2015-08-21 15:17:00

ደቡብ አፍሪቃ፦ ቤተ ክርስቲያን ለማዕድን ሃብት አውጭ ሠራተኞች ሰብአዊ ክብር ጥበቃ


የደቡብ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትህና ሰላም ድርገት በአገሪቱ የሚግኙት የተለያዩ አበይት የማዕድን ሃብት አውጭ ድርጅቶች የተፈጥሮ የማዕድን ሃብት ዋጋ ዝቅ በማለት ምክንያት የተያያዙት የሠራተኛ ቅነሳ ውሳኔ በማስደገፍ ባወጣው መግለጫ፦ ለአንድ አዲስ ማኅበራዊ ስምምነት እድል ሰጥቶ፣ አበይት ድርጅቶች በሚደርስባቸው የኤኮኖሚ ግሽበት ምክንያት እንዳይዘጉ በሚል ውሳኔ የደረሰባቸው ኪሳራ በሕዝብ የግብር ክፍያ ማዳን የተለመደ መጥቷል፣ ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች በገንዘብ ሃብት ሲደልቡና የኤኮኖሚው ሂደታቸው የተዋጣለት ሆኖ የሚያካብቱት የገንዘብ ሃብት ለገዛ እራሳቸው ጥቅም ብቻ የሚያውሉ ናቸው። ኪሳራው ለሁላችን ትርፉ ለኔ የሚለው የተለያዩ አበይት ኢንዳስትሪዎችና የኤኮኖሚ አውታሮች የሚከተሉት ሥነ ሃሳብ በድኻውና በሃብታሙ የኅብረተሰብ ክፍል መካከል ያለው አቢይ የኑሮ ደረጃ ልዩነት ከፍ እንዲል የሚያደርግና ድኻው ውደ ከፋው ድኽነት የሚከት መሆኑ በማብራራት፣ ለዚህ ሁሉ ችግር መፍትሔ አንድ አዲስ ኅብረተሰብአዊ ስምምነት ወሳኝ ነው እንዳለ ቺሳ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በማንኛው ዓይነት የኤኮኖሚ ቀውስ ሠራተኞችን የሚዋስ አዲስ ኅብረተሰብአዊ ስምምነት

የደቡብ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት የፍትህና ሰላም ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አበል ጋቡዛ የሰጡት መግለጫ የአገሪቱ የማዕድን ሃብት ሚኒ. ማእከል በማድረግ ሠራተኞች ከመቀነስ ይልቅ ሌላ አንድ አዲስ መፍትሄ ለማፈላለግ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው የገለጠው ቺሳ የዜና አገልግሎት አክሎ፣ የማዕድን አውጭ ድርጅቶች አዲስ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያበቃቸው የኤንዳስትሪ ፖለቲካ ኅዳሴ እንደሚያፍፈልጋቸውና ገልጠው ከዚሁ ጋር በማያያዝም የእነዚህ ድርጅቶች በዓለም ኤኮኖሚ የተወዳዳሪነት ብቃታቸውንም ለማሳየል የሚቻልበትን መንገድ ለማፈላለግ ከድርጅቶቹና ከሠራተኛው ማኅበራት ጋር እየመከሩ መሆናቸው ያመለክታል።

የጋራው ጥቅም ከግል ትርፍ የማካበት ምርጫ በፊት ማስቀደም

ብፁዕ አቡነ ጋቡዛ ባስተላለፉት መልእክት፣ ሰው ከትፍር በፊት ማስቀደም ያለው አስፍፈላጊነት አብራርተው፣ የተፈጥሮ ሃብት በማእድን አውጭ ድርጅቶች ሥር የሚተዳደር ቢሆንም ቅሉ ለጋራ ጥቅም ማእከል የሚያደርግ ኤክኖሚ ማስቀደም እንጂ የግል ጥቅም ከጋራው ጥቅም በፊት በማስቀደም ትርፍ ለኔ የኤክኖሚ ግሽበት ለሁሉም ከሚለው የኤኮኖሚ ፍልስፍና መላቀቅ ያፍፈልጋል እንዳሉ ቺሳ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.