2015-05-01 14:17:00

የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበረሰብ፦ ውይይትና አንድነት የሰላም መንገድ ነው


በኢጣሊያ ባሪ ከተማ ካቶሊካዊ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበረሰብ ያዘጋጀው የመካከለኛው ምስራቅ ማኅበረ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁነትና መጻኢ በሚል ርእስ ዙሪያ የጠራው ዓለም አቀፍ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች መንፈሳውያን መሪዎች የጋራው ጉባኤ የመካከለኛው ምስራቅ ማኅበረ ክርስትያን ለማዳን ውይይትና ውህደት መሠረት መሆኑ እንዳስተጋባ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገለጡ።

በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኘው ማኅበረ ክርስቲያን እምነቱንና ክርስቲያናዊ መለያውን አልክድም በማለቱ ምክንያት ለሞት እየተዳረገ መሆኑና ለሞት የሚዳርገው ተከስቶ ያለው ሁኔታ እሁንም እልባት እንዳጣ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበረሰብ መሥራች የሥነ ታሪክ ሊቅ ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር ገልጠው፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ ምድር ማኅበረ ክርስቲያን ማጥፋትና እንዳይኖር ማድረግ የክልሉ ኅብረእዊነት የሚቀጭ በዚያ ክልል ጥንታዊው የኅብረተሰብ ክፍል የሆነው ማኅበረ ክርስቲያን ለዚያ ክልል የሚሰጠው የላቀው ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ ማጥፋትና መካድ ማለት ሲሆን፣ መካከለኛው ምሥራቅ አለ ክርስቲያን መካከለኛ ምሥራቅ ሊሆን አይችልም እንዳሉ ይገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳብቲነሊ አክልው፦ መካከለኛው ምስራቅ አለ ክርስቲያን መካከለኛ ምስራቅ የሚያስብለው መለያው እንደሚዛባ በጉባኤ ንግግር ያስደመጡት የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ሪቻርድ ጋላገር እንዳሰመሩበትና ይኽ በሳቸው የተንጸባረቀው የቅድስት መንበር ሥጋት እንደሆነም የሚታወቅ ሲሆን፣ ባለፉት የመጨርሻ ቀናት ውስጥ በተለያዩ የመካከለኛው ምሥራቅ ክልሎች የተፈጸመው ሊገመት የማይቻል ለመግለጡም የሚያዳግትና የሚዘገንን ጸረ ማኅበረ ክስቲያን ተግባር መፈጸሙ አስታውሰው በክልሉ የሚታየው ጸረ ማኅበረ ክርስቲያን ጥቃት ከዚያ ክልል ያንን ውሁዳን የኅብረተሰብ ክፍል  ጨርሶ ለማጥፋት ያቀና የዘር ምንጠራ ድርጊት ነው ሲሉ ፕሮፈስር ሪካርዲ ባስደመጡት ንግግር በማብራራት፣ ክርስትና ለዚያ እስላማዊ አምባ ገነናዊ ሥርዓት ውይይትና መከባበር መግባባትን መቀራረብ የሚል የሰብአዊ መብትና ክብር ላይ ያነጣጠረ በቃልና የሕይወት የሚኖር ምስክረት ላይ የጸና መልስ የሚሰጥ ነው። ቤተ ክርስቲያን በተደጋጋሚ በእግዚአብሔር ስም ጸረ ሰባአዊ ተግባር መፈጸም ጸረ እግዚአብሔር መቆም ማለት ነው በማለት የምትገልጠው አቋሟ ሃይማኖት የሰላም መሣሪያ መሆኑ የሚመስከር ነው እንዳሉ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.