2015-05-15 16:41:00

ፍትህና ሰላም


የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የልማትና የማኅበራዊ አገልግሎት ማኅበራት የሚያቅፈው እ.ኤ.አ. በ 1950 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ የተመሠረተ ካሪታስ ኢንተርናዚናሊስ ማኅበር እ.ኤ.አ. ከግንቦት 12 ቀን እስከ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. አንድ ሰብአዊ ቤተሰብ ተፈጥሮን መንከባከብ በሚል ርእስ ሥር 20ኛው ጠቅላይ ጉባኤ እያካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ በጉባኤው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ቱርክሶን

እ.ኤ.አ. የግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጉብኤው ውሎው ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በቅርቡ ታትሞ በይፋ ለንባብ ይበቃል ተብሎ የሚነገርለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የደረሱት ሥነ ምኅዳር ላይ ያተኮረው ዓዋዲ መልእክት ማእከል በማድረግ፣ ቅዱስነታቸው ሰብአዊ ሥነ ምኅዳርና የተፈጥሮ ሥነ ምኅዳር በተመለከተ ከዚህ ቀደም በተለያየ ወቅት የሚገልጡት መሠረተ ሃሳብ አመክንዮአዊ ቅደም ተከተል በማስያዝ በጥልቀት የሚያብራሩበት የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት አዘል ሰነድ ነው። ስለዚህ በአዋዲው መልእክት ለአንድ ጤናማ ሥነ ምህዳር፣ ላንድ ጤናማ ሥነ ሰብእና ተፈጥሮ መንከባከብ ላይ ያነጣጠረ፣ ተፈጥሮ መንከባከብና ሰብአዊ ሕይወት መንከባከብ ተያይዘው የሚሄዱ ናቸው የሚል መሠረታዊ ሃሳብ የሚያቀርብ ሰነድ ነው። የተለያዩ ምሁራንና የሥነ ምንርምር ሊቃውንት የቲዮሎጊያና የፍልስፍና ሊቃውንት በጠቅላላ ምሁራን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥነ ምኅዳር ዙሪያ የሚደርሱት ዓዋዲ መልእክት በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸው ይሰማል፣ ዓዋዲው መልእክት ለሁሉና የሁሉም እንደሚሆን አያጠራጥርም። ወደ ኋላ መለስ ብለን ሥነ ምኅዳር ነክ ጳውሎስ ስድስተኛ፣ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሥነ ምኅዳራዊ ለውጥ በሚል ሥነ ሃሳብ ላይ በማተኵር የገለጡት የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት እንድናስታውስ የሚደግፍ ሰነድም ነው ካሉ በኋላ፣ መጽሓፍ ቅዱስ መሬት ገነት የአታክልት ሥፍራ በማለት ይገልጠዋል፣ ስለዚህ ሥነ ምኅዳር ሲባል የተፈጥሮ ውበትና ውህበት መንከባከብ ማለት ነው። ይኸንን የአታክልት ሥፍራ ምድረ በዳ ላለ ማድረግ መጠንቀቅ ይኖርብናል ብለዋል።

ተፈጥሮ መንከባከብ ሰብአዊነት መንከባከብ ማለት ነው። ስለዚህ ሁለቱ በመነጣጠል አንዱን ብቻ እግብር ላይ ማዋል አይቻልም፣ አለ ሰብአዊነት ተፈጥሮን ማክበር አይቻልም አለ ተፈጥሮ ማክበር ሰብአዊነት ማክበር እንደማይቻል አብራርተው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.