2015-06-03 16:26:00

የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት


የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የሊንጋየን ዶጉፓን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሶክራተስ ቪለጋስ ከመላ የፊሊፒንስ ሰበካዎች የተወጣጡ ስድስት ሺሕ ተጋባእያን ያሳተፈው እ.ኤ.አ. ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ብሔራዊ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ዓውደ ጉባኤ መክፈቻ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦ ትዕቢትና እራስ ወዳድነት ክርስቲያን መንግስተ ሰማይ እንዳይገባ የሚያግዱ ሁለት ኃጢአቶች ናቸው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ገዛ እራሱ አሳልፎ የማይሰጥ ገዛ እራስ ከእግዚአብሔር ያርቃል

ትዕቢተኛ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ሊያውቅ አይችልም። በገዛ እራሱና ለእኔ ባይነት የተሞላ እኔ ለገዛ እራሴ በቂ ነኝ ባይ ትዕቢተኛ ከእግዚአብሔር ጋር አለኝ የሚለው ግኑኝነት እውነተኛ ግኑኝነት አይደለም። የሚኖረው ግኑኝነቱ ፈጽሞ እውነተኛ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ይኽ ሰው ገዛ እራሱን እንደ እግዚአብሔር ይመለከታልና። ትህትና ከደግነትና ከየዋህነት ጋር የተቆራኘ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ቪለጋስ ባሰሙት ስብከት ገልጠው፣ ገዛ እርሱን ስለ ሌላው አሳልፎ የማይሰጥ ከእግዚአብሔር ይርቃል። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር እንቀርብ ዘንድ ሁላችን ሌሌላው ቅርብ መሆን ከሌላው ጋር ያለንን ተካፍሎ መኖር፣ ስለ ሌላው መቆርቆር ለድኻውና ለተናቀው ለተነጠለው ቅርብ መሆን ይገባናል። ይኸንን ለማድረግ የሚያስችለውም ገዛ እራሱን ዝቅ በማድረግ እኛን ለማዳን ወደ እኛ የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ ያደረገውን ለማድረግ አንፍራ ይኽ መንገድ ብቻ ነው ወደ እውንተኛው ደስታ የሚመራን። እርሱ ያደረገውን ለማድረግ የምንፈራ ከሆን ክርስቲያን ለመሆናችን ያጠራጥራል እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማእከል ድኻው ነው

ብፁዕ አቡነ ቪለጋስ የዓውደ ጉባኤው ዋና ርእስ፣ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማእከል ድኻው ኅብረተሰብ ነው የሚለውን ጠቅሰው በፊሊፒንስ ቃለ ወንጌል የገባበት ዝክረ አምስት መቶኛው ዓመት ምክንያት የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ካወጁት የእምነት አመት እንዲሁም ዝክረ 50 ዓመት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ምክንያት ያነቃቃው መንፈሳዊ መርሃ ግብር የቤተ ክርስቲያን አባላት የአስፍሆተ ወንጌል መሣሪያ መሆናቸው የሚያነቃቃ መሆኑ ገልጠው፣ ቃል ወንጌል ደርሶናልና እኛም በተራችን ቃለ ወንጌልን እናድርስ የሚል መሆኑ አብራርተው ቃሉ የተቀበለ የተቀበለውን ቃል ያደርስ ዘንድ ክርስቲያናዊ ጥሪ አለበት እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አመለከተ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.