2015-06-09 18:44:00

የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወትሮ እንደሚያደርጉት ትናትናም በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኙ ምእመናን ጋ አብረው መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል። ቅድስነታቸው ትናትና ከምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበ ግዜ ከትናትና ወድያ በቦዝንያ ሄርጾጎቪና ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስታወስ በቦዝንያ ሄርጾጎቪና በሰራየቮ ሐዋርያዊ ጉብኝት ያካሄድኩበት ምክንያት ሰላምን ለማበረታታት ሆኖ በዚሁ ክልል የሚኖሩ የተለያዩ ብሔር ብሔረ ሰቦች እና ህዝቦች በሰላም አብረው እንዲኖሩ ድጋፍ ለመስጠት ነው በማለት ለምእመናን ገልጾውላቸዋል።

ይህን ካሉ በኃላ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በበርካታ ሀገራት የሚከበረውን ስጋሁ ወደሙ ለክርቶስ የአስተንትኖ ማእከል በማድረግ ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ ግዜ እኔ ከሰማየ ሰማያት የወረደ የሕይወት ዳቦ ነኝ እና ይህን ዳቦ የበላ ለዘለዓለም ይኖራል፡ እንዲሁም የሰብአውነት ድኅነት ስለ ሆነ ምእመናን ተስሳታፊ እንዲሆኑ ተጠርተዋል ብለዋል።

ቅዱስ ቁርባን ስንቀበል የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት አጋር መሆናችን ያመለክታል ያሉት ቅድስነታቸው ፡ ከሱ ጋር ሕብረት እንፈጥራለን ማለት እንደሆነም በማያያዝ አስገንዝበዋል።

የተወደዳችሁ ህዝበ ክርስትያን እንግዲህ ቅዱስ ቁርባን ፍቅርና ምሕረት ማለት እንደሆነ የሕይወታችን አንዋንዋር ዘይቤ ቀያሪ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ካሉ በኃላ በሚስጢረ ስጋው እና በደሙ የሚመግበን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለታዊ ሕይወታችን የሚገናኘን ነው እኮ ብለዋል ቅድስነታቸው።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለቤተ ክርስትያን የሕይወት ምንጭ የሆነውን ስጋሁ ወደሙ የሚቀበል ክርስትያን ዕለታዊ ምግብ ላጡ ሰዎች ቸል ለማለት አይችልም ብለዋል።

ባለፈው ቅዳሜ በሳርየቮ ወደ ካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ተመልሰው ለዘመናት የኤውሮጳ ኢየሩሳሌም ትባል የነበረችው እና የተለያዩ ብሔር ብሔረ ሰቦች በሰላም ይኖሩባት የነበሩ ሳራየቮ ባለፈው ቅርብ ግዝያት የጦርነት እና የጥፋት ምልክት መሆንዋ አስታውሰው አሁን የዕርቅ እና የሰላም ሂደት እየተካሄደባት እንደሆነ ተናግረዋል።

ቅዳሜ ዕለት ሰራየቮ ላይ ያካሄድኩት ሐዋርያዊ ጉብኝትም የዕርቅ እና የሰላም ሂደቱን ለማበረታታት በማሰብ ነው ካሉ በኃላ ሂደቱ ከባድ ቢሆንም ተስፋ ሰጪ ሆኖ እንዳገኙት በማያያዝ አስገንበዋል።

የተለያዩ ሃይማኖቶች ተከታዮች ያደረጉላቸው ደማቅ አቀባበልም በእጅጉ እንደተደሰቱ ጠቁመው እና አመስግነው የተሰካ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነበር ሲሉ ገልጸውታል።

እግዚአብሔር ሳረየቮ ቦዝኒያ እና ሄርዞጎቪና ይባርክ ሰላሙ ያውርድ በማለት ከምእመናን ጋር በጋራ ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመዋል። 

በመጨረሻም ፊታችን ዓርብ የቅዱስ ልብ ክብረ በዓል እና ዓለም አቀፍ ጸረ ለአቅመ አዳም እና ሔዋን ያልደረሱ ስራ ተስታውሶ እንደሚውል አስታውሰው ለምእመናን ሰናይ ቀን ተመኝተው እና ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።

ይህ በዚህ እናዳለ ሆኖ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና ከቅትር በኃላ የአርጀንቲና መራሂተ መንግስት ፕረሲዳንት ክሪስቲና ፈርናንደዝ ደ ኪርሽነር በቫቲካን ሐዋርያው አዳራሽ ተቀብለው አነጋግረዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.