2015-09-14 15:48:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሐኪሞች ሰውን እንጂ ተዛማጅ ባህል እንዳያገለግሉ አደራ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሰሜን ኢጣሊያ በምትገኘው የቨርቸሊ ከተማ ዓመታዊ ጉባኤው ወደ ከፈተው የመላ ኢጣሊያ ካቶሊካውያን ሐኪሞች ማኅበር፦ ተዛማጅ ባህል ክርስትናው አመለካከት በሚያቀርበው እርሱም ሥነ ምግባር መንፈሳዊነትና በእውነት የሚያበራው የእውነት ብርሃን በሆነው አድማስ አማካኝነት በመቃወም ለወቅታዊው ባህል አቢይ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ አደራ የበሚል ቅዉም ሃሳብ ማእከል ያደረገ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትር ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት የቴልግራም መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እነዚህ የኢጣሊያ የካቶሊክ ሐኪሞች ማኅበር ዘወትር ዘላቂነት ያለው ሰብአዊና ክርስቲያናዊ እሴት በማስቀደምና እነዚያ እሴቶች ዋቢ ያደረገ ለሥነ ሕክምና ምርምርና ለሕክምና አገልግሎት እድገት አቢይ አስተዋጽዖ በመስተጠት ተግተው፣ የሕክምና አገልግሎት ለሰው ልጅ ሙሉ እድገት የሚል መሆኑ በቃልና በተግባር እንዲመሰክሩ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት የቴልግራም መልእክት አደራ በማለት ማሳሰባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው የኢጣሊያ የካቶሊክ ሐኪሞች ማኅበር ዓመታዊ ዓውደ ጉባኤ የቨርቸሊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ማርኮ አርኖልፎ፣ ብፁዕ ካርዲናል ዲዮኒጂ ተታማንዚ ብፁዕ ካርዲናል ኤድዋርዶ መኒከሊ ንግግር እንደሚያስደምጡ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ይኽ የሚካሄደው ዓወደ ጉባኤ የሚከተለው የሕይወት ተአምር በተሰኘው መርሕ ቃል ርእስ ሥር  የሥነ ቅብ ትርኢት እንደሚቀርብ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.