2015-08-19 15:30:00

ብፁዕ አቡነ ጋላንቲኖ


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ኑንዚዮ ጋላንቲኖ በኢጣሊያ ፒየቨ ተሲኖ፣ በትረንቶ የአሊቸ ደ ጋስፐሪ ማኅበር ባዘጋጀው ዓውደ ጉባኤ ተገኝተው ንግግር ያስደምጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ ብፁዕነታቸው በአሁኑ ወቅት ስለ ስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ በመንግሥትና በጠቅላላ የኢጣሊያ የፖለቲካ አካላት ላይ የሰነዘሩት ወቀሳ ባስከተለው አለ መግባባት ምክንያት እንዲሁም ከተለያዩ የፖሊቲካ አካላት እየተሰነዘረባቸ ያለው ወቀሳ ግምት በመስጠት እንደማይሳተፉ ለማኅበሩ ባስተላለፉት መልእክት ማሳወቃቸው ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።

ብፁዕ አቡነ ጋላንቲኖ ለማኅበሩ ባስተላለፉት መልእክት በቅድሚያ በተዘጋጀው ዓውደ ጉባኤ ተገኝተው ንግግር እንዲያስደምጡት የቀረበላቸው ጥሪ በሙሉ ልብ በእሽታ ተቀብለዉት እንደነበር በማስታወስ፣ ደ ጋስፐሪ ታላቅ የኢጣሊያ የፖለቲካ ሰው እንደነበሩና በአሁኑ ወቅት በኢጣሊያ ተከስቶ ያለው ፖለቲካዊ ማኅበራዊና ሰብአዊ ቀውስ የደ ጋስፐሪ ፖለቲካዊ ሰብአዊ ምሉእነት መሰረት ማጤኑ የታደሰ ፖለቲካ ያለው አስፈላጊነት ያስገነዘባል፣  በፖለቲካው ሂደት የፖለቲካው አካላት በቃልና በሕይወት አብነት ሆኖው እንዲገኙ የሚያሳስብ ጭምር እንደሚሆን ባስተላለፉት መልእክት በጥልቀት በማብራራት፣  ያስደምጡታል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው ንግግር በቀጥታ በሳቸው አማካኝነት ባለ መደመጡንም ይቅርታ መጠየቃቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በአሁኑ ወቅት በፖለቲካውና በኢጣሊያው ኅብረተሰብ መካከል ተቀስቅሶ ያለው ክርክር እንዳይባባስ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ላለ መሳተፍ እንደመረጡ ቢገልጡም በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተገኝተው የሚሰጡት ቃል የሚያስደምጡት ንግግር የሚሰጡት መግለጫ ከወንጌላዊ መንፈስ የመነጨ መሆኑ አብራርተው፣ የሰጡት ኃይለኛ መግለጫዎችና በሰነዘሩጥ ጠንካራ አስተያየት የአንዳንድ ሰዎች ስሜት የነካ ከሆነ ይቅርታን እጠይቃለሁ ብለው፣ የሚሰነዝሩት አስተያየትና የሚሰጡት መግለጫ ሁሉ በወንጌል ላይ የጸና ከወንጌላዊ መንፈስ የመነጨ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።    








All the contents on this site are copyrighted ©.