2015-04-29 16:32:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና የባን ኪ ሙን ግኑኝነት


በአገረ ቫቲካን ጳጳሳዊ የሥነ ማኅበራዊ ምርምር ተቋም ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተቋሙ መሬትን መንከባከብ፣ ሰውን ማክበር፣ የተፈጥሮ አከባቢ አየር ለውጥ የሚያቀርበው ግብረ ገባዊ ገጽታውና ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ በሚል ርእስ ሥር የጠራው ዓውደ ጉባኤ ከመጀመሩ ቀደም በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጉባኤ ለመሳተፍ አገረ ቫቲካን ከገቡት የተባብሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ተቀብለው ማነጋገራቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ በዓውደ ጉባኤው የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ሰርጆ ማታረላ መሳተፋቸው አስታውቀዋል።

ባን ኪ ሙን ዓውደ ጉባኤ ለመክፈት ባሰሙት ንግግር በቅድሚያ በዓውደ ጉባኤው መገኘታቸውና በጉባኤው መገኘታቸው ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ የሞራል ድጋፍ ለማግኘት ያላቸው ፍላጎት የሚያረጋግጥ መሆኑ ገልጠው፣ ዓውደ ጉባኤ ከመጀመሩ በፊት በግል ከቅዱስ አባታችን ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሚያካሂዱት ወቅት እ.ኤ.አ. መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት አመሪካ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕንጻ ባለው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው ንግግር እንዲያሰሙ የቀረበላቸው ጥሪ በመቀበላቸው አመስግነው፣ ቅዱስነታቸው ምኅዳር ዙሪያ የደረሱት ገና ታትሞ ለንባብ የሚበቃው ዓዋዲ መልእክት ለማንበብ ያላቸው ጉጉት ከፍ ያለ መሆኑ ገልጠው፣ ቅዱስነታቸው ተፈጥሮ ለመከባከብ መከተል የሚገባን መሥፈርት በማመላክት በተለያየ መልኩ ለዓለም የሚያቀርቡት ጥሪ፣ ስለ ስደተኞች ጦርነት እና ግጭት በሚመለከቱ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰጥት ሕንጸት በእውነቱ የሚመስገን ነው እንዳሉ ሳባቲነሊ አስታወቁ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ በአሁኑ ወቅት ያለው የተፈጥሮ ያካባቢ አየር ጤና አሳሳቢ ከመሆኑም ባሻገር ተፈጥሮ ለመንከባከብ ያለው አስፈላጊነት የሚያበስር ነጋሪ ደወል ጭምር መሆኑ ባሰሙት ንግግር ገልጠው፣ ይኽ ርእስ ማሕበራዊ ጤንነት፣ ስደተኛ ልማት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጋር የተቆራኘ መሆኑ አብራርተው፣ የዓለም የተፈጥሮ አካባቢ አየር መንከባከብ ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ ሁሉም የሚመለከት የሁሉም ኃላፊነት ነው፣ ስለዚህ በተፈጥሮ የአካባቢ አየር የሚከሰተው አደገኛው ለውጥ የሚያስከትለው ጉዳት ለይቶ ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ በማቅረቡ ዙሪያ የሥነ ምርምር ዘርፎች እንዲሁም ሁሉም ኃይማኖቶች የሚሰጡት አስተዋጽኦ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የገለጡት ባን ኪ ሙን የተፈጥሮ አየር ለመንከባከብ ዓለም አቀፍ ቅርጽ ያለው ስምምነት አስፈላጊ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ አስታወቁ።

ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ያሰሙት ንግግር ሲያጠቃልሉ በአሁኑ ወቅት እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ያለው በመዲትራኒያን የባህር ክልል ወደ ኢጣሊያና ወደ ኤውሮጳ የሚገባው የሕገ ወጥ ስደተኞች የሚያጋጥማቸው የሞት አደጋ  ነው። የሜዲትራኒያን ባህር የመቃብር ሥፍራ እንዲሆንና የባህሩ ውኃም የሓዘን እምባ ሆነዋል ቢባል ማጋነን እንዳልሆነ ገልጠው፣ የሞት አደጋ የሚያጋጥማቸው ድኾች በቀላሉ ለተለያየ ችግር የሚጋለጡት ከጦርነት ከእርሃብ ከአመጽና ከተለያየ ዘርፈ ብዙ ችግር ገዛ እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ጭምር ለማዳን ተስፋ አንግበው የሚጓዙ ዜጎች ናቸው፣ ስለዚህ የስደተኞች ጸዓት ለመግታት በተለይ ደግሞ የሞት አደጋ እንዳያጋጥም ከውዲሁ ለመግታት በሊቢያ የባህር በር ክልል የሚገኙት ዜጎች በሕገ ወጥ ተግባር ከቦታ ቦታ የሚያጓጉዙ የወንጀል ቡድኖች የሚገለገሉባቸውን መርከቦች ማውደም የሚል የኤውሮጳ ኅብረት የወሰደው ውሳኔ ተገቢ ምላሽ እንዳልሆነ ገልጠው፣ የሚያስፈልገው የወንጀል ቡድኖችን መቆጣጠርና ተከታትሎ ለፍርድ ማቅረብ ነው፣ በዓለማችን የሚታየው ችግሮች መፍትሄ ከውይይት የሚመነጭ አለበት እንዳሉ ሳባቲነሊ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.