2015-07-06 18:42:00

የር.ሊ.ጳ 9ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት በደቡብ አሜሪካ (ኤኳዶር ቦሊቭያና ፓራጓይ)


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሶስት የላቲን አመሪካ ሀገራት ይኼውም በኤኳዶር ቦሊቭያ እና ፓራጓይ  ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ትናትና እሁድ ጥዋት መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ተንስተዋል። ቅድስነታቸው ከሮም ከለኦናርዶ ዳ ቪንቺ  ዓለም አቀፍ አውሮጵላን ሲነሱ  ውሉደ ክሕነት እና የመንግስት ባለስልጣናት አውሮፕላን ማረፍያው ተገኝተው ሸኝቶዋቸዋል መልካም ጉዞም ተመኝተውላቸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በኤኳዶር ሰዓት አቁጣጠር ከቀትር በኃላ ሶስት ሰዓት ርእሰ ከተማ ኲቶ ገብተዋል። የኤኳዶር ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ባለ ስልጣናት እና የሀገሪቱ መንግስት ፕረሲዳንትእና ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርግውላቸዋል። የቫቲካን እና የኤኳዶር ብሔራዊ መዝሙሮች እንደተሰሙ የሀገሪቱ መሪ ፕረሲደንት ራፋኤል ኮረአ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድርገዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው ባሰሙት ቃል፡ “ክቡር ፕረሲደንት፤ የተከበሩ የመንግሥት ባለሥልጣኖች፤ በጵጵስና ወንድሞቼ፤ክቡራትና ክቡራን ጓደኞቼ ሁላችሁም፤- እንደገና በደቡብ አመሪካ እንድመጣና ዛሬ በዚችው ውብ የሆነች የኤኳዶር መሬት ከእናንተ እንድገናኝ ላበቃኝ እግዚአብሔር አመሰግናለሁ፣ የዚህችው የተከበረች አገር ሕዝብ መለያ በሆነው የእንግድነት ደማቅ አቀባበል እጅግ ደስ ብሎኛል ምስጋናየን አቀርባለሁ፣የተከበሩ ፕረሲደንት ባቀረቡልኝ መልካም ንግግር እንዲሁም ከሓሳቤ ጋር መስማማታችሁን ለመግለጥ ደጋግመው ስለጠቀሱኝ አመሰግናለሁ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ! ለሕዝብዎ መልካም የሚያስቡት እንዲፈጸምልዎና ተልእኮዎ ስኬታም እንዲሆን ያለኝን መልካም ምኞት እገልጣለሁ፣ለመንግሥት ባለሥልጣናትና ወንድሞቼ ለሆኑ ጳጳሳትና የመላዋ የአግሪቱ ቤተክርስትያንን ምእመናን እንዲሁም በዛሬው ዕለት የልቦቻቸው የቤተሰቦቻቸውና የአገራቸው በሮች ለፈቱልኝ ሁላቸው ልባዊ ሰላምታየን አቀርባለሁ፣ ለሁላችሁ ሰላምታየና ምስጋናየ ይድረሳችሁ፣

