2015-05-20 16:42:00

የባኩ ጉባኤ፦ ቅድስት መንበር በእግዚአብሔር ስም ቅትለት መፈጸም የእግዚአብሔር ስም ማርከስ ማለት ነው


በአዘርበጃን ርእሰ ከተማ ባኩ የተባበሩት መንግሥታት የኤውሮጳ ኅብረት ምክር ቤት በጋራ ያሰናዱት ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የተለያዩ ባህሎች የጋራው ጉባኤ የአዘርበጃን ርእሰ ብሔር አሊየቭ በማሳተፍ እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይኽ በሕዝቦችና በባህሎች መካከል መቀራረብና መተዋወቅ እንዲኖር የሚያነቃቃው ለዚህ የሚበጅ መሠረተ ሃሳብ የሚያቀርበው ጉባኤ ዘንድሮ ባህልና ተቀባይነት ያለው ለድኅረ 2015 ዓ.ም. የልማት እቀድ በሚል ርእስ ሥር የተመራ መሆኑ በጉባኤው ቅድስት መንበርን ወክለው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ መልኮር ሳንቸዝ ደ ቶቻ ይ አላመዳ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።

በተለያዩ ባህሎች መካከል የሚደረገው ግኑኝነት ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ጳጳሳዊ ምክር ቤቶችዋ አማካኝነት የምታነቃቃው ጉዳይ ነው። ባህል የማገናኛ መድረክ ለውይይት ምክንያት ጭምር ነው። ስለዚህ ባህል በመሠረቱ ለመለያየት ለመራራቅ ወይንም በሕዝቦች መካከል ያለው ልዩነት የሚያበክር አይደለም፣ ስለዚህ በባህሎች መካከል መቀራረብና መወያየት የሚል ጥሪ በእያንዳንዱ ባህል ዘንድ ያለ እምቅ ኃይል ነው። ሙዚቃ ስፖርት ስነ ምርምር ውበት ስነ ጥበብ ኵላዊ ቋንቋዎች ናቸው። ይኸ በትክክል ካልተረዳን ለመከፋፈል ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።

በጉባኤው ይላሉ ብፁዕነታቸው፣ ቅድስት መንበር ባህሎች በተነጥሎ የሚኖሩ የሚለያዩ አይደሉም፣ ብሔራዊ መለያ መከላከል ማቀብ ማለት ባህልን መነጠል ከሌላው ጋር ምንም ዓይነት ግኑንነት አይኑር የሚል ማለት እንዳልሆነ፣ በሁለተኛው ደረጃ በእያንዳንዱ በተለያየው ባህል በማንኛውም ዓይነት ርእዮተ ዓለምም ይሁን ሃይማኖት ነክ ጥያቄዎች የሰው ልጅ ሃይማኖተኛ መሆኑ ጋር ተገናኝ የጋራ ጥያቄዎች አሉ፣ ከየት ወዴት የሚል ጥያቄ፣ አፈጣጠር የፍጥረት ጅማሬ ጉዳይ በተመለከተ በጠቅላላ ኅላዌና ኅልውና ዕጣ ፈንታ የሚመለከቱ ጥያቄዎች አሉ፣ እንዲህ ባለ መልኩ የባህሎች መፈሳዊ ገጽታ ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ሓሳብ ማቅረቧ ገልጠው በሦስተኛው ደረጃ የሁሉም አገሮች መንግሥታት በተለያዩ ሁሉም ሃይማኖቶች መካከል ውይይት ያለው አስፈላጊነት እንዲያስተውሉና እንዲያነቃቁ አደራ እንዳለች ገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ደጋግመው በእግዚአብሔር ስም ቅትለትና ግድያ እግዚአብሔርን ማርከስ ነው በማለት የገለጡት ሃሳብ ብፁዕነታቸው አስታውሰው፣ በሃይማኖት ስም ግድያ ጸረ ሃይማኖት ነው። ሃሳብ የመግለጥ ነጻነት በሕግ የተመራ መሆን አለበት፣ እንዲህ ካልሆነ የአንዱ ሃሳብ መግለጥ ለሌላው ጥቃት ሊሆን ይችላል፣ የሌላውን ሰብአዊ ሃይማኖታዊ ክብር ማክበር ያስፈልጋል፣ የሰው ልጅ ሃይማኖት ማክበር ያስፍለጋል፣ ስለዚህ ቅድስት መንበር በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ እነዚህ ነጥቦች ማእከል ያደረገ መልእክት ማቅረቧ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.