2015-06-10 19:04:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! በቤተሰብ ዙርያ የጀመርነውን ትምህርት እንቀጥላለን፤ በዛሬው ትምህርታችን በቤተ እጅጉን የጋርዮሽ የሆነ ጉዳይ ስለ ሕመም እንመለከታለን፣ ደካማ ፍጡሮች የመሆናችን ተመክሮ ነው፤ በተለይ በቤተሰብ ውስጥ የምንኖረው ከሕጻናት ጀምሮ በተለይ ደግሞ የዕድሜ ባለጠጋዎች በእርጅና ሲደክሙ! አይደለም እንዴ?

በቤተሰብ ዙርያ ያለው መተሳሰር በተልይ የምናፈቅራቸው ሰዎች በሕመም ሲሰቃዩ ማየት እጅግ የሚያሳዝን ነው፣ ይህንን ኃዜኔታ በውስጣችን የሚቀሰቅሰው ፍቅር ነው፣ አብዛኛውን ጊዜ ለአንድ አባት ወይንም ለአንድ እናት ከገዛ ራሳቸው ሕመም ይልቅ የልጃቸው ሕመም ይከብዳቸዋል፣ ብዙ ቤተሰብ እጅግ ቅርብ የሆነ ሆስፒታል ነው ተብለዋል፣ በዘመናችን ሆስፒታል እጅግ ለተወሰኑ ጥቂቶች ብቻ የሚያገልግል ሆኖ እጅግ በራቀ ስፍራም ይገኛል፣ በቅርብ የማስታመም ዋስትና የሚሆኑና ከሕመም ለመዳን የሚረዱ እናት አባትና አያቶች ናቸው፣

በወንጌል ኢየሱስ ከሕመምተኞች ጋር ሲገናኝና ሲፈውሳቸው የሚተርኩ ብዙ ክፍሎች አሉ፣ እርሱ ሕመምን እንደሚፈውስ ሆኖ በሕዝብ ዘንድ ይቀርባል የሰው ልጅን ከማንኛው ሕመም ሊያድን እንደመጣም ይነግራል፣ መንፈሳዊ ሕመምና ሥጋዊ ሕመም፣ በማርቆስ ወንጌል “ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ” (1፡32) የሚለው ቃል ኅልናን የሚቀስቅስ ጥቅስ ነው፣ የዘመናችን ትላልቅ ከተማዎችን ሳስብ ሕመምተኞችን ለማዳን ተስፋ በማድረግ ይዘናቸው የምንሄድባቸው በሮች የት ይገኙ ይሆን ብየ እጠይቃለሁ፣ ጌታ ኢየሱስ አንዲት እናት ወይንም አንድ አባት ልጆቻቸውን ይዘው በመምጣት እጆቹን እንዲያኖሩላቸው በሚጠይቁበት ጊዜ አለምንም ማመንታት ይፈውሳቸው ነበር፣ ፈውሱ ሕግን ይቀድም ነበር፤ ለምሳሌ ያህል ቀዳሚት ሰንበትን አክብር የሚለውን ሕግ በመሻር ብዙዎችን በሰንበት ፈወሰ (ማር 3፤1-6) የህግ ሊቃውንት ለኢየሱስ ካቀረቡት ክሶች አንዱም በሰንበት አይሁድ ይፈውስ በመኖሩ ነው፤ ነገር ግን የኢየሱስ ፍቅር ጤና ለመስጠትና መልካም ነገር ለመሥራት ነበር፣ ይህ ተቀዳሚ ሥራው ነበር፣

ኢየሱስ ሐዋርያትን ሲልካቸው ሕሙማንን ለመፈውስ ሥልጣን ሰጣቸው “አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው።” (ማቴ 10.1) ይላል፣ በየሐንስ ወንጌል 9፡1-5 በተመለከተው ስለ በዕውሩ የተወለደ ሰው ለሐዋርያት ያለውን ማስታወስ አለብን ሓዋርያቱ ዕውሩን ባዩ ጊዜ በማን ኃጢአት ይሆን እንዲህ የሆነው የገዛ ራሱ ይሁን የወላጆቹ በማለት ሲከራከሩ ኢየሱስ ጥርት ባለ መንገድ የእርሱም አይደል የወላጆቹ የእግዚአብሔር ሥራ እንዲታይ ነው እንጂ ብሎ ይመልስላቸዋል፣ ልጁንም ይፈውሰዋል በዚህም የእግዚአብሔር ክብር ታየ፣ የቤተክርስትያን ሥራም ይህ ነው ሕሙማንን መፈወስ እንጂ በሓሜትና ንትርክ ግዜን ማባከን አይደለም፤ መርዳት ማጽናናትና መፈውስ እንዲሁም ዘወተር በሕመምተኞች አጠገብ መገኘት ይህ ነው የቤተ ክርስትያን ሥራ፣

