2015-08-19 15:23:00

በእስያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በስነ ምኅዳር ዘርፍ


በምያንማር የያንጎን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ቻርለስ ማኡንግ ቦ በባንግኮክ የመላ እስያ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት የተፍጥሮ የአይር ንብረት መዛባት ርእስ ዙሪያ ያዘጋጀው ዓውደ ጉባኤ መክፈቻ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፦ በዓለም ተከስቶ ያለው የተፈጥሮ አየር መዛባትና ብከላ ለመጋፈጥ ብሎም የተፈጥሮን ያካባቢ ጤንነት ለመንከባከብ ተጨባጭ መፍትሔ አስፈላጊ ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ገለጠ።

ሰብአዊ ቤተሰብና ተፈጥሮን ላይ የደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢነት

ሰብአዊ ቤተሰብና ያ የእግዚአብሔር ጸጋ የሆነው ተፈጥሮ ለአደጋ የሚያጋልጥ እየተከሰተ ያለው ጥቃት እንዲወገድ ሁሉም በእስያ የሚግኙት ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስቲያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት መርህ በማድረግ አቅማቸው ኃይላቸውና እውቀታቸው በማስተባበር አቢይ ሚና እንዲጫወቱ ብፁዕነታቸው ጥሪ እንዳቀረቡ ኤሺያን ኔው የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

በተፈጥሮ ያካባቢ አየር ብከላ እጅግ ተጠቂው ድኻው ኅብረተሰብ ነው

ብፁዕ ካርዲናል ቦ በምያንማር እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረው 150 ሺሕ ለሞት ከ 800 ሺሕ በላይ የሚገመቱት ደግሞ አለ ቤትና ንብረት ያስቀረው ናርጂስ የተሰየመው ዝናብ አዘል ኃይለኛው አውሎ ነፋስ እንዲሁም በቅርቡ የተከሰቱት የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋዎች ጭምር  አስታውሰው እጅግ ተጠቂውና የሚጠቃው ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ነው። ድኻው ኅብረተሰብ የመሬት ሙቀት መጨመር ስለ ሚባለው ጉዳይ ምንም አይነት ግንዛቤም አልነበረው፣ ሆኖም ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል በመሬት የሙቀት መጠን መጨመርና በተፈጥሮ የአየር ብከላ ጉዳይ ተጠያቂ ባይሆንም ቅሉ እጅግ ተጎጂው መሆኑ ገልጠው፣ በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ወቅታዊው ታሪክ መስቀለኛ መሆኑና በተፈጥሮና በሰብአዊ ቤተሰብ ላይ የሚጣለው ጥቃት በሰው ልጅ ጤንነት ላይ ብቻ ሳይሆን የምንኖርበት ዓለም ጤና መጓደል አደጋ የሚያጋልጥ ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ገለጠ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም በታይላንድ በካሪታስ ለሚጠራው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ፊሊፕ ባንቾንግ ቻይያራ ለዓውደ ጉባኤ ባስደመጡት ንግግር፦ የተፈጥሮ አየር ብከላና የተፈጥሮ ጤንነት መጓደል እዲቀረፈ ሁሉም ከግለ እስከ ማኅበረሰብ ኅብረተሰብ በተለይ ደግሞ በመንግሥታት ደረጃ አቢይ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ እንዳቀረቡ የገለጠው ኤሺያን ነውስ የዜና አገልግሎት በማያያዝ፣ የተፈጥሮ ጤንነት መንከባከብ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ ሲያብራሩ የመላ እስያ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ አልውይን ደሲልቫ በበኵላቸውም በተፈጥሮ ያካባቢ አየር ብከላ የሁሉም ግንብዛቤ ነው በሚል ርእስ ዙሪያ ሥር ባስደመጡት ንግግር አብራርተው፣ ለተፈጥሮ አየር ጥበቃ በሚደረገው ትግል የሁሉም ኅብረት አስፈላጊ ነው እንዳሉ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.