ከዛሬ በፊት ለሓዋርያዊ እረኝነት ስል ብዙ ጊዜ ኤኳዶርን ጐብኝቻለሁ፤ ዛሬም እንደግና የእግዚአብሔር ምሕረትንና ያች የዚህ ሕዝብ ማንነትን ያነጸችና ብዙ ፍሬ ያፈራች የኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ምስክር በመሆን መጥቼአለሁ፣ የዚህች እምነት ፍሬ ከሆኑ ብርሃናዊዋ ምሳሌ የሆነች ቅድስት ማርያና ዘኢየሱስ ቅዱስ ወንድም ሚሸል ፈብረስ ቅድስት ናርቺሳ ዘኢየሱስ እንዲሁም ር.ሊ.ጳ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የዛሬ ሰላሳ ዓመት ጓያኩል በጎበኙበት ወቅት ብፅ ዕናዋን ያወጁ ብፅዕት መርሰደስ ዘኢየሱስ ሞሊና መጥቀስ ይቻላል፣ እነኚህ ቅዱሳን እምነታቸውን በጦፈ ሁኔታ መስክረዋል በተለያዩ የማኅበረሰቡ ኑሮዎች የምሕረት ሥራ እያበረከቱ ኖረዋል፣ እኛም ዛሬ የሚያጋጥሙንን እክሎች ለመጋፈጥ እና እስከዛሬ የተቀዳጀናቸውን ግሥጋሴና ሥልጣኔ ለሁላችን ብሩህ መጻኢ እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ ያሉንን ልዩነቶች በመቀበልና ውይይትን በማራመድ እንዲሁም ማንንም ሳናገልል በወንጌል መፍትሔ ለማግኘት እንችላለን፣ ይህንም ገና የደቡብ አመሪካ ዕዳ የሆኑትን የተንኮተኮቱ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን በመርዳት እናድርገው፣ ቤተ ክርስትያንም የኤኳዶር ሕዝብን በማገልገል ድርሻዋን እንደምታበረክት ለክቡር ፕረሲደንት ቃል እንገባለን፣

ውዶቼ! እፊታችን ያሉትን ቀናት በተስፋ በመጠባበቅ ጉብኝቴን እጀምራለሁ፣ በኤኳዶር ቺምቦራዞ የሚባለው ቦታ ለህዋ እጅግ ቅርብ ሆኖ ለጸሓይ ለጨርቃና ለከዋክብት ቅርበት አለው ይባላል፣ እኛ ክርስትያኖች ኢየሱስ ክርስቶስን ከጸሓይ ቤተክርስትያንንም ከጨረቃ እናመሳስላቸዋለን፣ ጨረቃ የገዛ ራሷ ብርሃን የላትም፣ ከጸሓይ የተደበቀች እንደሆነ ትጨልማለች፣ ቤተ ክርስትያንም ጸሓይ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ የተለየች ወይንም የተደበቅ እንደሆነ ትጨልማለች ምስክርነቷን ለመስጠት አትችልም፣ በዚሁ ቀናት “ከላይ ከምትወጣ ጸሓይ” (ሉቃ 1፡78) ቅርበታችንን ለመመስከርና የብርሃንዋና የፍቅርዋ ነጸብራቅ እንሁን፣ ከዚሁ ቦታ መላው ኤኳዶርን ማለትም ከኪምቦራዞ ጫፍ እስከ ሰላማዊ ውቅያኖስ ጠረፍ እንዲሁም ከአማዞንያ ዱር እስከ ጋላፓጎስ ደሴቶች ለማቀፍ እወዳለሁ፣ እግዚአብሔርን ላደረገላችሁና ገናም እያደረገላችሁ ስላለው ሁሉ ከማመስገን አትቦዝኑ፤ ታናሹንና ደካማውን እንድትከላከሉ ችሎታ ይኑራችሁ፣ በወጣቶቻችሁ ተስፋ አኑሩ፤ የሕዝባችሁ ታሪክና ዝክር ለሆኑ አዛውንቶችንና ሕጻናትን ተንከባከቡ፣ ፕረሲደንታችሁ እንዳለው ገነት በሆነችው በአገራችሁ ግርማና በሕዝባችሁ ክብር ተደነቁ፣ኤኳዶር ለጥበቃው እንደ ጉልት የተሰጠችው ጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስና ጥቀ ቅዱስ ልበ ንጽሕት ድንግል ማርያም ጸጋና ቡራኬ ያፍስስላችሁ፣ ብዙ ምስጋና አቀርባለሁ! እግዚአብሔር ይስልኝ፣” ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል፣

