2015-05-13 16:42:00

ሚላኖ፦ ለተፋቱት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት


በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ እ.ኤ.አ. ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት በሰበካው የሚገኙት ቃል ኪዳን በማፍረስ ተፋተው ለሚኖሩት ምእመናን ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚከታተል ጽሕፈት ቤት መፈጠሩ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ ገለጡ።

ይኽ የተቋቋመው አዲስ የተፋቱት ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት አገልግሎቱ በይፋ እ.ኤ.አ. መስከረም 8 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀመር መሆኑ የዚሁ ጽሕፈት ቤት ዋና ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ሉካ ብረሳን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ጽሕፈት ቤቱ እንዲቋቋም ያደረገው ምክንያት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጠሩት ቤተሰብ ዙሪያ የመከረው ሲኖዶስና በዚህ ርእስ ዙሪያ መሠረት ገና ሊካሄድ የተጠራው ሲኖዶስ መሆኑ ገልጠዋል።

ለተፋቱት የሚሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንክብካቤ ከፍቅር የመነጨ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሠረት ያደረገ ተግባር መሆኑ ገልጠው፣ ብፁዕ ካርዲናል ስኮላ ከተካሄደው ሲኖዶስ በኋላ በመደጋገም ያሰቡት ብዙ የመከሩበትና የጸለዩበት እቅድ ነው። ምእመን በተለያየ ተጨባጭ ገጠመኝ ሁነት ቢገኝም ቤተ ክርስቲያን የጌታ ምኅረት በማበሰር ቅርብ በመሆን ተገቢ ሕንጸት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት በማቅረብ፣ በመዳን እቅድ የምትሸኝ ነች። ምንም’ኳ ሐጢአተኞች ብንሆንም እግዚአብሔር ዘወትር እኛን ከማፍቀር የማይቦዝን መሆኑ በጥልቀት በማብራራት፣ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ወቅት ምእመናን የሚኖሩት ሕይወት እንዲያጤንና የሚኖረው ሕይወት ለመገንዘብ የሚያበቃው ድጋፍ በማቅረብ እያንዳንዱ ምእመን ዕለት በዕለት ተገቢውን መንገድ ለይቶ ለማወቅ የሚያግዘው ሁሌ ጌታን መከተል ያለው አስፈላጊነት እንዲያስተነትን በመደገፍ ምስጢረ ተክሊል ጸጋ መሆኑ በማስገንዘብ፣ ምሥጢረ ተክሊል በመንከባከብ የላቀው ክብሩ የምታስተጋባበት ጽሕፈት ቤት ነው። ሆኖም ተጨባጩን የምእመናን ሕይወት ግምት የሚሰጥ ነው። ዘወትር በጌታ ፍቅር መኖር ለጌታ ታማኝ ሆኖ ለመኖር የሚደግፍ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚከናወንበት ጽሕፈት ቤት መሆኑ አብራርተው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.