2015-07-20 16:37:00

ብፁዕ አቡነ አውዛ፦ እኩልነት የተረገገጠበት ልማት የንግዱ ዓለም አይከውነውም


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተጠናቀቀው ሦስተኛው ዓለም አቀፍ መዋዕለ ንዋይና ልማት በሚል ርእስ ዙሪያ በአዲስ አበባ በተወያየው ዓለም አቀፍ ጉባኤ የተሳተፉት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ብፁዕ አቡነ አውዛ፦ ተፈጥሮና አካባቢ የሚያከብር በጠቅላላ የምኅዳር ጤንነት ማአክል በማድረግ በዓለም የሚታየው እርሃብ ጨርሶ እንዲወገድና ሊደረስ የተወጠነው ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ግቡን እንዲመታ ማነቃቃት ያለው አስፈላጊነት እንዳስመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይሴባሕ በተሰየመው ዓዋዲ መልእክታቸው አማካኝነት የበለጸጉ አገሮች በገዛ እራሳቸው ጥቅም ላይ ብቻ የተዘጉ ከሆነ ለድኾች አገሮች ልማት መረጋገጥ መሰናክል ይሆናሉ። ስለዚህ የበለጸጉት አገሮች ለራስ ጥቅም ከማተኮር ምርጫ ተላቀው ድኾች አገሮች በዓለም የሚረጋገጠው የዕደ ጥበብ እድገት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥረት የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦

የገበያው ኤኮኖሚ ለሁሉም መፍትሔ አይሆንም

እርሃብ እንዲወገድ ልማት እንዲረጋገጥ ሰላም የተካነው ሕብረተሰብ የማያገል ሌላውን የማይነጥልና የማያስወግድ እኩልነት የተካነው ዓለም አቀፋዊ ኤኮኖሚ ተፈጥሮን የሚንከባከብ የኤኮኖሚ ሥልት ማረጋገጥ ድኽነት ለመቅረፍና የድኾች አገሮች ልማት ለማረጋገጥ ፈር መሆኑ አብራርተው ድኽነትና እርሃብ ለመቅረፍ የሚደረገው ጥረት ለገበያው ዓለም መተው አያስፈልግም ምክንያቱም የገባያው ኤኮኖሚ መፍትሔ አይሆንም እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ሥነ ምርምር ዕደ ጥበብ ለሁሉም በማዳረስ መተባበርና ፍትህ የተሰኙት የሥነ ምግባር መመዘኛዎች የገበያው ዓለም ለበለጠ ዓላማ እንዲምርራ እንደሚደግፍ አያጠራጥርም እንዲህ በመሆኑ የሁሉም ድኾች አገሮችና ሕዝቦች ልማት የሁሉም ኃላፊነት ነው እንዳሉ አስታወቀ።

ሦስት ምኅዳሮች

ብፁዕ አቡነ አውዛ ለአንድ ተቀባይነት ላለው ልማት መረጋገጥ ደጋፊያን የሆኑትና የተቆራኙት ሦስት ገጽታዎች እነርሱም መዋዕለ ንዋይ ለተሟላ የሰብአዊ እድገት እንዲያተኵር የእያንዳንዱ አገር በተለይ ደግሞ በልማት ጎዳና የሚገኙት አገሮች የሚግፍ ዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ ማረጋገጥና በመጨረሻም የሚወጠነው የልማት እቀድ እግብር ላይ ለመድረስ የሚደረገው ጥረት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ለልማት የሚወጣው ወጪ ለተገባውና ለተመደበበት ተግባር እንዲውል መቆጣጠር ያለው አስፈላጊነት እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.