2015-09-07 16:12:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ወደ ተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ለሁሉም ቅርብ ለመሆን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከ መስከረ 22 ቀን እስከ መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መግንሥታት የሚያካሂዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ትርጉም በተባበሩት መንግሥታት ኤይቢሲ በተሰየመው የቴለቪዥን ጣቢያ አማካኝነት ባስተላለፉት የድምጸ ርእይ መልእክት አማካኝነት ሲገልጡ ለሁሉም ቅርብ ለመሆንና የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ቅርበት ቀርበው ለመስከር የሚል፣ በተለይ ደግሞ በፊላደልፊያ ሊካሄድ ተወስኖ ባለው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ለመሳተፍ ያለመ ነው ብለዋል።

የቅርበት አስፈላጊነት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወደ ተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሐዋርያዊ ዑደት ለማካሄድ በመዘጋጀት ላይ ናቸው፣ ቅዱስነታቸው ለተናቁት ለተጠሙት ለተራቡት ለስደተኞች ቅርብ መሆናቸውና ሁሉም እያንዳንዱ ይኸንን ቅርበት እንዲኖር የተጠራ መሆኑና በተለይ ደግሞ መንግሥታት ለእነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል ማእከል ያደረገ ሰብአዊነት የተካነ ፖለቲካ እንዲያረጋግጡ በመደጋገም የሚያቀርቡት ጥሪ ካለ መታከት ዳግም ለማስተጋባት ነው።

ባስተላለፉት የድምጸ ራእይ መልእክት አማካኝነትም እኔ ለሁሉም አለ ምንም ልዩነት በአቢያተ ክርስትያን ለሁሉም ሰው ልጅና መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰውች አገልግሎት የተጠራሁኝ ነኝ። ይኽ ደግሞ ቅርበት ነው፣ ለሕዝብ ቅርብ አለ መሆን አይቻለኝም፣ በጉዞአችሁና በዕለታዊ ሕይወታችሁ ልሸኛችሁ በጌታ በእምነታችሁ ላጸናችሁ በመካከላችህ እንድገኝ የጌታ ፈቃድ ይሁን። ለታሪካችሁና ለጉዞአችሁ ቅርብ ለመሆን በመካከላችሁ ለመገኘት በመዘጋጀት ላይ ነኝ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ለብቻ የአለ መሆንና ጽናት

አንድ ወጣት በቺካጐ በኢየሱሳውያን ማኅበር ሥር በሚተዳደረው ለተናቁትና ለተረሱት በማኅበረሰብ ጠርዝ የሚኖሩት የሚያንጽ ትምህርት ቤት ተማሪ ወጣት ቫለርይ ሀረራ ተነጥሎ መኖር በበሽታ መጠቃት የመሳሰሉት ችግሮች ሁሉ ከትምህርት ቤት በሚያገኘው ከእምነት ከሙዚቃ በሚያገኘው ድጋፍ ተጽናንቶ በመኖር ይኸው የሥነ መድሃኒት ቅመማ ተማሪ ለመሆን እየተዘጋጀ መሆኑ ገዛ እራሱ ለቅዱስነታቸው በማስተዋወቅ፣ ከወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል የሚጠብቁት ምን ይሆን በማለት ላቀረበላቸው ጥያቄ ቅዱስነታቸው ሲመልሱ፦ በቅድሚያ በምድራዊ ጉዞአቸው ለብቻቸው አለ መጓዝ ከተገባ ወዳጅ ጋር መጋዝን እንዲያውቁ፣ ከኢየሱስ ከማርያም ጋር መጓዝ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በጽናት መጓዝ፣ አንድ ወጣት አለ ጽናት ማየቱ እንዴት ያሳዝናል፣ የተከዘ ወጣት ነው፣ የተሰቃየና ደስታ አልቦ መልክ ያለው ወጣት ነው የሚሆነው፣ ጽናት ደስታ ይሰጣል ተስፋን ይሰጣል ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጸጋ ነውና፣ በሕይወት ጉዞ እርግጥ ነው ውጣ ውረድ አለ፣ ይኖራልም፣ ነገር ግን አትፍሩ ብልሆች ጥንቁቆች ሁኑ፣ ምክንያቱም ፍርሃትን ለማሸነፍ በቂ ኃይል አላችሁና፣ እትደንግጡ ባላችሁበት አትራመዱ ወደፊት በሉ።

ግንባርን ቀጥ አድርጎ መጓዝ

አንዲት የሁለት ልጆች እናት ላቀረበችላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ የሁለት ልጆች እናት ነሽ ካለብሽ ችግር አንጻር ሁለቱን ልጆች አለ መገላገል በመረጥሽ ነበር ቃላሉ መንገድም እርሱ ነበር፣ ጽንስ ማስወርድ በቀለለሽ ነበር። ሆኖም ግን ለሕይወት እሺ ያልሽ የሕይወት ክብር የተረዳሽ ነሽ ጌታ ሕይወት ነውና መልስ አይነሳሽም። ጌታ ይባርክሽ ብለው እንዳጽናኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ሁላችን የሁሉላችን ኃላፊነት አለብን፣

አንድ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚኖር ስደተኛ ሪካርዶ ከስደት ሌላ ለተለያየ ችግር አማራጭ መፍትሔው ምድር ነው በማለት ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፦ በዓለም የሚታየው የተለያየ መልክ ያለው ኢፍትሃዊነት ሳይ ከሁሉም እጅግ አቢይና ወደር የማይገኝለት ግብረ ኢፍትሃዊነት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል መሆኑ ያስታውሰኛል። እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሸከመው መስቀል ነው። የኢየሱስ መስቀል የጎዳና ተዳዳሪ፣ የመስቀል ጽሞና ቋንቋ በተግባር የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍል ይህ የመስቀል ጽሞና በዓለም ለሚታየው ዘርፈ ብዙ ስቃይ ልሳን ነው፣ በሰው ልጅ ላይ የሚከሰተው ግብረ ብዝበዛ መራመድ ማለት አይደለም፣ የሰው ልጅ ለማኅበራዊ ወዳጅነት የተፈጠረ ነው። ስለዚህ ሁሉም የሁሉም ኃላፊነት አለበት፣ ሁሉም በጋራ እንዲጓዝ ሁሉም የሁሉም ደጋፊ ነው። በመደጋገፍ ለመኖር የተጠራን ነን። ማኅበራዊ ወዳጅነት አንዱ እግዚአብሔር ለመፍጠራችን ምክንያት ነው።

ከሞት ማምለጥ

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ያስተላለፉት የድምጸ ራእይ መልእክት ሲያጠቃልሉ፦ በሁሉ የሰው ልጅ ስቃይ ሰቆቃና እንባ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ የሚገለጥ የእግዚአብሔር ጽሞና አለ። መጠጊያችን እርሱ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.