2015-05-18 12:52:00

ር.ሊ.ጳ. ፍርናንቸስኮስ፤- የመጀመርያ የመግባብያና የግኑኝነት ትምህርት ቤት ቤተሰብ ነው!


ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ቀን ትናንትና ለአርባ ዘጠነኛ ጊዜ በመላው ዓለም ተከብረዋል፣ባለፉት ዝግጅቶቻችን እንደተከታተላችሁት እ.አ.አ ጥር 23 ቀን 2015 ዓም ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ “ከሌሎች ጋር ለመግባባት የምንማርበት የመጀመርያው ትምህርት ቤት ቤተሰብ ነው” በሚል ርእስ ይህንን ቀን የሚመለከት መልእክት እንደጻፉ የሚታወስ ነው፣

በተለይ በወላጅ እናትና በሕጻንዋ መካከል ያለው ግኑኝነት ገና በማኅጸንዋ ውስጥ እያለ ይህንን የመግባባትና የመወያየት ባህርይ እንዳለ እንመለከታለን፣ የሕይወታችን የመጀመርያ ተመኵሮ የምናገኘውም ከዚሁ የእናትና የሕጻንዋ ግኑኝነት ነው፣ ይህም ሁላችንን አንድ ያደርጋል፣ ኣንድ ዓይነት ተመኵሮ አንድ ዓይነት ትምህርት እናገኛለን ማለት ነው፣ ሲሉ በሰፊው በጻፉት መልእክታቸው ሁሉም መቶ ከመቶ ፍጹም እንዳልሆነም መግንዘብ እንደሚያስፈልግ “ፍጹም ቤተሰብ የሚባል ስሌለ ከሚያጋጥሙን ግድፈቶች መፍራት የለብንም እንድያው አንዳንዴ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሲበዙ ግፋ ብሎ ለግጭትና ንትርክ ስንጋለጥ መፍራት የለብንም እነኚህን ነገሮች ፊት ለፊት በመጋፈጥ ገንቢ በመሆነ መንገድ መማር አለብን፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ የመግባባትና የመገናኘት ዋና ፈውስ ይቅር ባይነት ነው በአንድ የመግባባትና የመገናኘት ሂደት ሌላው የቤተሰብ ትምህርትም ብቅ ይላል፣ ይቅር ማለት ምሕረት መስጠት የምንማረውም በቤተሰብ ውስጥ ነው ምክንያቱም ወደር የለሽ የወላጆች የወንድማሞችና የእትማሞች እንዲሁም የአያቶች ፍቅር የሚገኘው በቤተሰብ ነውና፣ ሌላው የዘመናችን የቤተሰብ ነቀርሳ ለማለት የምንችለው አስቸጋሪ ጉዳይ የዘመናዊ ተክኖሎጂና መገናኛ ብዙኃን ነው፣ በቤተሰብ ውስጥ እያንዳንዱ የገዛ ራሱ ዓለም እስከ መፍጠር የሚያደርሱ የተለያዩ የተክኖሎጂ ውጤቶች ሰዎችን ሲነጣጥሉ ይታያሉ፣ ስለዚህ ይላሉ ቅዱስነታቸው፤ ስለዚህ ተክኖሎጂን ፈጠርነው እንጂ አልፈጠረንም፣ ልንመራው እንጂ በተክኖሎጂ መመራት የለብንም ሲሉ አስጠንቅቀዋል፣

ሌላው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን ችግር ስለተለያዩ ፖሎቲካዊ ዝንባሌዎችና ርእዮተ ዓለሞች ደጋግመው የሚያቀርብዋቸው ጉዳዮች አንዳንዴ በቤተሰብ ውስጥ የፖሎቲካና የርእዮተ ዓለም ክርክርና ውግያ ሊለኩሱ ይችላሉ፣ የባሰው ደግሞ ቤተሰብን እንደ አንድ የሚሸጥ የሚለወጥ ዕቃ የተለያዩ ሓሳቦች በማቅረብ በተለያዩ ፖሎቲካዊ ርእዮተ ዓለሞች እየቀቡት እንደፍላጐት የምትለዋውጠው ዓይነት አድርገው ያቀርባሉ፣ ነገር ግን ሕይወት በሥነ ኃሳብ ብቻ የሚመራ የርእዮተ ዓለም ጉዳይ ሳይሆን በተለይ በቤተሰብ በተጨባጭ በአካል በየሁኔታው ሁነኛ እርምጃ በመውሰድ በቍምነገር የሚኖር መሥዋዕት የሚከፈልበት እንዲሁም ከሌሎች ስለተቀበሉት ፍቅርና ለሌሎች ስለሚያበረክቱት ፍቅር የምንመሰክርበት ቦታ ነው፣ በባልና በሚስት መካከል ከሰርጋቸው ጀምሮ እያበበ የሚመጣው ፍቅር የመተሳሰቡና የመረዳዳቱ እንዲሁም የዚሁ ፍቅር ፍሬ በሆኑ ልጆቻቸውና በወላጆች መካከል ያለው ፍቅር ሃብትና መልካምነት መመስከር ነው፣ ሲሉ ቤተሰብን እንደዓይናችን ብለን መጠበቅ እንዳለብን ያስተማሩ ቅዱስነታቸው ወደ ዋናው አርእስት በመመለስም ይህንን ከቤተሰብ የምናገኘው የመግባባትና የመገናኘት ትምህርት በታሪክ ስላለፈው ከመናገርና ከመከላከል ይልቅ የበለጠ መጻኢ ለመገንባት በየዕለቱ በሚያጋጥሙን መስኮች በትዕግሥትና በመተማመን እንሥራ ሲሉ መልእክታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.