2015-05-15 16:50:00

ብፁዕ አቡነ ሞጋቨሮ፦ ኤውሮጳና ስደተኞች


በኢጣሊያ የባህር በር በኩል ወደ ኤውሮጳ የሚሰደደው ስደተኛ ዜጋ ለመቆጣጠርና ከቀን ወደ ቀን ብዛቱ ከፍ እያለ በመምጣቱ ብቻ ሳይሆን በሜዲትራኒያን የባህር ጉዞ የሚያጋጥመው አሰቃቂው የሞት አደጋ ለመቆጣጠርና የስድተኛው ጽኣት ለመግታት ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ ብሎም በዱብሊን ውል መሠረት ስደተኛው በገባበት አገር ፖለቲካዊም ሆነ ኤኮኖሚያዊ ጥገኝነት ማቅረብ አለበት የሚለው ውሳኔ ካለው የስደተኛው ብዛት አንጻር የስደተኛው ጸአት

ኢጣሊያ ብቻ የሚመለከት አድርጎ መተው እያስከተለው ያለው ችግርና ኢጣሊያ ካለው የስድተስኛው ብዛትም አንጻር ለስደተኛው የተሟላ ተገቢ መስተንግዶ ለመስጠት አዳጋች አየሆነባት በመምጣቱ ምክንያት በተደጋጋሚ ጉዳይ ኤውሮጳዊ መፍትሔ ያሻዋል በማለት የኢጣሊያ መንግሥት ያቀረበው ጥሪና ጥያቄ መሠረት የኤውሮጳ ኅብረት የመሪዎች ምክር ቤትና ቀጥሎም የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ወደ ኢጣሊያ የሚገባው ስደተኛ ለሁሉም የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ማከፋፈል የሚል ኅብረቱ ስደተኞችን የሚያስተናግድበትንና የሚቆጣጠርበትን ያጸደቀው አዲስ የስምምነት እቅድ በማስደገፍ የኢጣሊያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒ. አንጀሊኖ አልፋኖ የዱብሊን ስምምነት ውድቅ የሚያደርግ አዲስ ስምምነት በማለት ሰይመው፣ የዱብሊን ስምምነት ካለው የስደተኛ ጸኣት አንጻር ገቢራዊ አድርጎ ማቀቡ ከጥቅሙ ጉዳዩ የሚያመዝን ይሆናል፣ ኤውሮጳ፣ በጋራ ስደተኞችን በሕገ ወጥ መንገድ ከቦታ ቦታ የሚያንቀሳቅሱትን የወንግጀል ቡዱኖች የሚጠቀሙባቸው ባለ ሞተር ጀልባዎችም ሆነ መርከቦችን ገና ስደተኞችን ከማሳፈራቸው ቀድሞ ለማውደም የወጠው እቅድ ጸረ የወንጀል ቡድኖች ነው፣ በማለት አስተያየት ሲሰጡ፣ ስለ ተደረሰው ስምምነት በኢጣሊያ የማዛራ ደል ቫሎ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ሞጋቨሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦  ስደተኛው በባህር ጉዞ እያለ የሞት አደጋ ገና ሳያጋጥመው የነፍስ አድን ድጋፍ አጠናክሮ ማቅረብ በሕገ ወጥ አሠራር ሰዎችን ከቦታ ቦታ የሚያሸጋግሩትን የወጀል ቡድኖች ብበናት መቆጣጠር፣ ስደተኞችን ለኢጣሊያ ብቻ ሳይተዉ በኤውሮጳ አባል አገሮች ማከፋፈል፤ ተሰዳጁ ሕዝብ ለወንጀል ቡድኖች የገቢ ምንጭ እንዳይሆን ለወንጀል ቡድኖች ወጥመድ እንዳይጋለጥ ሕጋዊ የመግቢያ ሥርዓት መፍጠር ከዚህ ጋር በማያያዝም ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ የሚያጋልጡት ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሔ ማፈላለግ የተሰኙት ሃሳብ ያካተተው ስምምነት የሚደገፍ ነው ነገር ግን አዲሱ ስምምነት በቂ ነው ለማለት አይቻልም ብለዋል።

የስደተኛው ጉዳይ ማኅበራዊ ክስተት በመሆኑም ጉዳዩ ባህላዊ ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ አቀራረብ የሚጠይቅ ነው። የስደተኛው ጸአት ችግር አድርጎ ከሚሰብከው መሠረት አልቦ ፖለቲካዊ ንዝነዛ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት በኤውሮጳ የሚታየው ችግር ስደተኛው የቀሰቀሰው አይደለም፣ ተጨባጩ የስድተኛው ጉዳይ ግምት የማይሰጥ በይሆናል በግምት መናገርና አስተያየት መስጠት መገታት አለበት፣ ምክንያቱም እያንዳንዱ ስደተኛ ቁጥር ሳይሆን ሰው ነው የገዛ እራሱ ታሪክ አለው ብለዋል።

ስደተኛው የሚያጓጉዙት ከሰሜን አፍሪቃ የባህር ክልል የሚነሱትን ባለ ሞተር ጀልባዎችና መርከቦች አስቀድሞ ገና ስደተኞችን ከማሳፈራቸው በፊት ለይቶ ማውደም የሚለው በኤውሮጳው አዲስ ስምምነት ሥር የሠፈረው ሃሳብ ውጤት ይኖረዋል ብሎ ለመናገር ያዳግታል ብለው፣ ወደ አንድ ሉአላዊ አገር የባህር ክልል በመሄድ ጥቃት መሰንዘሩ ብዙ ጠንቅ ይኖረዋል፣ ስለዚህ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ስደተኛው የሚሳፈርባቸው ጀልባዎች ማውደም ለስደት የሚዳርግ ምክንያት መፍትሔ መስጠት ማለት አይደለም። ስለዚህ ስደትና ጸአት እንዳይኖር ከተፈለገ ለስደት የሚዳርግ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።    








All the contents on this site are copyrighted ©.