2015-08-05 19:41:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ከመንበረታቦት አገልጋዮች ጋር አብሮ ለመጸለይና ቃለ ምዕዳን ለመለገስ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና ማምሻውን ከመላው ኤውሮጳና ሌሎች አገሮች የተሰበሰቡ ከ9000 በላይ ለሚሆኑ የመንበረ ታቦት አገልጋዮች ማለትም በባህላችን እንደዲያቆናት ንፍቀ ዲያቆናትና አናጕንስጢስ የሚያገልግሉ ወጣቶችን ተቀብለው ባነጋገሩበትና አብረውም ጸሎተ ሰርክ በጸለዩበት ወቅት “በእግዚአብሔር መለኮታዊ ምሕረት የመዳንን ምስራች የሚያስከትለው ደስታ” ከሌሎች ጋር መካፈል እንዳለባቸው አሳስበዋል፣

ትናንትና በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ከ2 ሰዓት ጀምሮ በተልያዩ ዝግጅቶችና መዝሙሮች እንዲሁም ጸሎትና ምስክርነት የታከለበት ዝግጅት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተካሄደ በኋላ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ከወጣቶቹ ጋር አብሮ ለመጸለይና ቃለ ምዕዳን ለመለገስ በመካከላቸው ተገኝተዋል፣

የዚሁ ንግደ መሪ ከትንቢተ ኢሳያስ የተወሰድ ሲሆን “አብየት! እኔን ላክ” የሚለውን ቃል እንደ የአገልግሎትና በእግዚአብሔር እጆች ገዛ ራስን የመተው ምልክት ሆኖ የተጠቀሙበት አጋጣሚ ነበር፣ እንዲሁም የመንበረ ታቦት አገልጋይ በመሆን ለቅዱስ ቍርባን ያላቸውን ቅርበት ለመግለጥ ደግሞ “በዚሁ አገልግሎት ለእምነትና ለሌሎች ለማገልገል የምትማርበትና የምትለማመድበት ሜዳ” ሲሉ ገልጠውታል፣

በአደባባዩ ይታዩ ከነበሩ ባደሬዎች ለመረዳት እንደተጫለው ከሶስት የተለያዩ አህጉርና ከሃያ በላይ የሚሆኑ አገሮች የመጡ ወጣቶች እንደነበሩ ሲሆን የሰላም ምልክት በመሆን አብዛኛዎቹ ያግነቡት በተለይ ደግሞ ከዩክረይን የመጡ ወጣቶች ፍላጎታቸውን ለመግለጥ የተጠቀሙት ባንዴራ ነጭ ቀለም ያለው ነበር ይህም የሰላም ምልክት ነው፣ ከወጣቶቹ መካከልም አንድ ወጣት ይህንን ነጭ ባንዴራ ለቅዱሰነታቸው አረከባቸው፣ ሁላቸውም አብረው ቤተክርያትያንን የማገልገል ደስታ ለመግለጥ ዘምረዋል እንዲሁም ጸሎተ ሰርኩን ከቅዱስነታቸው በልዩ መንፈሳውነት አሳርገዋል፣

ቅዱስነታቸውም በበኩላቸው ባቀረቡት ስብከት “የኢየሱስ ፍቅር ሁሌ ኃይለኞች ስለሚያደርገን ዘወትር ድል እንቀዳጃለን፣ ምንም እንኳ ትንቢቱ እንደሚገልጠው ትናንሽና ደካሞች ብትሆኑ በኢየሱስ ጸጋና እርዳት ግን አዲስ ኃይል በመልበስ በሕይወት ጉዞ ለሚያጋጥሙ እክሎች ለማሸነፍ በቂ ኃይል አላችሁ” ሲሉ እነርሱ ብቻ ሳይሆን እኚህን ቃላት የተናገረው ራሱ ነቢይ ኢሳይያስ ይህንን እውነት እንደተረዳና “እግዚአብሔር ለአንድ ተልእኮ ሲያዘጋጅህ ኃጢአቶችህ ይቅር ብሎ ልብህን በማዘጋጀት ለተሰጠህ ተልእኮ ብቁ እንደሚያደርግህ ስለሚገልጥ ማለትም ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቃሉን ለማዳረስ እንዲሁም መለኮታዊ ምሕረቱን ለመግለጥ ጸጋውን ይሰጠሃል፣ ነቢዩ ኢሳያስም ይህን እውን ያደረገው ሁሉንም በእግዚአብሔር እጅ በመተውና በእርሱ በመተማመን ሲሆን ጌታም በበኩሉ ሁለመናውን በመለወጥ የእርሱ ብቍ መሳርያ እንዳደረገው ሁሉ ዛሬም ከወጣቶቹም ይሁን ከሌላ በኩል ነቢይ ሊያነሳ እንደሚችል” ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.