2015-08-19 15:19:00

ብፁዕ አቡነ ኵይሮጋ፦ በኮሎምቢያ ሰላም ለማረጋገጥ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አስተዋጽኦ


በኮሎምቢያ የቱንኻ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ልዊስ ካስትሮ ኵይሮጋ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ, ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 19 ቀን እስከ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ.ም. በኩባ በሚያካሂዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት በሃቫና በኮሎምቢያ የትጥቅ ትግል ከሚያካሂደው ፋርክ የተሰየመው አብዮታዊ ግንባር ተጠሪዎች ጋር በመገናኘት በኮሎምቢያ ሰላም እንዲረጋገጥ ያለመ ውይይት ያካሂዳሉ ተብሎ የሚገለጠው ዜና አስደግፈው በርግጥ በኮሎምቢያ ሰላም እንዲረጋገጥ በአገሪቱ መንግሥትና በፋርክ አብዮታዊ ግንባርት ተጠሪዎች መካከል በኩባ እየተካሄደ ስላለው የጋራ ውይይት ጉዳይ በተመለከተ የተለያዩ ማስታወቂያዎች ይደርሳቸዋል፣ ሆኖም ከሰላም ውይይት ተደራዳሪ አካላት ጋር ቀጥተኛ መግለጫ ቢደርሳቸው የበለጠ ነው፣ ስለዚህ ግኑኝነቱ ሊከወን የሚቻል ቢሆንም ቅሉ የግኑኝነቱ እቅድ በኵባ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚመለከት ወይንም የሚወሰን ሳይሆን ጉዳይ የኵባ መንግሥት የሚመለከት ነው እንዳሉ አንሳ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የኮሎምቢያ የሰላም ውይይት በሃቫና

በኮሎምቢያ ሰላም እንዲረጋገጥ በመንግሥትና በፋርክ ታጣቂ ኃይል መሪዎች መካከል የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኮሎምቢያ ሰላም እውን እንዲሆን ዘወትር የሚያቀርቡት ጥሪ ነው። ይኽ የቅዱስነታቸው የሰላም ምኞት በተመለከተ ርእስ ዙሪያ ይላሉ ብፁዕ አቡነ ካስትሮ ኵይሮጋ ሰላም እንዲረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ቅዱስነታቸው በቀጥታ ወይንም በአንድ የሳቸው ሐዋርያዊ ልኡክ አማካኝነት ሊያከናውኑት ይችላሉ እንዳሉ የገለጠው አንሳ የዜና አገልግሎት አያይዞ፦ በመካሄድ ላይ ያለው የሰላም ውይይት አወንታዊ ውጤት እንደሚኖረው ቅድስ አባታች ተስፈኛ ናቸው፣ ሆኖም በቅድስት መንበርና በፋርክ መካከል ግኑኝነት እንዲካሄድ በኮሎምቢያ የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጥረት የሚያስፈልግ አይመስለኝም እንዳሉ አስታወቀ።

ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር ለመገናኘት የፋርክ ፍላጎት

አጂ የተሰየመው የዜና አገልግሎት ያሰራጨው ዜና የጠቀሰው ሲስሞግራፎ የዜና አገልግሎት የፋርክ ታጣቂው አብዮታዊ ግንባር ተጠሪ ኢቫን ማርከዝ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ለመገናኘት ፋርክ ጥያቄ ማቅረቡና አወንታዊ ምላሽ እንዳገኘ ሲያመለክቱ፣ አክሎ ፋርክ በመካሄድ ላይ ያለው የሰላም ድርድር ውጤታማ ይሆን ዘንድ አንደሚመኝና ይኽ ደግሞ በካቶሊክዊት ቤተ ክርስቲያን ጥረት ሊረጋገጥ እንደሚችል ነው እንዳሉ አስታወቀ።

የፋርክ ተጠሪዎች ከኮሎምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር በመገናኘት በመካሄድ ላይ ያለው የሰላም ውይይት ሂደቱና ምን ተመስሎው በማብራራት እውነት ፍትህና እንዲሁም ጠበኝነት ማስወገድ በተሰኙት ርእሶች ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸው ኢቫን ማርኵዝ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩ የገለጠው ሲስሞግራፎ የዜና አገልግሎት በማያያዝ ዘላቂ የቶክስ አቁም ስምምነት ርእስ ዙሪያ የተከናወነው ውይይት በተለይ ደግሞ በኮሎምቢያ የተለያዩ የቀኝ ፖለቲካ ተከታይ ቅትረኛ ታጣቂ ኃይሎች እንዳሉም ጠቅሰው ለተሟላ ሰላም መረጋገጥ የእነዚህ የተለያዩ ቅጥረኞች ትጥቅ መፍታት ወሳኝ ነው እንዳሉ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.