2015-05-11 16:03:00

ብሩንዲ፦ ዓመጽና የመፈናቀል አደጋ


በብሩንዲ ሁለቴ በተከታታይ ርእሰ ብሔር በመሆን ያገለገሉት የርእሰ ብሔር የሥልጣን ዘመናቸው በማጠናቀቅ ላይ የሚገኙት ፒየረ ንኩሩንዚዛ የቡሩንዲ ሕገ-መንግሥት ለሀገር መሪ  የሚሰጠው  ሁለት የሥልጣን ተልእኮ ዘመን ውሳኔ እንዲሁም የአሩሻ የስምምነት ውል በመጣስ ዳግም እ.ኤ.አ. ሰነ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ ለሦስተኛ ጊዜ ተመራጭ ርእስ ብሔር ሆነው እንደሚቀርቡ በሰጡት ውሳኔ ምክንያት በአገሪቱ ዓመጽና ውጥረት መነቃቃቱ ሲገለጥ፣

በአገሪቱ የርእሰ ብሔር ንኪሩንዚዛ ዳግም እጩ ተመራጭ ሆነው እንደሚቀርቡ የሰጡት ውሳኔ የቀሰቀሰወ ሕዝባዊ ዓድማ ለመግታት የአገሪቱ የመከላከያና የጸጥታ አስከባሪ ኃይል በስፋት መሰማራቱ ሲገለጥ፣ በተቀሰቀሰው ዓመጽ 16 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውና ሌሎች ከ 30 ሺሕ በላይ የሚገመቱት የአገሪቱ ዜጎች አገራቸውን ጥለው ወደ ጎረቤት አገሮች መፈናቀላቸው ከአገሪቱ የሚሰራጩ የዜና ምንጮች ይጠቁማሉ።

የፕሬዝደንቱ የሥልጣን ዘመናቸዉ ለሦስተኛ ጊዜ ለማራዘም ያላቸው ፍላጐት የአገሪቱ ሕገ መግንሥት የማያከብር ተግባር ሲሆን፣ በአገሪቱ የተረጋገጠው ጸጥታና መረጋጋት ዳግም ለአደጋ የሚያጋልጥ እንደሚሆን የተለያዩ የአፍሪቃ ፖለቲካ ተንታኞች ሲያመለክቱ፣ በአገሪቱ ተከስቶ ካለው አመጽና ሁከት ወደ ከፋ ደረጃ ሊያዘግም እንደሚችል ካለው ሥጋት አንጻር በአገሪቱ ከዚህ ቀድም የነበረው በታሪክ የሚዘክረው ዳግም ግጭት ዳግም ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት ወደ ጎረቤት አገሮች የሚሰደደው የአገሪቱ ዜጋ ቁጥር ከቀን ወደ ቀን ከፍ ሊል እንደሚችል ይነገራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.