2015-06-10 16:21:00

ጋና፦ የብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ


በጋና ርእሰ ከተማ አንካራ በክዋመ ንክሩማህ ክልል በሚገኘው በአንድ የነዳጅ ማደያ ማእከል ባጋጠመው የቃጠሎ አደጋ ያስከተለው አሰቃቂው የብዙ ሰው ሕይወት ሞትና የንብረት መውደም የጋና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እጅግ ለሓዘን እንደዳረገውና ለተጎዳው ለሟች ቤተሰብና ንብረታቸው ላጡት ሁሉ ቅርብ መሆኑ ባወጣው መግለጫ አንዳመለከተ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በዚያ እ.ኤ.አ. ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከሰተው የቃጠሎ አደጋና አሁኑም ገና የሚታየው ኃይለኛው ዝናብ እያስከተለው ያለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ብዙ ሕዝብ አለ ቤትና ንብረት ማስቀረቱንም የጋና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ በመጥቀስ፣ ሕይወቱን ያጣው 150 የአገሪቱ ዜጋ እግዚአብሔር በመንሥቱ እንዲቀበላቸው ተማጥነው ለቆሰለው ለተፈናቀለው ሁሉ ትብብርና ድጋፍ ይቀርበለት ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ገለጠ።

ኃይለኛው ዝናብ እያስከተለው ባለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት እይደረሰ መሆኑ የገለጠው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ አክሎ የቤቶችና የከተሞች ግንባታና የማስፋፋት እቅድ የሰው ልጅ ህይወት ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጥ እንጂ እንዳመጣውና እንዳሻው ግንባታውን ማፋጠን ግንባታ ሳይሆን ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ውድመት የሚያስከትል መሆኑ ጭምር በማብራራት፣ አደጋው ከተከሰተ በኋላ ወደ ተጎዳው ክልል የሚኒስትሮች መጉረፍና ንግደቱ ሕዝቡን አሰልችቶታል፣ የሚያስፈልገው ጉብኝቱ ሳይሆን ቤቶችና መንገዶች በሚገባ መገንባት ነው ብሎ የመንግስት መስተዳዳድር የሚከተለው የቤቶችና የመንገድ ግንባታ እቅድ መተቸቱ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ህዝብም አለ ፈቃድና ሕግ አለ መስተዳድር መሪነት በሕገ ወጥ መንገድ ቤቶችን ከመገንባት መቆጠበ ይኖርበታል። አንዱ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ እንዲስፋፋ የሚያደርገውም በሕገ ወጥ የመንገዶችና የቤቶች ግንባታ ነው። ሕግ አለ ማክበር የገዛ እራስ ሕይወትና የሌላው ሕይወት የብዙ ሕጻናት ሕይወት ለአደጋ ማጋለጥ ይሆናል። ስለዚህ ሕግ የማክበሩ ባህል እንዲስፋፋ አደራ በማለት የጋና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያስተላለፈው መግለጫ ማጠቃለሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
All the contents on this site are copyrighted ©.