2015-07-13 16:24:00

አባ ሎምባርዲ፦ ቅዱስ አባታችን የመላ ፓራጓይ ሕዝብ እምነት ያጸናሉ


የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱ ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከፓራጓይ ሕዝብ ተወካዮች ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት የአገሪቱ ሕዝብ በተወካዮች አማካኝነት የገዛ እራሱ መጻኢ ባለቤት መሆኑ ለማረጋገጥ እንዲችል ሕዝብና ተወካዮች እንዳበረታቱና በኑ ጉኣዙ መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከትም የፓራጓይ እምነት በማርያማዊ መንፈሳዊነት የተሞላ መሆኑ መመስከራቸው ገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የፓራጓይ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ለማጠቃለል መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳራጉበት ሥፍራ የአገሪቱ መእመናን የሚኖረው ማርያማዊ መንፈሳዊነት ማእከል መሆኑ አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ የአገሪቱ ሕዝብ የማርያም አማላጅነት እናትነት የሚኖርበት የሚመሰክርበት ቅዱስ ሥፍራ ነው። ቅዱስ አባታችን ገና የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ ከፓራጓይ ተሰዶ በአርጀንቲና የሚኖረው የፓራጓይ ዜጎች በቅርብ የሚያውቁ ናቸው። የቅዱስ አባታችን ምስክርነት ተራው ሕዝብ የሚኖረው መንፈሳዊነት ጥልቅ አይደለም ብለው ለሚያምኑ የስሜታዊ ሃይማኖተኛነት ነው ብለው ለሚፈርዱ አንዳንዴ የቲዮሎጊያ ሊቃውንት ለሚገኙባቸው ምህራን አካላት ተጋርጦ ነው።

ከአገሪቱ የበላይ አካላት ጋር ተገናኝተው ባሰሙት ንግግር በዓለም የሚታየው ምግባረ ብልሽት ሙስና አድልዎ የመሳሰሉትን ችግሮች ሁሉ ዳሰዋል፣ ስለ ጉዳዩ ሰፊ አስተንትኖ አቅርበዋል፣ የሕዝቡ የወጣቱ የቤተ ክርስቲያን ጥያቄ መሠረት በማድረግ ያቀረቡት ንግግርና ምዕዳን መሆኑ አባ ሎምባርዲ ገልጠዋል።

የአንዲት አገር ብልጽግና በጥቂቱ ዜጋ የሚከወን ሲሆን የመነጠል አዝማሚያ ይኖረዋል። በአገር ብልጽግና ሁሉም ዜጋ ተሳታፊ የሚያደርግ እድገት ለሁሉም የአገር ሕዝብ የሚበጅ ሁሉንም የሚያቅፍ እኩልነትና ፍትህ የሚከተል እንደሚሆን ቅዱስ አባታችን ባስደመጡዋቸው ንግግር እንዳሰመሩበትም አባ ሎምባርዲ አብራርተው፣ በተደመጡት ንግግሮች ሁሉ ወንጌላዊ ኃሴት የተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ጎላ ብሎ መንጸባረቁንም ገልጠው፣ ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ አመራር እድገት እንዲኖር የሚያሳስብና የሚደገፍ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ሁሉ የሚደረግላቸው አቀባበል እጅግ የሚያስደንቅ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.