2015-06-01 17:01:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ገና መድኃኒት ባልተገኘለት በሽታ ለተጠቁት ሕፃናት፦ የሕይወት ጀግኖች ናችሁ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ኡኒታልሲ ህሙማንን የሚንከባከብና ወደ ተለያዩ ቅዱሳት ሥፍራዎች የሚፈጽሙት መንፈሳዊ ንግደት የሚንከባከበው የኢጣሊያ ክርስቲያን የበጎ ፈቃድ ማኅበር የተሸኑትን ገና መድኃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተጠቁት 20 ህሙማን ሕጻናትና ወላጆቻቸውና ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ ገለጡ።

እነዚህን ሕፃናት አንዳንዶቹ ሲወለዱ ጤናማ የነበሩ ከተወለዱ በኋላ ገና መድሃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተጠቁ። አንዳንዶቹ ደግሞ ገና በእናት ማሕፀን እያሉ ገና መድሃኒት ያልተገኘለት በሽታ እንዳለባቸው በሓኪሞች የተገለጠ ሆኖ እያለ ወላጆቻቸው ጽንስ ከማስወረድ ለአንድ ቀን ላንድ ሰዓት ለንዲት ደቂቃም ይሁን የሕይወት ባህል መመስከር፣ እያንዳንዱ የሚወለደው ሰው የሚኖረው የሕይወት ዘመኑ እንዲት ደቂቃም ትሁን ማክበር የላቀ መሆኑ በመታመን ጽንስ ማስወረድ እንቢ በማለት ባሳዩት ጽኑ እምነት የላቀ መሆኑ የገለጡ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. ተመሳሳይ ግኑኝነት ማከናወናቸው ያስታወሱት ልእክት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ አክለው አንዳንዶቹ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው በሰማይ ቤት ተወልደዋል እንዳንዶቹ ደግሞ ገና አሁንም በሕይወት እንዳሉ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባሰሙት ቃል አስታውሰው፣ ጌታ ሆይ ሕፃናት ለምን ይሰቃያሉ? ልክ እንደ የቅድስት ሥላሴ የቅዱስ ቁርባን ምሥጢር መልስና ትንተና የለንም። ለእግዚአብሔር መጋረጥ አንፍራ፣ ምንም መልስ ሳናገኝ እንቀር ይሆናል፣ ነገር ግን ከእርሱ ጋር የምታካሄደው የመልስ ፍለጋ ግጥምያ በአባትነቱ ጥበቃ ሥር የሚከናወን ነውና አባታዊ ፍቅሩ የሚያጋጥመን ችግር ለመሻገር የሚያበቃ ኃይሉና ጸጋው ያድለናል። ኃይላችን እግዚአብሔርና በእግዚአብሔር ዘንድ ነው። በእርሱ አባታዊ እይታ ዘንድ ያለ ነው። የእግዚአብሔር አፍቃሪው አይን በእኛ ላይ ነው።

በእናንተ ፊት ለመናገር በእውነቱ ቃላቶች ያጥረኛል። እፊታችሁ ሆኜ በእናንተ ላይ የሚግለጠው ኃይል አደንቃለሁኝ አስተነትናለሁኝ፣ ብርታታችሁና ጽናታችሁ አደንቃለሁኝ፣ ጽንስ በማስወረድ የሚፈታ ችግር የለም። ጽንስ ማስወረድ የወንጀል ቡድኖች ደንብ ነው። ሕይወት ለሞት መዳረግ የወንጀል ቡድኖች መመሪያ ነው።

ሁሌ ስለ እናንተ እጸልያለሁ በጸሎቴ አስባችኋለሁ፣ የብርታትና የጽናት ጎዳና የመስቀል ጎዳና ነው። ስለ ትንሣኤ የምትሰጡት ምስክርነት ከልብ አመሰግናችኋለሁ፣ የእናንተ ምስክርነት ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን ጭምር ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን የሞት ባህል እንቃወም በማለት የለገሱት ቃል ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.