ወንጌሉን የተከተለን እንደሆነ ሁሉ እንደሚታደስና እውን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፣ እንዲሁም በዓለማችን ገኖ ያለውን ሥራ አጥነት ቤተሰብን በማስቀደመና ፍላጐታቸውን ለሟሟላት ሁነኛ እርምጃ በመውሰድ መፍትሔ ሊገኝለት ይቻላል” ሲሉ ካስተማሩ በኋላ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገው ስለመጀመርያዊ የደቡብ አፍሪቃ የብፅዕና አዋጅ ማለት ስለ ብፁዕ በነዲክት ዳስዋና ጓደኞቹ ለእምነታቸው ሲሉ የተቀበሉት መስዋዕትነት ለዘመናችን ምስክርነትና ብርታት መሆኑንም ገልጠዋል፣

ጌታ በወንጌሉ እንደሚያስተምረን ለድል መቀዳጀትና ለእብሪት የሚመራ የሕይወት ጉዞ ለጊዜው ደስ የሚያስኝ ቢመስልም ወዲያው የሚወድምና በቀላሉ ወደ ሓዘን የሚለወጥ ስለሆነ ይህንን ትተን በትሕትናና በእምነት ጠባቡን መንገድ የተከተልንና ለቤተሰብ ቅድምያ በመስጠት ለወንድሞቻችን ያሰብን እንደሆነ ምንም እንኳ ጉዞው ከባድ ቢሆነም ወደ እውነተኛው ነጻነት የሚወስደንን መንገድ ይህ ነው፣

ለዘመናችን ችግር የዳረገን አለማዊው አስተሳሰብ ሲሆን ከእኔነትና ከኃጢአት የሚመንጭ ስለሆነ ጌታ እንደሚለን መስቀላችን ተሸክመን እርሱን መከተል ብቻ ከዚህ ሊያድነን ይችላል፣ የገዛ ራሳችን ጥቅም ፍለጋንና ዓለማዊ አስተሳሰብን መካድ የግድ ነው፣ እንደጌታ ትእዛዝ ከሆነ ሁለመናችን ለእርሱና ለወንጌሉ መስጠት ያስፈልጋል፣ እርሱም ተቀብሎ አሳድሶና እውነተኛ ሕይወት አልብሶ መልሶ ይሰጠናል፣ እንዲህ ያደርግን እንደሆነ የተትረፈረፈ ሕይወት እናገኛለን፣ መንገዱን መከተል ደግሞ ትምህርቱን መከተል ነው፤ መምህራችን ኢየሱስ ጌታና ፈጣሪ ሳለ ትሕትና ለብሶ ለአገልግሎት መጣ፣ እርሱን ማወቅና መከተል ሕይወታችን መሆኑን ለማስገንዘብ በወንጌል መጀመርያ ሕዝብ ማን እንደሚሉት ቀጥሎም ሓዋርያትስ ማን እንደሚሉት ሲጠይቅ እምነታቸውን ሚዛን ላይ በማኖር ነበር፣ ይህ ጥያቄ ለእያንዳንዳችን ዛሬም ይቀርብልናል፣ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ ክርስቶስ ነህ ብለን እምነታችን የመመስከርና ሕይወታችን የመለወጥ ጊዜ አሁን ነው፣ ይህ ሲሆን ግን የእግዚብሔር ጸጋን የሚቃወም ጠላት እንዳለና ሁሌ እንደሚፈትነን መዘንጋት የለብንም፣ ያ ሓዋርያትን ወክሎ የጌታ ማንነትን በማወቅ አንተ የእግዚአብሔር ሕያው ልጅ ክርስቶስ ነህ ያለና ከአንተ ወደ ማን እንሄዳለን አንተ የሕይወት ቃል አለህ ብሎ እምነቱንና ጽናቱን የመሰከረ ጴጥሮስ ወዲያውኑ ጸላኤ ሠናይት ፈተና ሲያጋጥመው ኢየሱስን የመስቀልና የሞት ነገር አይድረስብህ ሲለው አንተ አለት ነህ በዚህም አለት ቤተክርስትያኔን እገነባለሁ ብሎ የወደሰው ሂድ ከኔ ራቅ አንተ ሰይጣን ሲለው ማየት ምኑን ያህል በፈተና የተከበብን መሆናችንን ያሳያል፣ ለዚህም ነው ሊከተለኝ የሚፈልግ ገዛ ራሱን ትቶ መስቀሉን ይዞ ይከተለኝ ያለው ሲሉ ካስተማሩ በኋላ ወደ ወጣቶች ዞር በማለትም እናንተ ወጣቶች ጌታ እንዲናገራችሁ ፍቀዱለት በሕይወት ከሁሉ የበለጠ የኢየሱስን ድምጽ ለመስማት ዝግጁ መሆን! ቀረብ ብሎ ሊያነጋግርህ መፈቀድ ስለሆነ እሰቡበት ጸሎት አዘውትሩ፣ ሲሉ አደራ ብለዋል፣

ስለ መጀመርያው የደቡብ አፍሪቃ ብፁዕ ሳሙኤል በነዲክት ዳስዋና ስለሚሰደዱ ክርስትያን ሲናገሩ ደግሞ ዛሬ በደቡብ አፍርቃ ብፅዕናው የታወጀው የዛሬ 25 ዓመት እ.አ.አ በ1990 ዓም በወንጌል በማመኑ በሞት ተቀጣ፣ በሕይወቱ በሰጠው ምስክርነትና ብርታት ለዓለማዊ ኑሮና አረመናዊ ኑሮን አልቀበልም በማለቱ ታላቅ ምስክርነት ሰጠ፣ ምስክርነቱም ከሌሎች ብዙ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ወጣቶችም ይሁኑ አዛውንቶች ሕጻናትም ሳይቀሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ ሲሉ እየተሰደዱና እየተገደሉ ካሉ የዘመናችን ሰማዕታት ይጨመራል፣ እነኚህ ሁሉ ሰማዕታትና ብፁዕ ሳሙኤልበነዲክት ዳስዋን ስለምስክርናቸው እናመስግናቸው እንዲያማልዱልን ደግሞ እንጠይቃቸው፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም ደግሞ እምነታችን ከዘመናችን ሓሳውያነ መሲሖች የውሸት አማልክቶቻቸው ንጽሕናዋን ትስጠን ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣

ይህ በእንዲህ ሳለ በሮማ በተለያዩ እስር ቤቶችና መታረምያ ቦታዎች ከሚገኙ እስረኞች የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ለመስማት አብረው ለመጸለይና ቡራኬ ለመቀበል በካፐላ ሲስተና በሚባለው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ክፍል ሆነው ተከታትለዋል፣ ይህ የሆነበት ዋናው ምክንያት እፊታችን ወርሓ ታሕሳስ ለሚጀምረው የምሕረት ኢየቤል እስረኞች የሚሳተፉበት መንገድ ይፈለግ ብለው ቅዱስነታቸው በጠየቁት መሠረት ሲሆን ይህ ዕድለኛ የሆነ ቡድን ትናንትና በቫቲካን አትክልት ቦታዎችና ሙዘዩም ጉብኝት አድርገው ልክ እኩለ ቀን ደግሞ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በመገኘት ከቅዱስነታቸው ጋር አብረው በመጸልይና ትምህርታቸውን በማዳመጥና ሓዋርያዊ ቡራኬን በመቀበል ተሳትፈዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.