2015-06-08 16:33:00

ናይጀሪያ፦ የሰብአዊ መብትና ክብር ረጋጣ አሳሳቢነት


እ.ኤ.አ. ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በናይጀሪያ ምስራቃዊ ክልል በምትገኘው በዮላ ከተማ ባለው የገበያ ሥፍራ በተጣለው የአጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ሳቢያ ከሰላሳ በላይ የሚገመቱ ዜጎች ለሞት መዳረጋቸው ሲገለጥ፣ የክልሉ ባለ ሥልጣናት የሸበራው ጥቃት ተጠያቂው እስላማዊው አክራሪው ቦኮ ሃራም ነው ሲሉ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉም በናይጀሪያ አሸባሪው ኃይል ብቻ ሳይሆን የመንግሥት ወታደሮች ጭምር ተጠያቂ የሚያስብላቸው የሰባአዊ መብትና ክብር ረገጣ ድርጊት በስፋታ እንደሚታይ ሲያመለክት፣ ስለ ጉዳዩ በተመለከተም ለኢጣሊያ ኮረረ ደላ ሰራ ለተሰየመው ዕለታዊ ጋዜጣ ልኡክ ጋዜጠኛ ማሲሞ አልበሪዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በናይጀሪያ የመንግሥት ወታደሮችና የክልሉ ባለ ሥልጣናትና የመንግሥት አካላት ጸረ ሽበራ በሚል ምክንያት የሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ ሲፈጽሙ ይታያል፣ በአንዳንድ ቦኮ ሃራም በሚቆጣጠረው ክልል አሰቃቂ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ሲፈጽም እንደሚታይና፣ በአሸባሪው ኃይል ቁጥጥር ሥር የነበሩት ከተሞች በአገሪቱ የመከላከያ ኃይል አባላት ነጻ እንደወጡም የመንግሥት ወታደሮች የአሸባሪያን ተባባሪዎች በሚል ክስ ተጠርጠሪዎች ናቸው በሚሉዋቸው የክልሉ ነዋሪው ሕዝብ ለስቃይ እንደሚዳርጉ ገልጠዋል።

አሸባሪው ኃይል ከእድሜ በታች የሆኑትን ዜጎች ለሸባራ ተግባር መገልገያ መሣርያ ያንደሚያውላቸውና፣ ከእድሜ በታች የሆኑት ሴቶች ደግሞ ለፍትወት ሥጋ መገልገያ መሣርያ በማድረግ ለአዲስ ባርነት አጋልጧችዋል። ተሰውረው የቀሩት የሚጠለፉት የደረሱበትና የገቡበት ጨርሶ የማይታወቅ የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር ብዛት ከፍ እያለ ነው። ይኽ ደግሞ በአሸባሪዎችም ሆነ በአገሪቱ መደበኛ ሠራዊትና የጸጥታው አስከባሪው የፖሊስ ኃይል አማካኝነት ጭምር የሚፈጸም ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው ብለዋል።

አዲሱ የናይጀሪያው መንግሥት ተስፋ የተደረገባቸው መርሃ ግብሮችን በዝርዝር ቢያቀርብም። የፖለቲካ አካላት ቃል የመግባቱ ሁኔታ የተለመደ ጉዳይ ነው። የፖለቲካ አካላት ሁሉም የሚገቡት ቃል ሥፍር ቁጥር የለውም። የገቡትን ቃል እግብር ላይ ሲያውሉ አይታይም። ናይጀሪያ ሃብታም አገር ነች የሕዝቡ ኑሮ የስካንዲናቪያን አገሮች ጋር የሚመጣጠን የሕይወት ደረጃ ለማለት ባልደፍርን እንደ ማንኛው የበለጸገ አገር የኑሮ ደረጃ ሊኖረው የሚችልበት አገር ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.