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እና የኤኳዶር መሪ ፕረሲዳነት ራፋኤል ኮረአ አውሮፕላኑ ማረፊያ በሚገኘው የፕሮቶኮል አዳራሽ አጭር ቆይታ አድርገው ሐሳብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከኲቶ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ሚያርፉበት ከተማይቱ ውስጥ ወደ ሚገኘው ቤተ ሊቀ ጳጳሳት ተጉዘው የትናንትና ውላቸውን አጠቃልለዋል። ቅድስነታቸው ትናትና በኤኳዶር የጀመሩመሩት ሐዋርያዊ ጉብኝት የቀጠለ ሲሆን ዛሬ ረፋድ ላይ በሀገሪቱ ሰዓት አቁጠጠር 265 ኪሎ ሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው ወደ ጓያኲል ከተማ መብረራቸው ይታውቃል። ጓያኲል ከተማ እንደ ደረሱ በከተማይቱ ሊቀ ጳጳስ የሚመሩ የቤተ ክርስትያን ባለ ስልጣናት እና የመንግስት ሹማምንት አቀባበል አድርግውላቸዋል።

ቅድስነታቸው ከጓያኲል አውሮፕላን ማረፍያ ከተማይቱ ውስጥ ወደ ሚገኘው ወደ ብሔራዊ ገዳመ መለኮታዊ ምሕረት ተጉዘው እዚያው በግል ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመዋል። ከዚህ ሎስ ሳማነስ ወደ ተባለው ትልቅ መናፈሻ የተጓዙ ሲሆን በዚሁ መናፈሻ ሲጠባበቅዋቸው የቆዩ በብዙ ሺ ምእመናን በደስታ እና በእልልታ አቀባበል አድርጎውላቸዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሎስ ሳማነስ ትልቅ መናፈሻ በበርካታ ካርዲናልት ጳጳሳት እና ካህናት ተሸኝተው ሥርዓተ ቅዳሴ አሳርገዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራኒሲስ በሎስ ሳማነስ ትልቅ ማናፈሻ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምእመናን በተሳተፉበት ሥርዓተ ቅዳሴ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ እና ባሰሙት ስብከት  የዕለቱ  ቃለ ምንባብ  ወንጌል  የቅዱስ ዮሐንስ  ወንጌላዊ  ዋቢ በማድረግ በገሊላ ክፍለ ሀገር በምትገኘው ቃና በተባለው ቦታ ሠርግ ነበር የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች። ኢየሱስ እና ደቀ መዛምርቱም ወደ ሰጉ ተጠርተው ነበር በሠርጉ ግብጃ ላይ የውይን ጠጁ ባለቀ ግዜ የኢየሱስ እናት ኢየሱስን የወይን ጠጅ የላቸውም እኮ አለችው ኢየሱስም አንቺ ሴት ከአንቺ ጋ ምን አለኝ ግዜየ ገና አልደረሰም እኮ አላት። በዚያን ግዜ እዚያ ለነበሩት አገልጋዮች እሱን የሚላችሁ አድርጉት አለቻቸው። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስብከታቸውን በማያያዝ አይሁዳውያን የመንጸት ሥርዓት ስለ ነበራቸው ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ነበሩ እያንዳንዱ ጋን ሁለት ወይም ሶውስት እንስድራ ውሃ ለመያዝ ይችል ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮችቹን ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው አላቸው እነሱም እስከ አፋቸው ሞሉአቸው ከዚህ በኃላ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮቹን በሉ አሁን ቀድታችሁ ለግብጃው ሐላፊ ስጡት አላቸው እነሱም ወስደው ሰጡት የግብጃውን ሐላፊ ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውሃ በቀመሰ ግዜ ከየት እንደመጣ አላወቀም ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር። ኢየሱስ ይህን ተአምራት ሁሉ መጀመርያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ክልል ቃና በተባለ ቦታ አደረገ በዚህ ዓይነት ክብሩን ገለጠ ደቀ መዛምርቱም በሱ አመኑ። ቅድስነታቸው ዮሐንስወንጌል ምርኩስ በማድረግ የኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመርያ የቃና ተአምር ከሰበኩ በኋላ ቤተ ሰብ አንድ ትንሽ ውስጣዊ ቤተ ክርስትያን ያቆማል ይህም ሕይወት ይሰጣል መለኮታዊ ምሕረትም ያስተላልፋል  በማለት በስብከታቸው ላይ አክለው አመልክተዋል።

