2015-05-13 16:39:00

ፊረንዘ፦ የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች ሁለተኛው የጋራ በዓል 2015


እ.ኤ.አ. ከግንቦት 15 ቀን እስከ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢጣሊያ ሁለተኛው የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች የጋር በዓል አብረን ወደ ባሻገር እንጓዝ በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ በኢጣሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ድጋፍ አማካኝነት እንደሚካሄድ የቫቲካን ረድዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድራያና ማሶቲ ገልጠው፣ ይኽ የጋራው በዓል በዓለማችን የሚታየው ኃይማኖት መሠረት ያደረገ ግጭትና ውጥረት አክራሪነት አሸባሪነት ጸረ ኃይማኖት መሆኑና ብዙኅነት እሴት እንጂ የግጭት ምክንያት ሊሆን አይችልም የተሰኘው እማኔ በማረጋገጥም፣ በኃይማኖትና በባህል የተለየውን ማጥፋት ጸረ ሰብአዊ መሆኑ ለማስተጋባት ያቀደ በዓል መሆኑ

ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የዚህ በፊረንዘ የሚካሄደው ሁለተኛው በዓል አስተባባሪ ፍራንቸስካ ካማፓና ኮምፓሪኒ ገልጠው፣ በዚህ በዓል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪ ብፁዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ ሁለተኛ በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉዋድ ትዋል፣ የአይሁድ ሃይማኖት መምህር ስታይንሳልትዝ እንዲሁም ከተለያዩ ሃይማኖቶች የተወጣጡ ምሁራን፣ የፖለቲካ አካላት እንደሚሳተፉ ገልጠዋል።

አብረን ወደ ባሻገር እንጓዝ የተሰኘው የዘንድርው በዓል ርእሰ ጉዳይ ካሸባሪነት ካክራሪነት ከኃይማኖት ግጭት ከዘረኝነት፣ ሰው ላደጋ ከሚያጋልጥ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ሁሉ ወዲያ አንመልከት፣ ወዲያ ስንመለከት ሰብአዊነት ጋር እንገናኛለን፣ ምንም’ኳ በባህል በኃይማኖት በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ቢኖርም፣ በሰብአዊነት መሆን ያለው ውሁደት የሚያነቃቃ በዓል ነው ብለዋል።

በኃይማኖቶች መካከል የሚታየው ልዩነት የግጭት ምክንያት ሳይሆን ከላቀው እሴት ጋር ለመገናኘት ውበትን ለማስተንተን የሚያግዝ፣ ሁሉም በጋራ በሰላም ለመኖር እንዲችል የሚደግፍ መሆን አለበት። ስለዚህ ይኽ የፊረንዘ በዓል የኃይማኖቶች ልዩነቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ገልጠው፣ ያለው ልዩነት ለመተዋወቅ ለመቀራረብና ለወንድማማችነት የሚያነቃቃ የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች መለያ ማቀብ ለኃይማኖታዊ ግጭት ምክንያት ሊሆን እንደማይችልና፣ ሁሉም ፍጻሜ ላይ በማተኮር አብሮ ወደ ባሻገር የላቀው ላይ በማተኮር አብረው ለመጓዝ የተጠሩ መሆናቸው የሚያበክር በዓል ነው ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.