2015-08-31 14:58:00

የብፅዕና አዋጅ


ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. ነሐሴ 29 ቀን 1915 ዓ.ም. የኦታማን ግዛት በፈጸመው የስደትና የቅትለት ተግባር ለሞት የተዳረጉት የእምነት ሰማዕት የሶሪያ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍላቫይን ሚሸል መልኪ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን ወክለው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ብፅዕና እንደታወጀላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጀ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የብፁዕ አቡነ ማልኪ የብፅዕና አዋጅ በአሁኑ ወቅት ለሚዋረዱትና ለሚስደዱት ማኅበረ ክርስቲያን የተስፋና የማበረታታቻ መልእክት ነው እንዳሉ ብፁዕ ካርዲናል አማቶ ለብፅዕና አዋጅ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት እንዳሰመሩበት ከብፅዕናው አዋጅ ፍጻሜ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የሶሪያ ሥርአት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በበይሩት ኤጳርቅና የአንጽዮኪያ ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ኢግናዝዮ ዩሰፍ ሦስተኛ ዩናን ገልጠው በዚህ የመካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረ ክርስቲያን በተለይ ደግሞ በኢራቅና በሶሪያ ለስደት ለስቃይ በተጋለጠበት የሰብአዊ መብትና ክብር በሚጣስበት በሚታገትበት በአሁኑ ወቅት የታወጀው ብፅዕና እግዚአብሔር ሕዝቡን ለብቻው እንደማይተው የተስፋ ምልክት የክልሉ ማኅበረ ክርስቲያን በእምነትና በተስፋ ጸንቶ በክልሉ እንዲኖር የሚያበረታታ ጸጋ ነው ብለዋል።

እየተስፋፋ ያለው እስላማዊው አገር ለመግታት የምዕራቡ ዓለም አሁኑም ቢሆን አንድ ወጥ የሆነ የጋራ ምላሽ አልሰጠም፣ ስለዚህ ሁኔታው እጅግ እየከፋ በመሄድ ላይ ነው። ወደ ኤውሮጳ የሚጎርፈው የስደተኛው ብዛታ በአሁኑ ወቅት በኤውሮጳ አገሮች ብዙ እያናገረ ይገኛል። መስተንግዶ መስጠት መልካም ነው ሆኖም ለስደት የሚዳርጉት እክሎች መሠረታዊ መፍትሔ እስካላገኙ ድረስ የስደተኛው ጸአት በሚያስደነግጥ ሁነት እንደሚቀጥል አያጠራጥርም፣ ለተከበረው የብፅዕናው አዋጅ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን አመስግነው ይኽ ደግሞ ቅዱስነታቸው ለመካከለኛው ምስራቅ ሕዝብና ማኅበረ ክርስቲያን ስቃይ ስደትና መከራ ቅርብ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ነው። ብፁዕ አቡነ መልኪ የዛሬ አንድ መቶ ዓመት በፊት የእምነት ሰማዕትነት በተቀበሉበት ነሐሴ 29 ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብፁዕና ስታውጅላቸው በእውነቱ ተስፋ እምነትና ፍቅር የሚያድስ ማኅበረ ክርስቲያን የሚያጋጥመው ስደትና መከራ በጌታ ኃይል በመወጣት ክርስትናው በአገሩና በክልሉ እንዲኖር የሚያበረታታ ነው። መካከለኛው ምሥራቅ መለኰታዊና ሰብአዊ ድጋፍ የሚያሻው ክልል ነው። የምዕራቡ ዓለም ለስደትና ለስቃይ የሚዳረገው ሕዝብ ቅርብ እንዲሆን ጥሪ በማስተላለፍ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.