እምነት በቤተ ሰብ ላይ ከየእናት ወተት ይዳበለቅ እና የወላጆች ፍቅር ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ያቀርባል ብለዋል ቅድስነታቸው። የምሕረት ዓመተ ኢዮቤል ከመጀመሩ በፊት ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክስርትያን ቤተ ሰብን ትኩረት የሰጠ የጳጳሳት ሲኖዶስ ትጀምራለች ካሉ በኃላም በአሁኑ ግዜ ቤተ ሰብን የሚፈታተኑ እና በቤተ ሰብ ያንሰራፉ ችግሮች እና እክሎች መፍትሔ ለማግኘት ሁነኛ ጥረት እንደታካሄድም በኤኳዶር በጓያኲል በሎስ ሳማነስ ትልቅ ማናፈሻ የተካሄደውን ሥርዓተ ቅዳሴ ለተከታተለ በብዙ ሺ ለሚግመት ህዝብ ክርስትያን ባሰሙት ስብከት አስገንዝበዋል።

በሎስ ሳማነስ ትልቅ ማናፈሻ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የተመራ ሥርዓተ ቅዳሴ ከተጠናቀቀ በኃላ የጓያኲል ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ አንቶንዮ አረጊ ያርዛ ቅድስነታቸውን አመስግነዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሥርዓተ ቅዳሴ ተሳታፊ ለሆኑ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተዋል። በመጨረሻም ሃያ አንድ ኪሎ ሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው ሃፍየር የኢየሱሳውያን ኮለጅ ተጉዘው ከተከታቶቻቸው እና ከኮለጁ አባላት ጋ ለምሳ ተቀምጠዋል።

ከምሳ እና አጭር እረፍት በኃላም ከጋያኲል ከተማ በሀገሪቱ ሰዓት እቁጣጠር ከምሽቱ አስራ ስማንት ከአስራ አምስት ደቂቃ ወደ ርእሰ ከተማ ኲቶ ተመልሰዋል። ከዝያም የክብር ጉብኝት ለማድረግ ወደ Carondeler ቤተመንግስት ተጉዘው ከመራሄ መንግስት ከፕረሲዳንት ራፋኤል ኮረአ ጋር ተገናኝተው ሐሳብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፋርፋንሲስ በCarondeler ቤተመንግስት ከፕረሲዳንቱ እና ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት ጋ ያደረጉት ውይይት እንደተጠናቀቀ በፕረዚዳንቱ ተሸኝተው በሐምሳ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ሚገኘው የኲቶ ካተድራል ተጉዘው ካተድራሉ ውስጥ ከተገኙ ምእመናን ለሥርዓተ ጸሎት ቆይታ አድርገዋል። ለምእመናኑም ይህን ቃል ሰጥተዋል “ውድ ወንድሞች፣ ወደ ኪቶ የመጣሁት ለመንፈሳዊ ንግደት ሲሆን ከእናንተ ጋር የስብከተ ወንጌል ደስታን ለመካፈል ነው፣ ከቫቲካን ስነሳ ከቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ሆና የር.ሊ.ጳ ጉዞዎችን የምትጠብቀው የቅድስት ማርያና ዘኢየሱስ ስእልን ተሳልሜ ነው ጉዞየን የጀመርኩት፣ እኛ ሁላችን ከምሳሌዋ እንድንማርና ይህ ጉዞ ፍሬ እንዲኖረው ለእሷ ተማጠንኩኝ፣ የመስዋዕትዋ ብርታት ዋጋ በግብረ  ምግባረ ሠናይዋ በሊልይ አበባ ይመሰላል፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ያለው ምስልዋም በ ሊሊ እቅፍ አበባ ነው፤ በቤተክርስትያን ማእከል ሆና የሁላችን እቅፍ አበባዎች የመላው ኤኳዶር ለጌታ ታቀርባለች፣

