2015-09-04 16:21:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ትህትናና አግርሞት ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት ልብን የሚከፍቱ ናቸው


ቅዱስ አባትችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መስከረም 3 ቀን የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ጎርጎሪዮስ አቢይ የምታከብርበት ዕለት መሆኑ በማስታወስ፣ የዕለቱ ቅዱስ ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች ከጻፈው መልእክት ምዕ. 1 ከቍ. 9-14 እዲሁም የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 5 ከቍ. 1-11 የተነበበውን መሠረት በማድረግ፦

ከኢየሱስ ጋር የሚያገናኙ ሁለት መንገዶች

ጴጥሮስ … አንተ ካልህ ግን እነሆ መረቡን እንጥላለን የጴጥሮስ እምነት፣ መረቡ እስኪቀደድ ድረስ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ። ይኽ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸመው ተአመር። ሌሊቱን ሁሉ አንድም ዓሣ ሳያጠምዱ ደክመው እያሉ በኢየሱስ በዚህ ተስፋ በሚሰጠው ተስፋ ሳይቆርጡ በእርሱ ታምነው እርሱ ያለውን አደረጉ። በእርሱ መታመን እርሱ ያለውን ማድረግ።

ኢየሱስ አብሮ ከሕዝብ ጋር ሕዝቡ በሚጓዝበት መንገድ ይገኛል። ሆኖም ለብቻው ገለል ብሎ የሚጸልይበት ጊዜም ነበረው። በሚጸልይበት ሥፍራ ታጥሮ ሳይቀር ከጸለየበት ሥፍራ ወርዶ ሕዝብ ጋር ለመገናኘት ይወጣል። አግርሞትና ትህትና ከኢየሱስ ጋር የሚያገናኙ በሮች ናቸው።

ኢየሱስ  የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ አጋንንትም ያውቃሉ

የሕግ ሊቃውንት ፈሪሳውያን የአግርሞትና የትህትና መንፈስ ስላልነበራቸው ልባቸው በትዕቢት የተዘጋ ነበር። በገዛ እራሳቸው ብቃት የሚተማመኑ፣ እኔ ለገዛ እራሴ እበቃለሁኝ ባዮች፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑ ያውቃል ነገር ግን ኃጢአተኛ መሆኑ ይታመናል።

እጋንንት ስለ የኢየሱስ እውነት በሚገባ ያውቃሉ፣ የሚሠራው የሚፈጽመው ድንቅ ሥራና ተአምር ሁሉ ያውቃሉ፣ ነገር ግን ስለ ኢየሱስ አይመሰክሩም። በገዛ እራሳቸው ብቃት የተዘጉ ትዕቢተኞች ናቸውና።

ትዕቢተኛነት ኃጢአተኛ መሆንህ ላለ ማወቅ መንገድ በመሆኑ ከኢየሱስ ክርስቶስ ያርቃል።

ኢየሱስ ጌታ ነው ብሎ ለመናገር እጅግ ቀላል ነው፣ ሆኖም ኃጢአተኛ መሆንህ ለማወቅ እጅግ ያዳግታል። የዚያ ቀራጩ ትህትና ኃጢእተኛ ስለ መሆኑ የሚያውቅና ትዕቢተኛ ፈሪሳዊው እናስታውስ። ኃጢአተኛ ነኝ ብሎ መናገርና ኃጢአተኛ መሆህን ማወቅ ክኢየሱስ ጋር ያገናኛል። ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እውነተኛ ግኑኝነት እንዲኖር ያደርጋል። በቁምስናዎቻችን በማኅበረሰባችን በውፉያን ሕይወት ሰዎች መካከልም ኢየሱስ ጌታ ነው የሚሉ ብዙ ናቸው፣ ለይስሙላ ሳይሆን መለወጥ በመሻት በቅንነትና በትህትና ኃጢአተኛ ነኝ የሚሉ ግን እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ስለ ሌሎች መናገር በጣም ቀላል ነው። ሁላችን ስለ ሌሎች በመናገር ልማድ ሊቃውንቶች ነን። እንተ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እኔ ኃጢእተኛ ነኝ የሚል የእምነት ኑዛዜ መኖር ነው የሚያስፈልገው።

ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት መፍቀድና በእርሱ ለመገኘት ፈቃደኛ መሆን

ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ያሳደረብን አድናቆት ሳናጠፋ ኢየሱስን እንክዳለን፣ ጴጥሮስን እናስታውስ። ስለዚህ ትህትና ያስፈልጋል፣ ትሁት ብቻ ነው ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት የሚፈቅድ፣ ከኢየሱስ ጋር ሲገናኝ ያነባል የሚያነባውም ኃጢአተኛ መሆኑን ስለ ሚያውቅ ነው። ስለዚህ ወደ ንስኃ ያመራል ብለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስደመጡት ስብከት ጌታ ከእርሱ ጋር ለመገናኘትና በእርሱ ለመገኘት እንችል ዘንድ ጸጋውን ይስጠን ከእርሱ ጋር መገናኘት አስደናቂ መሆኑ እናስተውል ዘንድ ይደግፈን፣ አንተ እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነህ፣ አምናለሁ ይኽንን እምነት እኖራለሁ ቢሆንም ኃጢአተኛ ነኝ የሚል የእምነት ኑዛዜ እንኖር ዘንድ ያብቃን በሚል ጸሎት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.