ቤተ ክርስትያን ስለታመሙ ወገኖቻችን እንድንጸልይ ጥሪ ታቀርባለች፣ ለሕመምተኞች መጸለይ መጓደል የለበትም፣ በግልም ይሁን በማኅበር አብዝተን መጸለይ አለብን፣ በወንጌል ማቴዎ 15፡21-28 ተመልክታ ስላለችው ስለከናዓኒትዋ ሴት ያስተነተን እንድሆነ አንዲት አረሜናዊት ሴት ማለትም ከሕዝበ እስራኤል ያልሆነች ኢየሱስን ልጅዋን እንዲፈውስላት ስትለምነው ኢየሱስም እምነትዋን ሌፈትን ድርቅ ባለ መንገድ “መጀመርያ የእስራኤል መንጋየን ነው ማየት ያለብን አልችልም” ሲላት ሴትዪቱ ግን ምንም ሳትታክት ልመናዋን መቀጠልዋ በነገራችን ላይ አንዲት እናት ለፍጥረትዋ እርዳታ ስትጠይቅ በምንም ተአምር አትታክትም፤ ሁላችን እንደምናውቀው እናቶች ለልጆቻቸው እስከ መጨረሻ ይታገላሉ፣ ኢየሱስ የልጆች ምግብ ለውሾች መስጠትም አይሆንም ናላት ግዜም በታላቅ እምነት ውሾችም ጌቶች በተመገቡበት የወደቀውን ርፍራፊ ይበላሉ ስትል በመለሰችበት ጊዜ “ሴትዬ ሆይ እምነትሽ ታላቅ ነው እንደፈለግሺው ይሁን” ብሎ ልመናዋን ሲመልስ እንመለከታለን፣

በቤተሰብ ሕመም ሲያጋጥም በሰብአዊ ደካማነት በቤተሰቡ ችግር ይፈጠራል፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የሕመም ግዜ የቤተሰብ መተሳሰርን ያጐለብታል፣ ስለዚህ ልጆቻችንን ከሕጻንነት ጀምረን በሕመም ጊዜ ስለሚያስፈልገው መተባበርና መረዳዳት ልናስተምራቸው ያስፈልጋል፣ የዚህ ዓይነት ትምህርት ለሰብአዊ ሕመም ማስታገሻ በመሆን ልብን ያራራል፣ አለበለዚያ ልበ ደንዳና በመሆን መደንዘዝም ይቻላል፣ ለመሆኑ በሥራ መስክም ይሁን በሌላ አጋጣሚ ስንት ወላጆች አባትም ይሁን እናት በድካም ተሸንፈው ፊታቸው ገርጥጦ እንመለከታለን፤ ደህና አይደለህም እንዴ ብለይ የጠየቅን እንደሆነ ትናንትና ጥቂት ሰዓታት ነው የተኛሁት ልጃችን ታሞ እኔና ባለቤተ በየተራ ስናስታምመው አደርን ይሉናል፣ እነኚህ ሥራዎች የጀግንነት ሥራዎች ናቸው፣ በጽናትና በብርታት ይፈጸማሉ፣

የቅርብ ወዳጆቻችን የምናፈቅራቸው ሰዎች ድካምና ሥቃይ ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን የሕይወት ትምህርት ሊሆኑ ይችላሉ፤ የአንድ ቤተሰብ አባል ሲታመም ቅርብ ሆኖ መርዳትን ልጆቻችን እንዲማሩት የልጅ ልጆቻችን ደግሞ እንዲረዱት ማድረግ ያስፈልጋል፣ ይህንን የሚረዱት ደግሞ በታመሙ ጊዜ በጸሎትና በፍቅር ቀርበን ስናስታምማቸውና ቤተሰባዊ መተሳሰብና ፍቅርን ስንገልጽላቸው ነው፣ ማኅበረ ክርስትያን አንዲት ቤተሰብ በሕመም ስትፈትን ብቻዋን መተው እንደሌልብን ጠንቅቀው ያውቃሉ፣ ለዚሁ ወንድማማዊ የቤተ ክርስትያን መረዳዳትም ማለትም ቤተሰቦች በሥቃይና ሕመም ጊዜ ቅርብ ሆነው ስለሚረድዋችው ጌታን ማመስገን አለብን፣ አንድ ቤተሰብ በሌላው ቤተሰብ ላይ የሚያሳየው ክርስትያንዊ መቀራረብ የአንዲት ቍምስና እውነተኛ መዝገብ ነው፤ የተስፋ መዝገብ ሆኖ በችግር የሚገኙትን ቤተሰቦች የእግዚአብሔር መንግሥት ቀለል ባለመንገድ ለመረዳት ይጠቅማል፣ የእግዚአብሔር ቅርበት ናቸውና፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.