2015-05-06 15:56:00

ብፁዕ ኣቡነ ፊዚከላ፦ የምኅረት ዓመት የጸጋ ዓመት


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያወጁት የምኅረት ዓመት ለሁሉም ክርስቲያን የጸጋ ወቅትና ሁሉም ክርስቲያን ለአዲስና ለዳግም ኣስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃ የመለወጥ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አፍታ መሆኑ የምኅረት ዓመት ዙሪያ እ.ኤ.አ. ግንቦት  5 ቀን 2015 ዓ.ም. የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የመሩት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ ማብራራታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞካኖ አስታወቁ።

ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ምኅረት ለማቅረብ ሊገታ የማይቻል አቢይና ጥልቅ ምኅረት የማወጅ ፍላጎት እየኖረች ነው፣ ይኽ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ኃሴት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ ገና የምኅረት ዓመት በይፋ ከማወጃቸው በፊት የቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚው የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ዓላማ የጌታ ምኅረት የሚል መሆኑ ቀደም በማድርግ የገለጡት ነው፣ ይኽ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ተጀምሮ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ጌታ በሚከበርበት ዓቢይ በዓል ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ ይክ የምኅረት ቅዱስ ዓመት በተለያዩ መንፈሳዊ ሊጡርጊያዊ ባህላዊና የአስተንትኖ መርሃ ግብሮች አማካኝነት ተፈራርቆ ቀጣይነት ባለው መንፈስ የሚከናወን መሆኑ አብራርተዋል።

ይኽ ቅዱስ ዓመት ከሮማዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጀምሮ በሁሉም ክልል በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚኖር ነው።

በቤተ ክርስቲያን ታውጆ የሚኖረው እያንዳንዱ ቅዱስ ዓመት በመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚኖረው መፍንፈሳዊ እቅድ የገዛ እራሱ ቲዮሎጊያዊ ትርጉምና ፍጻሜ ያለው መሆኑ ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አብራርተው፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቅዱስ የምኅረት በር የሚከፈትበት ቀዳሜ ዓመት መሆኑና ከምኅረት ልኡካነ ወንጌል ማኅበር የቀረበው የዚህ የምኅረት ዓመት ምልክት በዓቢይ ጾም መግቢያ ወቅት የሚታደል ሲሆን፣ ከዚህ በመቀጠልም ካህናት የዚያ የደግ እረኛ አብነት እንዲኖሩ ጥሪ የሚስተጋባበት ወቅት እንደሚሆን አስታውቀዋል።

የምኅረት ዓመት መርህ ቃልና ትእምርት

የምኅረት ቲዮሎጊያ ጽማሬ የሆነው አባ ማርኮ ኢቫን ሩፕኒክ የስነ ቅብና ንድፍ ሥራ ውጤት በቤተ ክርስቲያን አቢይ ክብር የሚሰጠው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ማንኛውም ሰብአዊ ውሱንነት የማያግደው ፍቅር የሚያበስር ሚሥጢረ ትስብአት ያንን የጠፋውን ሰው በእቅፉ በማኖር የሚገለጠው ኵላዊ መዳን እቀድ የሚያወሳ መልካም እረኛ የሰው ልጅ ጥልቅ አካል ሙሉ በሙሉ በመንካት በሙሉ ፍቅር ሕይወቱን እንዲለወጥ የሚለግሰው ፍቅር በሚያብራራና የሚገለጥ ቅዱስ ምስል ሲሆን መርህ ቃሉም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከሉቃስ ወንጌል የተወሰደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እግዚአብሔር መኃሪያን ሁኑ ሲል የሚያቀርበው ጥሪ ነው፣ ይኽ መርህ ቃል እንደ እግዚአብሔር መሃሪ መሆን ማለት እትፍረድ የሚል ፍቅርና ምህረት ለግስ የሚል ጥልቅ የምህረት ትርጉም የሚያብራራ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አስታወቁ።

የምኅረት ዓመት ሊጡርጊያዊ ያከባበር መርሃ ግብር

የእግዚአብሔር ፍጹም ምኅረት በተለያየ ደረጃ በመኖር ብፁዓን ጳጳሳትና ካህናት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ደጋግመው ወደ ጥጋ ጥግ የከተሞቻችንና የኅላዌ ክፍል የጌታ ፍቅር ማድረስ በማለት የሚሰጡት ምዕዳን እንዲኖሩ በቃልና በሕይወት የጌታ ፍቅር እንዲመሰክሩ የሚያነቃቃ፣ ወደ ተናቁት ወደ ድኾች ስደተስኞች በማቅናት ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ስለ ወንድሞች መኖር የሚነቃቃበት የተለያዩ መርሃ ግብሮች ያካተተ መሆኑ ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል።

በዚያ የምኅረት ዓመት መንፈሳዊ ንግደት ስለ ሚፈጽሙ መጸለይ

ወደ ሮማ ለመንፈሳዊ ንግደት ከተለያየ አገሮች የሚመጡት መንፈሳዊ ነጋድያን ሃሳብ ያደረገ ጸሎት የሚከናወንበት ቅዱስ ዓመት መሆኑ ገልጠው የምኅረት ዓመት  በእንግሊዝኛ በስፓንና በፖርቱጋል በፈረንሳይኛ በጀርመንኛና በፖላንድ ቋንቋዎች ሥር ይፋዊ ድረ ገጽ www.im.va በሚል አድራሻ መደረሱ የገለጡት ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ አክለው በዚያ ቅዱስ ዓመት ወቅት የጸጥታና ደህንነት ጉዳይ በተመለከተም ያለው ወቅታዊው የዓለማችን ሁኔታ ግምት በመስጠት የሁሉም መንፍሳዊ ነጋድያን ጸጥታና ደህንነት ዋስትና ለመስጠት በአገረ ቫቲካንንና በኢጣሊያ መንግስት መካከል ስለ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት የጋራ ግኑኝነቶች እንደሚካሄዱ ገልጠው የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማጠቃለላቸው ሎሞናኮ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.