2015-05-25 16:52:00

ኬንያ፦ የብፅዕና አዋጅ


እ.ኤ.አ. በ1900 ዓመታት መግቢያ በወንጌላዊ ልእኩነት በኬንያ ያገለገሉት በአገሪቱ ሕዝብ መኅሪ እናት በሚል መጠሪያ የሚታወቁት የኮንሶላታ ልኡካነ ወንጌል ደናግል ማኅበር አባል ገና በ 39 ዓመተ እድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት እናቴ ኢረነ ስተፋኒ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውሳኔ መሠረት እ.ኤ.አ. ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. የዳር ኤስ ሳላም ሊቀ ጳጳሳት የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፖሊካርፖ ፐንጎ በኒፐፐ ከተማ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ብፅዕና እንደታወጀላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፅዕት ኢረነ በኢጣሊያ ብረሻ ክፍለ ሃገር በ 1891 ዓ.ም. ተወልደው በ20 ዓመት እድሜያቸው የኮንሶላታ ልኡካነ ወንጌል ደናግል ማኅበር ገብተው በ 23 ዓመት ዕድሜያቸው ወደ ከንያ ተልከው በወታደራዊ ሆስፒታል ለሚታከሙት ህሙማን የአንደኛው ዓለም ጦርነት ቁስለኞች በፍቅር በትህትና በነበራቸው የህክምና ሙያ አማካኝነት በማገልገል በማጽናናት የሚሰዋ ፍቅር የመሰከሩ መሆናቸው የታሪክ ማኅደራቸው ይመሰክራል።

በ 1920 ዓ.ም. በገኮንዲ ሰበካ በሚገኘት ትምህርት ቤት አስተማሪ በመሆን የትምህርት ዕድል ላልነበራቸው ከትምህርት ገበታ ለተለዩትና ለተነጠሉት ወጣቶች በመፈለግ ወደ ትምህርት ገበታ በማቅረብ ሙሉ ሰባአዊና ክርስቲያንዊ ድጋፍ በማቅረብ ያገለገሉ፣ ሺሕ ሕይወት ቢኖረኝ ጌታ ሆይ ሺውን ሕይወት ላንተ ይሉ የነበሩ በክልሉ ተከስቶ በነበረው ወረርሽኝ በሽታ የተጠቃው ሕዝብ በማገልገል ላይ እያሉ በበሽታው ተለክፈው የታመመውን በመደገፍ ሙሉ በሙሉ የስቃዩ ተካፋይ በመሆን ላገለገሉት ሕዝብ የሆነው ሁሉ በሆኑ ስለ ፍቅር ሕይወታቸው ለሕዝበ እግዚአብሔር የሰዉ መሆናቸው የታሪክ ማህደራቸው የጠቀውሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ለፍቅር ስለ ፍቅር በፍቅር ሕይወታቸው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 26 ቀን 1930 ዓ.ም. በ 39 ዓመት እድሚያቸው  በመሰዋት በሰማያዊ ቤተ የተወለዱ የክልሉ ሕዝብ የምኅረት እናት በማለት ይገልጣቸው እንደነበርም አስታውቀዋል።

ይኸንን የእግዚአብሔር መሃሪነትና ርህራሄ በቃልና በሕይወት የሰጡት ምስክርነት ዛሬ በከንያ አገልግሎት ለሚሰጡት የማኅበሩ ደናግል አባላት በክልሉ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አብነት መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።    








All the contents on this site are copyrighted ©.