2015-07-13 16:20:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ በፓራጓይ ኑ ጉአዙዝ ያሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ፍጻሜ በኋላ የአሱንሲዮን ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድሙንዶ ፖንዚኣኖ ቫለንዙወላ መሊድና በደቡብ አመሪካ ለቁስጥንጥንያ የውህደት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ታራሲዮስ ካሰሙት የሰላምታና የምስጋና ቃል በኋላ ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው በፊት ኢየሱስ የማርያም እናትነት በመስቀል ላይ ሆኖ በስቃይ ላይ እያለ የሰጠን ጸጋ ነው። የማርያም እናትነት የኢየሱስ ለእኛ የመሰዋት ጸጋ ነው። ከዚያች ሰዓትና ቀን በኋላም ማርያም ከልጆችዋ ጋር ነች፣ በተለይ ደግሞ ከሚሰቃዩትና በድኽነት ከተጠቁት ጋር ነች በሚል በማርያም እናትነት ላይ ያነጣጠረ አስተንትኖ ማስደመጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በሕዝቦች ታሪክ የገባች በሁሉም አገሮች በላቲን አመሪካ በፓርጓይ የሚኖር እምነት የማርያም ፍቅር የሚንጸባረቅበት ነው። በታማኝነት ወደ ማርያም እናትነት አቅኑ፣ ልባችሁ ለእናትነትዋ ክፍት አድርጉ፣ የሕይወታችሁ ገጠመኝ ሁሉ በእማኔ አቅርቡላት። በእናታዊ ፍቅሯም ታጽናናችኋለች፣ በልባችሁ ተስፋ ቦግ እንዲል ታደርጋለች።

በዚያ በጽርሃጽዮን ከደቀ መዝሙርት ጋር በመሆን ለጸናች ማርያም (ግብረ ሐዋ. 1፣ 13-14) በቤተ ክርስቲያን ላይ ከለላዋ ታኖርም ዘንድ በቤተ ክርስቲያን አባላት ዘንድም የወንድማማችነት መንፈስ ታጸና ዘንድ እማጠናለሁ። በማሪያም አማላጅነት ቤተ ክርስቲያን የሁሉም ቤት ሁሉንም የምታስተናግድ ለሁሉም አሕዛብ እናተ ትሆን ዘንድ እጸልያለሁ።

ውዶቼ ዘወትር ስለ እኔ ትጸልዩ ዘንድ አደራ። የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በፓራጓይ እጅግ የተፈቀረ መሆኑ የተረጋገጠ ነው። እኔም በልቤ አኖራችኋለሁ ስለ እናንተና ስለ አገራችሁም እጸልያለሁ ብለው ጸሎት መልአከ እግዚእብሔር መርተው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.