2015-06-01 16:52:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ኢየሱስ ነጻነታችንና ብቸኛው የነጻነታችን ክንፍ እርሱ ነው


እ.ኤ.አ. ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት የአሕዛብ ቅጥር ግቢ በሚል ርእስ ሥር የሚያካሄደው ባህላዊ ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ስነ ጥበባዊ የውይይት ዓውደ ጉባኤ ጋር በማያያዝ ለየት ባለ መልኩ የወጣቶች ቅጥር ግቢ በሚል ሥያሜ በየዓመቱ ወጣቶች ጉዳይ ላይ በማነጣጠር የሚያካሂደው ባህላዊ ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ሥነ ጥበባዊ ዓውደ ጉባኤ ምክንያት በማኅበራዊ ሰብአዊ ኤኮኖሚያዊ ችግር የተጠቁትን ታዳጊ ወጣቶች የሕፃናት ባቡር በተሰኘ ርእስ ሥር ከቅዱስ አባታችን ጋር በማገናኘት መከናወኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ገልጠው፣ በዚህ የታዳጊ ወጣቶች ባቡር በተሰኘው መርሃ ግብር የኢጣሊያ የባቡር የመጓጓዣ ባለሥልጣን ወጣቶችን በአገረ ቫቲካን በሚገኘው የባቡር ጣቢይ ደረስ በማጓጓዝ መተባበሩ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እነዚህ በተለያየ ወንጀል ምክንያት ወላጆቻቸው በወህኒ ቤት የሚገኙባቸው በተለያየ ማኅበራዊና ሰብአዊ ችግር የተጠቁት ታዳጊ ወጣቶችን በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው ከተደቀነብን ችግር ማዶ እንብረር በችግር ታጥረን የወቅቱና መጻኢውን ሕይወታችንን አናጨልም በማለት ከሮማ ከቺቪታቸኪያ ከላቲና ከባሪና ከትራኒ የመጡትን በተለያየ ችግር ለተጠቁት ሕፃናት ምዕዳን በማቅርብ፣ ከታዳጊ ወጣቶች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በመስጠት በመወያይት በለገሱት ምዕዳን አክለው በህልም መብረር፣ በከበበን ችግር ሳንታጠር ካለብን ችግር ማዶ እንመልከት እንዳሉ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

በራዳማው ልብ ማለም የተሳነው ነው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በወህኒ ቤት ማለም ወደ ላይ የመብረር ህልም የማይቻል ነው የሚል ቃል ማእከል ያደረገ ከታዳጊ ወጣቶች አንዱ ላቀረበው ሃሳብ ካዳመጡ በኋላ፣ ታዳጊ ወጣቶችን አትፍሩ ወደ ላይ ብረሩ በዕለታዊ ችግር ሳትሰጥሙ ወደ ፊት አቅኑ። ወደ ላይ አቅኑ። ወደ ላይ የመብረር ህልም በምንም ነገር ሊሰናከል እንደማይችል ገልጠው፣ የማያልም ወደ ላይ የማያቀና ሕይወት መልካምነት የተሳነው ይሆናል። ደስታ አልቦ ይሆናል፣ እናንተ ግን ባለባችሁ ችግር ሁሉ ሳትፈሩ ወደ ላይ ብረሩ። አልቦ ህልም ሕይወት የተዘጋ ልብ ያለው ይሆናል፣ የድንጋይ ልብ አይኑረን አደራ እንዳሉ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

ኢየሱስ እንበር ዘንድ ይደግፈናል

ስታልም ሁሉ የምትፈልገው ነገር ታልማለህ፣ ነገር ግን ቀዝቃዛና ድንጋያማ ልብ የማያልም ልብ ነው ሲል አንድ ታዳጊ ወጣት ላሰማው ቃልና  የተናገረውን ጠቅሰው የእግዚአብሔርና የኢየሱስ ቃል የማናዳምጥ ስንሆን፣ መጸለይ አናውቅም፣ አለ ክንፍ መብረር አይቻልም፣ ጸሎትና ቃለ እግዚአብሔር ክንፍ ይሆነናል። ስለዚህ ጸልዩ ቃለ እግዚአብሔር አፍቅሩ አደራ።

የፍትሕና የሓቅ ፍሬ

ታዳጊ ወጣቶች ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የፍትህና የሐቅ ፍሬ በሚል ስያሜ የተለያዩ ገጸ በረከቶች በማቅረብ ለቅዱስነታቸው ያላቸው ፍቅር ሲያስተጋቡ። ቅዱስ አባታችን ኢየሱስ የሐጢአተኞች ጓደኛ፣ ሐጢአተኞች በሽተኞችን የሚፈልግ ነው ብለው በሞትህና በትንሣኤህ ሰላምህን ስጠን ከሐጢአት አንጻን። የፍቅር የፍትሕና የሐቅ ፍሬ እናቀርብልሃለን በሚል ታዳጊ ወጣቶች ባቀረቡት ጸሎት የተካሄደው ግኑኝነት መጠናቀቁ ደ ካሮሊስ ገለጡ።
All the contents on this site are copyrighted ©.