2015-08-26 16:32:00

የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ


የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት የብሔራዊ ፍትሕና የሰብአዊ እድገት ጉዳይ የሚያነቃቃው ድርገት ሊቀ መንበር የሚያሚ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቶማስ ጀራርድ ወንስኪይ በአገራቸው እ.ኤ.አ. መስከረም 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ታስቦ የሚውለው ብሔራዊ የሥራ ቀን ምክንያት ካቶሊካዊ እምነታችን ሥራ ክቡር በመሆኑ የተገባ የደሞዝ ክፍያና የቤተሰብ ሕንጸትና መረጋጋት ለማነቃቃት የሚደግፍ ክቡር የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያግዝ ማኅበራዊና ኤኮኖሚያዊ ሥልትና መዋቅር እንዲታነጽ በሚደረገው ጥረት ለመተባበር ጥሪ ያቀርብልናል የሚል ቅሙው ሕሳብ ላይ ያነጣጠረ መልእክት ማስተላለፋቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ቤተሰብ የሥራ ማእከል

ብፁዕ አቡነ ጀራርድ ወንስኪይ ያስተላለፉት መልእክት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት መሠረት ያደረገም ሲሆን፣ ቤተሰብ የማኅበረሰብ ብሎም የኅብረተሰብ ማእከል መሆኑ በማብራራት በአሁኑ ወቅት ሥራ በእኩል የማይዳረስ የሥራ አጥነት ችግር የሚያዛምት ሥራው ከተገኘም የተገባ የደሞዝ ክፍያ የማያሰጥ በመሆኑ ይኽ ጉዳይ ያንን የኅብረተሰብ ማእከል የሆነው ቤተሰብ ለተለያየ ችግር እየዳረገው ነው እንዳሉ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ የሥራ አጥነት ችግር ትዳር ለመመሥረት እክል መሆኑና ሥራ አጥነት እንዲቃለል የማይደግፍ የሥራ ዕድል የማይፈጥር ኤኮኖሚ ዓለማችን እየተላመደው ነው። ይኽ አይነቱ ኤኮኖሚ ተቀባይነት እንዳለው የሚያደርግ ልማድ አደራ እንዲወገድ ማሳሰባቸው አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሥራና በሰው ልጅ መካከል ያለው ግኑኝነት ሲገለጡ፣ የሰው ልጅ ለሥራ መጠራቱ የዘፍጥረት እውነት ነው። የሥነ ምኅዳር እንክብካቤና የሥነ ምኅዳር ምሉእነት መሠረት ያደረገ የኅብረተሰብና የሰው ልጅ ችግር መፍትሔ እንዲያገኝ የሚደግፍ ሥራ እንዲጸና ያቀረቡት ጥሪ ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ጠቅሰው የሰው ልጅ ክብር የሚጻረረው በሥራ ዓለም የሚታየው ግብረ ብዝበዛ፣ የሰው ልጅ ለተለያየ ጸያፍ ተግባር መገልገያ ለማድረግ የወንጀል ቡድኖች የሚፈጽሙት ከቦታ ቦታ የማዘዋወሩ ድርጊት የተገባ የሥራ ዕድል በምፍጠር መንግሥታት ሁሉ እንዲዋጉት ጥሪ ማቅረባቸው ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።

የታደሰ ኅብረተሰብ የሚጸናው በመደጋግፍ ሲመሠረት ብቻ ነው

ለታደስ ኅብረተሰብ ጎዳና ይላሉ ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት፦ በመተባበርና በእምነት ላይ መጽናት ነው። ይኽ ደግሞ ለሌሎች ስቃይና መከራ ግድ  የለሽ የሚያደርግና በገዛ እራስ ለመዝጋት የሚዳርግ ግለኝነት ስግብግብነት ቁስ አካላዊነት እንቃወም ዘንድ አደራ እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.