2015-07-15 16:25:00

ሜትሮጶሊታ ዮአኒስ ዚዚኡላስ፦ “Laudato si’ - ይሴባሕ” ዓዋዲ መልእክት በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ለሚደረገው ውይይት መሠረት ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “Laudato si’ - ይሴባሕ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል የሚደረገው ለውህደት ያቀናው ለጋራው ውይይት መሠረት መሆኑ ዓዋዲ መልእክቱ ለንባብ ለማብቃት እ.ኤ.አ. ሰነ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በአዲሱ የሲኖዶስ አዳራሽ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ በመሳተፍ ንግግር ያስደመጡት የፐርጋሞን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሜትሮጶሊታ ዮአኒስ ዚዚኡላስ  ካቶሊካዊ ሥልጣኔ ከተሰየመው በየሁለት ሳምንት አንዴ ከሚታተመው የኢየሱሳውያን መጽሔት ዋና አዘጋጅ አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ጋር ባካሄድ ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።

የሥነ ምኅዳራዊ ቀውስ በቅድሚያ መንፈሳዊ ችግር ነው

በመጽሔቱ እንደሚነበበውም ሜጥሮፖሊታ ዚዚኡላስ ዓዋዲው መልእክቱ የተለያዩት አቢያተ ክርስቲያን ለአንድነት የሚጠራ የልብ መለወጥ የአኗኗር ሥልት እንለውጥ ዘንድ የሚጠራ መሆኑ ሲያብራሩ። የሥነ ምኅዳር ችግር በቅድሚያ መንፈሳዊ ችግር መሆኑና መሠረቱም የአዳም ኃጢአት ነው። ሰው ከተፈጥሮ ጋር የነበረው የተስተካከለ ግኑኝነት ያዛባውም ኃጢአት ነው። መዳን የሚፈልግ የሰው ልጅ ስግብግብነት የሚወልደው የሥነ ምኅዳር ሃጢአት ቸል ለማለት አይቻለውም። ከዚህ ጋር በማያያዝም ሜጥሮፖሊታ ዚዚኡላስ የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ አንደኛ በ 2002 ዓ.ም. ከዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጋር ሥነ ምኅዳር መንከባከብ ላይ ያነጣጠረው በቨነዚያ ሰነድ የሚጠራው ውል መፈረማቸው አስታውሰው፣ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሥነ ምኅድራ ጥያቄ ማእከል በማድረጋቸው የውህደት ኦርቶዲክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ደስ መሰኘታችው ገልጠዋል።

ምኅዳርና ሰብአዊ ፍትህ የአዋዲው መልእክት ማእከል ናቸው

የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለውህደት ያቀናው በጋራ የሚያካሂዱት ጥረት ያለፈው ታሪክ ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ወቅታዊው የዓለም ሁኔታ ጭምር የሚያስተውልና ወቅታዊውና መጻኢን የሚመለከት መሆን አለበት። አከባቢ ማክበር ሥነ ምኅዳር የልማት ጸር አይደለም፣ እንዳውም ለገዛ እርሱ ልማትና የዘርፈ ብዙ ልማት መሠረት ነው። ሁሉም አቢያተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ የሥነ ምኅዳር ቀን በጋራ የሚያከብሩበት ዕለት በጋራ ይወስኑ ዘንድ ያላቸው ምኞች ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ የውህደት ፓትሪያርክ እ.ኤ.አ. በ 1989 ዓ.ም. መስከረም 1 ስለ ተፈጥሮና ስለ የተፈጥሮ እቃቤ የሚጸለይበት ቀን እንዲሆን መወሰናቸውም አስታውሰው፣ ይኽ የጸሎት ዕለት በሁሉም አቢያተ ክርስቲያን ተቀባይነት አግኝቶ ገቢራዊ ቢሆን ለተፈጥሮ እንክብካቤ አቢይ የምስክርነት ምልክት ነው የሚሆነው በማለት ገልጠዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.