2015-04-29 16:41:00

ቅድስት መንበር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. የኤኳዶር ርእሰ ብሔር ራፋኤል ኮረአ ደልጋዶን ተቀብለው እንዳነጋገሩ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ፦ ከኤኳደር ርእሰ ብሔር ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት ፍጻሜ በኋላ በታንዛኒያ የሲጊዳ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድዋርድ ማፑንዳን ተቀብለው እንዳነጋገሩ አስታውቀዋል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሐዋርያዊ የበላይ ፍርድ ቤት ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዶሚኒክ ማምበርቲ የሐዋርያዊ ፍርድ ቤት የጠበቃዎች ድርገት አባል በማድረግ እንደሰየሙዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.