2015-07-27 15:42:00

ብፁዕ አቡነ ዘናሪ፦ ቅዱስ አባታችን ለሚሰቃየው ሕዝብ ቅርብ ናቸው


በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት እስላማዊ አገር ሲል ገዛ እራሱን የሰየመው እስላማዊው አክራሪው ታጣቂው ኃይል የሚሰነዝረው ጥቃት የሚፈጽመው ግብረ ሽበራ፣ በቱርክ ክልል የተቀሰቀሰው ውጥረት በተለይ ደግሞ በሶሪያ ተከስቶ ያለው ጦርነት ቀን በቀን የብዙ ሰው ሕይወት ለሞት ብዙ ዜጎች ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ እያጋለጠ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ቅዱስ አባታችን ካለ መታከት ዘወትር ለሚሰቃየው ሕዝብ ቅርብ መሆናቸው የሚያሰሙት የሰላም ጥሪ በማስደገፍ በሶሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በመሆን እ.ኤ.አ. ከ 2009 ዓ.ም. እያገለገሉ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ዘናሪ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 29 ቀን አባ ዳሎሊዮ የታገቱበት ሁለተኛ ዓመት የሚዘከር መሆኑ አስታውሰው፣ ውጥረትና ግጭት እልባት ሲያጣ የታገቱትን የመርሳቱ አዝማሚያ እየተለመደ ይሄዳል። አባ ዳሎሊዮ ሶሪያን የሚያፈቅሩ ለዚያ ክልል ሕዝብ ሰላምና ፍትሕ አቢይ አስተዋጽኦ ያበረከቱ በአገሪቱ የተለያዩ ሁሉም ሃይማኖቶች መካከል የጋራ ውይይት ያበረታቱ መሆናችው ብፁዕ አቡነ ዘናሪ ገልጠው፣ ከአባ ዳሎሊዮ ጋር ሌሎች ሁለት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ሰላማውያን ዜጎች ጭምር መታገታቸውንም አስታውሰው ቅዱስ አባታችን በሶሪያ ብቻ ሳይሆን በተለያየው የዓለማችን ክልል የታገቱት ሁሉ ነጻ እንዲለቀቁ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ያላሰለሰ ጥርት እንዲያደርግ ምእመናን ስለ ታገቱት እንዲጸልይ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው ብለዋል።

ቤቱንና ንብረቱ ጥሎ ወደ ጎረቤት አገሮች የተሰደዶው የሶሪያ ሕዝብ አራት ሚሊዮን በአገሩ ውስጥ የተፈናቀለውም ሰባት ሚሊዮን ከግማሽ መድረሱንም ገልጠው፣ የሞት አደጋ እንዲሁም የመቁሰል አደጋ የሚያጋጥመው የአገሪቱ ዜጋ ብዛት እጅግ ከፍ እያለ ነው። ከጠቅላላው የሶሪያ ሕዝብ ብዛት ውስጥ 60 በመቶ በሥራ አጥነት የተጠቃ ነው። ድኽነት አንዱ አደገኛ ቦምብ ነው። የዓለም አቀፍ ማኅብረሰብ ይኽ እየተዛመተ ያለው ጦርነት ለመግታት ወደ ውይይት የሚመራ በሳል ፖለቲካ እንዲያነቃቃ ጥሪ አቅርበዋል።

በሶሪያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በአገሪቱ ከሚገኙት የተለያዩ ሃይማኖት የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች ጋር በመገናኘት የጋራ ውይይት በማነቃቃት ሕዝብ በሰላም ባህል በማነጽ፣ ግብረ ሠናይ በማነቃቃት ለሚሰቃየው በድኽነት ለተጠቃው ለሚፈናቀለው ለሚሰደደው ሁሉ ቅርብ በመሆን መንፈሳዊና ሰብአዊ ድጋፍ እያቀረበች ትገኛለች፣ ለዚያ ክልል ሕዝብ ቅዱስ አባታችን ቅርብ መሆናቸው መስክረው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.