2015-04-29 16:37:00

ብፁዕ አቡነ ሶሮንዶ፦ ሥነ ምኅዳር ርእስ ዙሪያ ቅዱስ አባታችን የደረሱት ዓዋዲ መልእክት


ጳጳሳዊ የሥነ ምርምር ተቋም ዋና አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሳንቸስ ሶሮንዶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በአገረ ቫቲካን ጳጳሳዊ የሥነ ማኅበራዊ ምርምር ተቋም ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተቋሙ መሬትን መንከባከብ፣ ሰውን ማክበር፣ የተፈጥሮ ከባቢ አየር የሚከሰተው ለውጥ ያለው ግብረ ገባዊ ገጽታውና ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ በሚል ርእስ ሥር የተጠራው ዓውደ ጉባኤ ለማስጀመር ንግግር ያሰሙት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ  ምኅዳር ዙሪያ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት መጠናቀቁ ገልጠዋል፣ ዓዋዲው መልእክቱም እ.ኤ.አ. 2015 ዓ.ም. ግንቦት ወር ማብቂያ ስኔ ወር መባቻ ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለንባብ እንደሚበቃ ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥነ ምኅዳር ዙሪያ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ቅርጽ ያለው በመሆኑ ይኽ የሥነ ምርምር ተቋም ቅዱስነታቸው የሚገልጡት ሃሳብ ሥነ ምርምራዊ ገጽታው በማቅረብ በዓለም የሚታየው የተፈጥሮ የካባቢ ጤንነት መጓደል መፍሔው  ለይቶ ዓዋዲ መልእክቱን በማስደገፍ ለማስተጋባት አልሞ የጠራው ዓውደ ጉባኤ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ሶሮንዶ ገልጠው፣ ሰው የተፈጥሮ ጠባቂ ነው የሚለው መጽሓፍ ቅዱሳዊ ጥሪና ይኸንን የተፈጥሮ ጠባቂ የመሆን ጥሪው መሠረት ያደረገ የልማት እቅድ በማረጋገጥ እንዲኖር እግዚአብሔር ተፈጥሮን እንዲጠቀምበት ሲል በሰጠው ኃላፊነት ሥር የሚኖር ጥሪ ነው። ተፈጥሮን አለ መጠቀም ሳይሆን የተፈጥሮ ክብር የሚያከብር የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር በሚያከብር ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ ሂደት የሚከተል ተግባር መሆን አለበት። ዓውደ ጉባኤ ይኸን ነው ያበከረው ብለዋል።

አመክንዮ ከሌለ እሳቤ የሚቻል አይደለም፣ አለ አመክንዮ እሳቤ አይኖርም ስለዚህ ከዚህ በመንደርደር እምነት እና ምርምር ተሟይ መሆናቸው እናረጋግጣለን፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዋዲ መልእክት ይኸንን ተሟይነት መሠረት ያደረገ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.