ቅድስት ናርቺዛ ዘኢየሱስና ብፅ ዕት መርሰደስ ዘኢየሱስ ሞሊና በቅድስት ማርያና ምሳሌ ለቅድስና እንደደረሱ ሁሉ እኛም እንድንመስላቸውና ትምህርታቸውን እንድንከተል ቅዱሳን ዘወትር ጥሪ ያቀርቡልናል፣ ዛሬ በዚህ ቦታ ስንቶች ናቸው በተለያዩ ችግሮችና መከራዎች የሚሰቃዩት ስንቶችስ ናቸው የሙት ልጆች በመሆናቸው የሚሰቃዩና በስቃይ ላይ የሚገኙ እንዲሁም ገና በልጅነት እድሜያቸው የታናናሾቻቸውን የሕይወት ሓላፊነት ያሚረከቡ ስንቶችስ ናቸው በየእለቱ በሽተኛንና እዛውንትን በማስታመም የሚገኙትን በሙሉ ቅድስት ማሪያና እንዳደረገችው እንዲሁም ቅድስት ናርቺዛና መርሰዲስ አርዓያነቷን ተከትለዋል። እግዚአብሔር ከኛ ጋር እንደሆነ ማወቁ ከባድ አይደለም። እነሱ ከዓለም ዓይን የተለየ ምንም አዲስ ነገር አልፈጸሙም። የፈጸሙት የክርስቶስን ስጋ ስቃይና መከራ በሕዝቡ ላይ በሚያሳዩት የፍቅር አገልግሎት ምስክርነት ነበር ይሕንንም ሲያደርጉ ብቻቸውን አልነበሩም ከሌሎች ጋር በሕብረት ሆነው ነበር። የምንገኝበትን ካቴድራል ለመመስረት ስራውን ለመስራት ከመጓጓዣው ግንበኛው አናጢው ጀምሮ ባገሩ ሕዝቡና ባሕል ደንብ መሰረት ነው። በሕብረት በመስራት ለማኅበረሰቡ መጠቀሚያ ያለ ትዕዛዝ ማስታወቂያና ጭብጨባ ተገነባ። እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልገው እነዚህ የድንጋይ አለቶች ቤተክርስቲያኑን ያቆሙ እንዲሁም እኛ ሌሎች የጎደለባቸውን ነገሮች በኅላፊነት ከመመልከት ባሻገር በመርዳት የብዝዎቹን ወንድሞች ህይወት ካጋጠማቸው ችግርና ተስፋመቁረጥ ማውጣት እንችላለን።  ዛሬ በዚህ ቦታ ስገኝ የልባችሁን የደስታ ተካፋዮች አድርጋችሁኛል። ሰላምን የሚያወራ መልካም የምስራችንም የሚናገር መድኅኒትንም የሚያወራ ጽዮንንም አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው። (ኢሳ.52) የተጠራንበት ውበት የክርስቶስን መልካም የሽቶ መዓዛን እንድናሰራጭ ነው። ጸሎታችን ግብረ ሰናይ ተግባራችን መስዋዕታችንና ምስክርነታችን የክርስቶስ መልካም መዓዛ ጠረን ይኑረው። እናንተም ይህንን አውቃችሁ ብትሠሩ ብፁዓን ናችሁ።(ዮሐ.13፡17) ጌታ ይባርካችሁ!”       

ከሥርዓተ ጸሎት በኋላ ወደ ቤተ ሊቀ ጳጳሳት ተመልሰዋል በዚህም የዛሬ ውሎአቸው ተጠናቅቀዋል። የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ኤኳዶር ሐዋርያዊ ጉብኝት ነገም ቀጥሎ ይውላል።








All the contents on this site are copyrighted ©.